Breaking News
Home / Amharic / 4 የኦሮሞ የጦር መኮንኖች በፋኖ ተገደሉ።

4 የኦሮሞ የጦር መኮንኖች በፋኖ ተገደሉ።

 

ዛሬ ላይ ”የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት” የሚባል ተቋም የለም። ፈርሷል። ለዚህ ማሳያ በርካታ ነጥቦችን ማንሳት ይችላል። ሻለቃ አህመድ አብረሃም, ሻለቃ ግርማ ፈይሳ, ኮለኔል ሀብታሙ መገርሳ, ኮለኔል አብዲሳ አዱኛ… የተባሉት የአቢይ አህመድ ጦር አዛዥ የኦሮሞ ወታደሮች በማንነታቸው ተመርጠው፣ ፋኖ በተባለው ያማራ ነፍሰ ገዳይ ቀማኞች (murderer mafias) ዴሴ ላይ መገደላቸው ትልቁ ማሳያ ነው።

አቢይ አህመድ የሚባለውን ጨቅላ ሚንስተር የተፈናጠጠችው የነ ዲያቆን ዳንኤል ኢትዮጵያ በዚህ ደረጃ ልጆቿን የምትበላ ነች።

በዚህ ጉዳይ ላይ ይሄ #FinfineeTimes የጻፈው እኔ ካለኝ የውስጥ መረጃ ጋር የሚጣጣም ነው።

*********

ፋኖ ምን አስቦ ነው …???

[By Finfinee Times]

የኦሮሞ ተወላጅ ወታደራዊ መኮንኖች ከህወሓት ጋር ተባብራችኋል በሚል በፋኖ ተረሽኘዋል። ሺህ አለቃ አህመድ አብረሃም .. ሺህ አለቃ ግርማ ፈይሳ ..ኮለኔል ሀብታሙ መገርሳ .ኮለኔል አብዲሳ አዱኛ በፋኖ ደሴ ላይ ተረሽነዋል።

ኮነሬል መንግሥቱ ሀይለማርያም በጦርነት ወቅት ያፈገፈጉ ወታደራዊ አዛዦችን ይረሽኑ ነበር። አንዳንዴ ሰራዊቱ ፊት ለፊት አንዳንዴ ደግሞ ቤተመንግስት አስጠርተው ያስገድሉ ነበር።

በወቅቱ የነበሩ ወታደራዊ ጀነራሎች ይህንን ጉዳይ እያነሱ ለውድቀታቸው አንዱ መንስኤ እንደነበር ይገልፃሉ። ምንም እንኳን ድርጊቱ ተቀባይነት ባይኖረውም …ኮነሬል መንግስቱ ሀይለማርያም ከነበራቸው ስልጣን ስብዕና ተነስተን ይህንን ድርጊት ሊፈፅሙ ይችላሉ።

የአማራ ልዩ ሀይሎችና ፋኖ በየትኛው ሞራልና ስልጣን ይሆን ወታደራዊ መኮንኖችን የገደሉት ? … የተረሸኑት የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው። በዚህም ምክንያት መከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች እያጉረመረሙ እንደሆነ ከታማኝ ምንጮች መረጃዎች እየወጡ ናቸው።

መከላከያ ሰራዊት በዚህ ሰአት ያለምንም ጥርጥር ከእዝ ሰንሰለት እየወጣ ነው። የዘመቻ ሀላፊነት ስራን እየሰራ ያለው የአማራ ክልል ነው። የሎጂስቲክ ጉዳዮችን ከህዝቡ ከሚገኙ እርዳታዎች ነው እየሸፈነ ያለው።

መከላከያ ሚኒስትር በሀገሪቱ እየሆነ ስላለው ነገራቶች መረጃዎች ያሉት አይመስልም። የሆነው ሆኖ የዛሬው የፋኖ ተግባር በቀላሉ የማይታለፍ ተግባር ነው። የመጨረሻው መጀመሪያ ጊዜ ሲመጣ እንደዚህ አይነት ክስተቶች በእርግጥ ያጋጥማሉ።

መዋቅር ይፈርሳል … እምቢተኝነት ይነግሳል .. የእዝ ሰንሰለቱ ይላላል .. ሞራል ይደቃል ..ነገራቶች ከተግባር ይልቅ በወሬ ይቀየራሉ .. መደማመጥ ይቀራል .. እርስ በርስ መጎሻሸም መጋጨት ይመጣል። በመጨረሻም የማይቀረው ክስተት ይፈጠራል። ይህም እየደረሰ ስለመሆኑ አይቶ መናገር ይቻላል።

One comment

  1. በቀለ ገብሬ

    መኮንኖቹ ለምን እንደተገደሉ ማጣራት ያስፈልጋል፡፡ የወያኔ እጅ ገብቶባቸውም ሊሆን ይችላል፡፡ ይሄ ደግሞ ጦርነቱ ከተጀመረ አዲስና የመጀመሪያ እንዳልሆነ ይገመታል፡፡ሁሉም እዚያ ያሉት ለአንድ ዓላማ ነው፡፡ ተቃራኒ ዓላማ ይዞ ወይም ለጠላት ሲሠራ ከተገኜ በጦር ሜዳ እንደዚህ ያለው እርምጃ የሚጠበቅ ነው፣ ይህንን አውቆና ቆርጦ የሚገባበት ነው፡፡ እርምጃ የሚወሰደው በብሔረሰብ ማንነቱ ሳይሆን ሠራዊቱ ከቆመለት ዓላማ ውጭ ሀገርን፣ ሕዝብን እና ሠራዊቱን የሚጎዳ ሆኖ ሲገኝ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ይሔ ዓይነቱ እርምጃ ከአሁን በፊትም አማራ ነን በሚሉ ባንዳዎች ላይም ተወስዱዋል፡ ፊንፊኔ ታይምስ ግን ለመዘገቡዋ እርግጠኛ ዐይደለሁም፡፡ ለልዩ ሓይልና ፋኖ ምን ሞራል ኖሮአቸው ነው የሚረሽኑት የሚለው ከተራ ጥላቻና ጠባብ ብሔርተኝነት ያለፈ አይሆንም፡፡ ይልቁንም የበላይ አመራሮች በቅርበት አየተገኙ የየዕለትውሎወዎችን እየገመገሙ ማስተካከያ እርምጃ አለመውሰድና ዳር ዳሩን እየሄዱ ችላ ማለት ለሠራዊቱ፣ ለሀገሪቱና ለራሳቸውም ጭምር አደጋ ሊሆን እንደሚችል ማንም ሊገምተው የሚችል ነገር ነው፡፡ ይህ ሲባል ግን ችግሩን የዚህ ወይም የዚያ ብሔረሰብ ነው ብሎ ነገሮችን በብጣብልጥነት ከድብቅ አጀንዳ ጋር አያይዞ ችላ ማለት የሚገባውን ኃላፊነት አለመወጣት ነው፡፡

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.