ኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ መከሰቱ ከተነገረ በሗላ በአዲስ አበባ ከተማ በጤና መጠበቂያ ቁሶች እንዲሁም በግብርና ምርቶች ላይ ያለአግባብ ዋጋ ጨምረው የተገኙ 188 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል።
አንዳንድ ፋርማሲዎች 5 ብር የነበረውን የአፍ መከላከያ እስከ 200 መቶ ብር፣ ነጭ ሽንኩርት ከ100 – 110 ብር የነበረውን ከ250 – 290 ብር፣ ሙዝ በኪሎ 25 ብር የነበረውን 60 ብር፣ በርበሬ 90 ብር የነበረውን 130 ብር ሲሸጡ የተገኙ ድርጅቶች እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።