ሰበር መረጃ፦
የዐማራን ህዝብ መንግስታዊ መዋቅር ዘርግቶ በጦርነት፣ በረሃብ፣ በበሽታ እንዲጠቃ በማድረግና በሌሎችም ረቂቅ ዘዴዎች ለማጥፋት ተግቶ እየተንቀሳቀሰ ያለው የዓብይ አህመድ ኦሮሙማው አስተዳደር በ 2016 ዓ.ም የበጀት ዓመት በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ “የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት” በሚል ሽፋን ከ 120 ሺህ በላይ የዐማራ ወጣት ሴቶችን ለአረብ ሃገራት መሸጡን ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ከዓመታት በላይ ከ 100 ሺህ የሚልቁ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሳውዲ የበረሃ እስር ቤቶች ታጉረው በሚፈጸምባቸው ሰቆቃ፣ ረሃብና የህክምና እጦት እያለቁ በሚገኙበት ሁኔታ ተጨማሪ ከ 120 ሺህ የሚልቁ ተምረው ቤተሰብን መርዳት እንዲሁም ትዳር መስርተው ልጆች ማፍራት የሚችሉ ወጣት የዐማራ ሴቶችን “የሞት ምድር” ወደሚባለው መካከለኛው ምስራቅ በስራ ሽፋን መላካቸውን ዛሬ በኩራት የገለጸችው፤ የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል ናት።
የአብይ አህመድ ዋና የቀኝ እጅ መሆኗ የሚታወቀው፣ ለዐማራ ህዝብ እጅግ የመረረ ጥላቻ ያላትና ጅማ ተወልዳ ያደገችው ጽንፈኛ የስልጤ ፖለቲካ አቀንቃኟ ሙፈሪያት እንዲሁም በሚኒስትር ማዕረግ የኡብይ የውጭ ግንኙነት አማካሪ የሆነው ሬድዋን ሁሴን፤ በስልጤ ዞን፣ እንዲሁም በደቡብ ክልል እንደ ጉራፈርዳ ባሉ አካባቢዎች በዐማራዎች እና የኦርቶዶክስ አማንያን ላይ ለተፈጸሙ ጥቃቶች በተጨማሪም ለአብያተ ክርስቲያናት ቃጠሎና ውድመት ተጠያቂ ተደርገው በተደጋጋሚ የሚከሰሱ ናቸው። ኦሮሙማው ቡድን ከ 95 በላይ የስልጠና እና መመልመያ ማዕከላትን ከፍቶ ከግማሽ ሚልዮን በላይ የሚገመቱ የዐማራ ሴቶችን ወደ አረብ ሀገር ለሰቆቃ ለመዳረግ እንቅስቃሴ ውስጥ ሲገባ፤ ጉዳዩን ያስፈጽሙ የነበሩት ከዓመታት በፊት በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የዐማራ ሴት ተማሪዎች በኦነግ ሸኔ በታፈኑበት ወቅት “ውሸት ነው” እያለ የእነ ዓብይን እኩይ ገመና ሲሸፍን የነበረው አሁን ላይ ደግሞ ሙፈሪያትን እንዲያግዝ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተደርጎ የተሾመው ባንዳው ንጉሱ ጥላሁን እና የቀድሞው የዐማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ ናቸው።
እጅግ የሚያሳዝነው ኢትዮጵያውያኑ በዓለም የመጨረሻው ዝቅተኛ ክፍያ እንዲከፈላቸው መዋዋሉና የስራና ደህንነት ዋስትና የሌላቸው መሆኑ በዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በተደጋጋሚ ሲነቀፍ የቆየ ሲሆን፤ ከሚያገኟት ከእጅ ወደ አፍ የማትሞላ የዶላር ክፍያም መንግስት እየቆረጠ እንደሚወስድባቸው መጋለጡ ለሞት መላኩ ሳያንስ ተጨማሪ የሚፈጽምባቸው የባርነት የጉልበት ብዝበዛ የግፍ ግፍ መሆኑ እየተገለጸ ነው።
ሕዝባችንን በኦሮሙማው ጦር ማስጨፍጨፋቸው ሳያንስ፤ እንዲህ ለሞትና ባርነት የሚዳርጉን የብአዴን ጉግማንጉጎች በፍጥነት ከዐማራ ክልል ብቻ ሳይሆን ከመላው ኢትዮጵያ ተጠራርገው ሊወገዱ ይገባል።