Breaking News
Home / Amharic / የባህርዳር ከንቲባ ዶ/ ር ድረስ ሳህሉ በባህርዳር ከተማ የሚገኙ ፋኖዎችን እንዲበተኑ አደረጉ።

የባህርዳር ከንቲባ ዶ/ ር ድረስ ሳህሉ በባህርዳር ከተማ የሚገኙ ፋኖዎችን እንዲበተኑ አደረጉ።

አላማጣ፣ቆቦ፣ወልዲያ፣መርሳ፣ወርጌሳ፣ውጫሌ፣ መሃል አምባ ኮምቦልቻ ወዘተ የአማራ ክልል ከተሞች በትግራይ ወራሪ ሀይል እንደተያዙ ነው።
ከ200 በላይ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችን በባህርዳር ማረሚያ ቤት አስሮ ማስቀመጡ ሳያንስ በዚህ ሰአት ፋኖን መበተን ምን ማለት ነው
የክልሉ መንግስት ምን አይነት ስራ ነው እየሰራ ያለው???

የብአዴን ነገር ታጥቦ ጭቃ ነው ወገኖች። በባህርዳር የአማራ ፋኖ ስልጠና እንዲቆም ታዟል ። ትንሽ ድል ተገኝቶ ጁንታው ሲሸሽ ፋኖን ለጎሪጥ ማየቱ አሁንም ቀጥሏል። በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 8 ፔዳ አካባቢ የአማራ ፋኖ በባህርዳር በሚል ስም ተደራጅተው ከ15 ቀን በላይ ጊዚያዊ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ ከ4ሺህ በላይ ፋኖዎች ባልታወቀ ምክንያት ከዛሬ ህዳር 25/2014 ዓ.ም ጀምሮ በቦታው መሰልጠን እንደማይችሉና ስልጠናውን ማቋረጥ እንዳለባቸው ተነግሯቸዋል ።

የሚያሳዝነው 2380 አባላት ያሉበት አባላት መሰልጠን እንደማይችሉ ለመንገር የፌዴራል ፖሊስ ኃይልና መከላከያ ነው የላኩባቸው ፣ ቀድመው ቦታው ላይ ተገኝተው ስልጠናውን የጀመሩት ወጣቶች ከፍተኛ የሆነ ድብደባና ወከባ ደርሶባቸዋል ።
ስልጠናውን ሲወስዱ የነበሩ ጁንታው በአማራ ላይ እያደረሰ የሚገኘው ጭፍጨፋ፣ ንብረት ማውደም፣ የእናቶች መደፈርና መፈናቀል የቆጫቸው በከተማው በተለያዩ የንግድ ሥራ የተሰማሩ ባለሐብቶች ፣ መምህራን ፣ ወጣቶችና ተማሪዎች ነበሩ ። ለምን ብለው ሲጠይቁ መሰልጠን ከፈለጋችሁ መከላከያ ወይም ልዩ ኃይል ነው መቀላቀል ያለባችሁ እንጅ እንዲህ አይነት ህገ -ወጥ ስልጠና ይቁም ተብሎ ከበላይ ትዕዛዝ መጥቷል የሚል መልስ ተሰጥቷቸዋል ።

አሁንም እንላለን ብአዴን ከበላይ አካል ቀጭን ትዕዛዝ መቀበሉን ያቁም ፣ አመራሩ ትዕዛዝ መቀበሉን ትቶ ችግር ውስጥ የሚገኘውን ህዝብ የፋኖን አቅም በሙሉ በሙሉ ተጠቀሞ ጦርነቱን በአጭር ቀን ተጠናቆ ወደ ልማት እንመለስ ።

የደራ ወርቅ ቤተ-አማራ

SUPPORT AMHARA FANO

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.