Breaking News
Home / Amharic / ፋና ብሮድካስቲንግ እና ዋልታ ኢንፎርሜሽን ብሄራዊ ጣቢያው ኢቲቪ አልተገኙም!

ፋና ብሮድካስቲንግ እና ዋልታ ኢንፎርሜሽን ብሄራዊ ጣቢያው ኢቲቪ አልተገኙም!

 
በኦሮሚያ ክልል በወለጋ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል እንዲሁም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተፈጸመ ያለውን ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ በተመለከተ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)፣ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ(ባልደራስ)፣ እናት ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትኅ ፓርቲ(ኢዜማ) እና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ትዴፓ) በጋራ ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 25 ቀን 2013 ዓ.ም መግለጫ ሰጠው ነበር ።
ነገር ግን የህወሀት የቀድሞ ንብረቶች ፋና ብሮድካስቲንግ እና ዋልታ ኢንፎርሜሽን እንዲም ጠሚዶ በሄደበት ሁሉ የሚያዘጠዝጠው ኢዜአ እና ለመጣ ለሄደው አፋሽ አጎንባሹ ብሄራዊ ጣቢያው ኢቲቪ አልተገኙም ።አርትስ ቲቪ እና ባላገሩ ቲቪም ፈርተው መግለጫው ላይ አልተገኘም ። ማተብ አስበጣሹ EBS የዐቢይን ግልምጫ ሰግቶ እሱም አልተገኘም። ከምንም በላይ የገረመኝ እና ሲሆን መተከል እና ወለጋ ወርዶ መዘገብ የሚጠበቅበት የእኛው ጉድ አሚኮ(የቀድሞ አብመድ) መግለጫው ላይ አለመገኘቱ ድንቅ ብሎኛል (በእርግጥ ካሜራ ሳይዙ ባዶ እጃቸውን ጋዜጠኞች ተገኝተዋል) ለሌላ መንግስታዊ ድግስ የሚንጋጋ ካሜራ ለእዚህ ጊዜ ያልሆነ ለመቼ ሊሆን ነው?
ለማንኛውም ለአንድ ጉዳይ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በጋራ መቆም ሚዲያውን ሊያስደስተው ሲገባ መደንበሩ በእጅጉን ገርሞኛል ።

One comment

  1. This type of cooperation should continue, include more parties and consolidate solidarity to get your voices heard. Continue this way, many people are happy today.

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.