Breaking News
Home / Amharic / ጥሪ ለአማራ ተወላጆች በዲያስፖራ ! ድረሱልን !

ጥሪ ለአማራ ተወላጆች በዲያስፖራ ! ድረሱልን !

 
አርቆ አሳቢው የአማራ ህዝብ ሀገር ለመመስረት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ሀገራዊ አንድነትን አንግቦ ከክልሉ ውጪ በመውጣት ሰው የማይኖርበትን ጫካ እየመነጠረ መንገድ እየሰራ
ጫካውን ወደ ከተማነት እየቀየረና ለኑሮው የሚያስፈልጉትን ግብአት እያሟላ በሄደበት ስልጣኔን እያስተማረ እዛው ላይ ጎጆውን እየቀለሰ ሀብት ንብረት አፍርቶ ከብሔሩም በላይ
ኢትዮጵያዊነቱን አስቀድሞ የሚኖር የሀሳብና የተግባር ባለቤት ነው።
 
👉ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ አማራው ሊመሰገንና ሊሸለም ሲገባው በተቃራኒው የሞት ፍርድ ተፈርዶበት ለብዙ ዘመናት በግፍ በካራ እንደ በግ ሲታረድ፣ከነ ሂወቱ ገደል ሲሰደድ፣በቁሙ በዕሳት ተለብልቦ ሲቃጠልና ለብዙ ዘመናት ደክሞ ያፈራውን ሀብት ንብረት በእሳት ሲነድበት ማየት ምነኛ ያማል።
 
👉ይሄን ግፍና ጭቆና መቋቋም የከበደው ከክልሉ ውጪ የሚኖሩት አማሮች ሂወታቸውን ለማትረፍ በዚህ ፈታኝ ወቅት ከኦሮምያ ክልል በመፈናቀል ወደ ትውልድ ቀያቸው እየተመለሱ እንደሆነም በሰፊው እያስተዋልን ነው።
 
👉ከዚህ ውስጥም በሰሜን ሸዋ ዞን መርሃቤቴ ወረዳና ዓለም ከተማ ውስጥ በቁጥር ከ150 እስከ 200 የሚደርሱ ተፈናቃዮች እንዳሉ ለማረጋገጥ ችለናል።
👉ስለዚህ ከሞት አምልጠው ለመጡት ወንድም እህቶቻችን ጋር ከጎናቸው በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ አማራዊ ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል።
👉 በመጨረሻም መንግስት ትኩረት ባለመስጠቱ ለተፈናቃይ ብሎ የተመደበ እህል እንኳን ወቅቱን ጠብቆ እንደማይሰጣቸ በተለይ ከኮራና ጋር ተያይዞ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችል ግብአት ስላልተረዱ ብዙ እንግልት እንደደረሰባቸው፣ማረፊያ ቦታም ሆነ ከቦታ ቦታ በነፃነት ለመንቀሳቀስ ይረዳቸው ዘንድ የመታወቂያ ካርድም እንዳልተሰጣቸውም ከአንደበታቸው በመስማት ለማረጋገጥ ችለናል።
👉 ማሳሰቢያ :- የአማራ ክልል መንግስት ከክልሉ ውጪ ያሉትን አማራዎች መታደግ ተስኖት ዛሬ ላይ ደሞ ይሄን በማይባል ሲቃይ ውስጥ አልፈው ወደ ክልልላቸው ለገቡት ተፈናቃዮች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ባፋጣኝ ወደ መልሶ የማቋቋም ስራ እንዲሰራ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
እባካችሁ ለወገን እንድረስለት :: የቻልነወን ያህል እንርዳ !
 
 
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.