Breaking News
Home / Amharic / ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የ2019 የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸንፈዋል፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የ2019 የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸንፈዋል፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የ2019 የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸነፉ
********************
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማትን በማሸነፋቸው 9 መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም 9 ሚሊዮን የስዊድን ክሮነር ይበረከትላቸዋል፡፡

ዘንድሮ ለዘርፉ ከቀረቡ እጩዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የ16 ዓመቷ ስዊድናዊት የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋች ግሪታ ተንበርግ በሰፊው ያሸንፋሉ የሚል ግምት ተሰጥቷቸው ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከ20 ዓመት በፊት ደም አፋሳሽ የነበረውንና በርካታ ሰዎች ያለቁበትን የኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት መቋጫ እንዲያገኝ አድርገው ሰላም በማውረዳቸውና ምስራቅ አፍሪካ የትብብር ቀጠና እንዲሆን ያደረጉት ድፕሎማሲያዊ ጥረት የኖቤል ሽልማቱን እንዲያሸንፉ ጉልህ ሚና ተጫውቷል ተብሏል፡፡

በተለይም ወደ ደም መፋሰስ እየገባች የነበረችው የሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች ተደራድረው የስልጣን ክፍፍል በማድረግ ወደ ሰላም መመለሳቸውም ትልቅ ዋጋ የሚያሰጥ ስኬት ተደርጎም ተወስዷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአንድ ቀን 350 ሚሊዮን ችግኝ ማስተከላቸውና በእርሳቸው አመራር የካቢኔያቸውን ግማሹ በሴቶች እንዲያዝ ማድረጋቸውም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲቸራቸው ያደረገ መሆኑን የፖለቲካ ጠበብቶች ግምታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በተለያዩ መስኮች ጉልህ ተግባራቶችን ያከናወኑ ግለሰቦችን ተቋማት በየዓመቱ የሚሸለሙበት የኖቤል ሽልማት በአለማችን ከሚሰጡ ሽልማቶች መካከል ቀዳሚው ነው፡፡

የኖቤል የሰላም ሽልማት እስካሁን ለ133 ግለሰቦችና ተቋማቶች ተሰጥቷል፡፡ እ.ኤ.አ 1938 ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ለኖቤል ሽልማት መታጨታቸው የቢቢሲ መረጃ ያሳያል፡፡
ምንጭ EBC

ይህ ሽልማት ቀላል ነገር አይደለም። ከባድ ዲፕሎማቲክ ክንድ ነው። የሚሰጥህም ባለፈው እድሜ ለሰራኽው ብቻ አትደለም። ከአሁን በሁዋላም ለምታደርገው effort የሚሰትህ ሃላፊነት ነው። ለሰላም፣ ለእኩልነት ፣ ለአንድነት እና ነፃነት ማለት ነው። ይሄ ሽልማት መከራን ችሎ እና ታይቶ በማይታወቅ ትእግስት ፣ ልጆቹን እየገበረ ፣ መስጅድ እና ቤተክርስትያን እየተቃጠለበት ፣ ባንኮች እየተዘረፈበት ፣ ተሰዶ እና ተፈናቅሎ በየመጠለያው የተደፋው ፅኑ ህዝባችን ያስገኘለት ክብር ነው። ሲያንሰን ነው። ሌላ አገር ቢሆን ኖሮ የገሃነም በሮች ይከፈቱ ነበር። ይሄን ዴክተር አብይ ያውቀዋል። አሁን እኛ ጥያቂያችን ፣ ይህን ክብር ይዘህ ከአሁን በሁዋላ የምትሰራው ምንድን ነው መሆን ነው ያለበት።

 

ለሁሉም ግዜ አለዉ እንካን ደስ አለህ አብይ እኔ ይህንን ስሰማ በጣም ደስታየ እጥፍ ድርብ ሆነ ግን ቤት ክራይ አስመርሮኛል ተዉ አንድት ክላስ ቤት ለኔ አጥተህ ነዉ እባክህ??????????

 

Tesfaye Gabriel Now it is a time to form a UNITED ETHIOPIA, forgetting behind old fashioned thoughts. Big congratulations to Dr Abiy and all Ethiopians. Many thanks to our Lord God for his achievement.

Solomon T Gebru When some of our the so called politicians trying to undermine his work and every single day trying to destroy his reputation the world recognizes him as a great young leader , I hope they learned a lesson , some of them they were in politics even before he was in office.

ሽልማቱ የኤርትራንና የኢትዮጵያን ህዝቦች የማስታረቅ ጉዳይ ከሆነ እርቁን ተክትሎ ህዝብን ለማቀራረብ በሁለቱ መንግስታት አንዳችም የተሰራ ነገር አላየንም። ይልቁንም የሁለቱ ሀገራት ጦርነትና የህዝብ የ20አመት ስቃይ ያደረስውን ማህበራዊ ቀውስ በደንብ እንድንረዳው ያደረገው ሳይታክትና ሳይሰለች በርካታ የተጠፋፉ ቤተሰቦችን አፈላልጎ ያገናኘውና የፍቅርና የቁጭት እንባ ያራጨን ጆሲ (የሴፍ ግብሬ) እንዲሁም የቴሊቪዥን ጣቢያው ምስጋና ይገባቸዋል።

Begashaw Kebede አለም በተለያየ ምክንያት መሪዎችን ያደንቃል።
በአንድ ወቅት ያደነቁትንም ፣ በሌላ ግዜ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ አድርገው ሲያወግዙም ብዙ ግዜያት ታይቷል።
ዋናው የየትኛውም ሃገር ዜጎች ጥያቄ ግን “መሪዬ በእኔ ኑሮ እና ህይወት ውስጥ ምን ለውጥ አምጥቷል? በሌሎች የተደነቀበት ጉዳይ (ሰላም) የእኔን ኑሮ እና ህይወት ይገልጻል ወይ?” እና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ናቸው።
መንግስት አለ ወይስ የለም እያሉ የሚጠይቁ ብዙ ሚልዮን ዜጎች ፣ ጉልበተኞች/አሸባሪዎች እንዳሻቸው የሚፈነጩባት ሃገር ህዝቦች ፣ በየመጠለያ ጣቢያው ይሚንገላቱ ሚልዮኖች ፣ ከቦታ ቦታ መዘዋወር ያቃታቸው እና በስጋት የሚወጡ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን በዛሬው ሽልማት የሚያገኙት ደስታ ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል አላውቅም።
እኔን ግን ፣ በእርግጠኝነት ፣ ከእአስፈሪ ጭንቀቴ አልገላገለኝም። እንኳን ሊገላግለኝ ፣ የተሳለቁብኝ እና በቁስሌ ላይ ጨው እንደጨመሩበት ሆኖ ነው የተሰማኝ።
ችግራችን ከሰው አቅም በላይ ነው እና ፣ ፈጣሪ ይድረስልን።

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.