ጉዞ ወደ አዲስ አበባ ፣ መስመር አንድ #ግርማካሳ
በቴሌግራም
https://t.me/wameraGK
ለፋኖዎች አዲስ አበባ ለመግባት እንዴት ቀላል እንደሆነ ከጂዮግራፊ ርቀት አንጻር አንዳንድ ሃሳቦች በሚቀጥለውት ጥቂት ጦማሮች ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡ ከወታደራዊ ጥንካሬ፣ ከጂዮግራፊ አመቺነት ወይም ቶፖግራፊ አንጻር ወዘተ ብዙ ማሳያዎች ይቀርባሉ፡፡
ይህም መረጃ መስጠት አይደለም፡፡ ማንም ወታደራዊ አመራር የሚያወቀው ሃቅ ነው፡፡ ፡ ነገር ግን አገዝዙ እየተሸነፈ እንደሆነ ለማሳየትና አላስፈላጊ ጥፋት ከመድረሱ በፊት ብልጽናዎችንና የጦር ጀነራሎቻቸውን ለማስጠንቀቅ ፣ እጅ እንዲሰጡና እየተሸነፉ መሆናቸውን እንዲያምኑ ለማድረግ ነው፡፡
በደብረ ብርሃን መስመር ኦሮሞና አማራ ክልል ከሚያዋስነው የመጀመሪያው ወሰን ቦታ ተነስተን አዲስ አበባ ለመሄድ፣ 79 ኪሎሜትር ወይንም የአንድ ሰዓት ተኩል መንገድ ይወስዳል፡፡
በዚህ መስመር ሁለት ጊዜ አማራ ክልል ተገብቶ ነው አዲስ አበባ የሚደረሰው፡፡ የመጀመሪያው ሸኖ ከመገባቱ በፊት ወደ አማራ ክልል ይገባል፤ ሸኖ ለብቻ ተቆርጣ ዳር ዳሩን ወደ ኦሮሞ ክልል እንድትገባ ስለተደረገ ወደ ኦሮሞ ክልል ተመልሰን እንገባለን፡፡ ሸኖ ከታለፈ በኋላ ደግሞ እንደገና አለለቱ ከመገባቱ በፊት ወደ አማራ ክልል ይገባል፡፡፡ በዋናው መንገድ ወደ 20 ኪሎሚተር የሚሆነውን በአማራ ክልል ውስጥ የምናልፈው፡፡ ስለዚህ ከመጀመሪያው የኦሮሞና አማር ክልል ድንበር ተነስተን አዲስ አበባ እስንደርስ ድረስ፣ በኦሮሞ ክልል የምንጓዘው 59 ኪሎሜትር ነው ብቻ ነው፡፡
ከአዲስ አበባ ተነስተን ወደ ደብረ ብርሃኑ ስንጓዝ መጀመሪያ አምራ ክልል ውስጥ የምንገባው ልክ አለለቱን አልፈን 47 ኪሎሜተር ብቻ ከነዳን በኋላ ነው፡፡ በጣም ቅርብ ነው፡፡ከአዲስ አበበ ሞጆና ድብረ ዘይት እንደማለት ነው፡፡
እነ ሸኖ እነ አለልቱን ብንወሰድ በከተሞቹ በብዛት ያሉት አማርኛ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡ ብዙዎቹ የኦሮሞና የአማራ ውህዶች ናቸው፡፡ ሰንዳፋና ለገጣፎንማ እርሷቸው፡፡ አዲስ አበባ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡
በነዚህ አካባቢዎች ፋኖዎች መንቀሳቀስ ሲጀምሩ፣በተወሰነ መልኩም ጀመረዋል፣ “ይህ አካባቢ ያለው ማህበረሰብ ይደግፋቸዋል ወይስ ይቃወማቸዋል? ” የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ይረዳ ዘንድ ፣ ከደብረ ብርሃን አዲስ አበባ ያለው ዲሞግራፊ ምን እንደሚመስል መጠነኛ ግንዛቤ እንዲኖር ነው ይህን ያሰፈርኩት፡፡
ይህ አካባቢ ባሌ ዲንሾ ወይንም ወለጋ አንፊሎ አይደለም፡፡ ለጽንፈኛ ኦነጎች ድጋፍ የሚሰጡ የበዙበት አካባቢ፡፡ በዚህ አካባቢ ያለው ማህበረሰብ ያለ ምንም ጥርጥር ፋኖን የሚደገፍ ፣ ከፋኖ ጎን የሚቆም ማህበረሰብ ነው፡፡ በዚያ ያለው አማራው፣ ውህዱ፣ ኦሮሞውም ሳይቀር፡፡ በዚያ ያለው ኦሮሞ የባሮ ቱምሳ ወይንም ዋቆ ጉቱ ኦሮሞ አይደለም፣ የራስ ጎበና ዳጬ የቱለማ ሚኒሊካዊ ኦሮሞ ነው፡፡
በዚህ አካባቢ ፋኖዎች ሲንቀሳቀሱ፣ “ኦሮሚያ ውስጥ ስለሆነ፣ ኦሮሞ አያሳልፋቸው” የሚል አመለካከት አለ፡፡ ይህ አመለካከት ከእውቀት ማነስ የመነጨ አመለካከት ነው፡፡ ኦሮሚያ የሚባለው በኦነግና በህወሃት ሲሸነሸን በርካታ በኦሮምያ ውስጥ በተከታተሉ አካባቢዎች፣ በተለይም ሸዋ፣ ኦሮሞ ያልሆኑ በብዛት መኖራቸውን አለመረዳት ነው፡፡
እንግዲህ ፋኖዎች አንድነታቸውን ካጠናከሩ፣ በተለይም የሸዋ ፋኖዎች በአንድ እዝ ስር በቶሎ ከመጡ፣ ከደብረ ብርሃኑ፣ ጫጫ፣ ሸኖ፣ አለለቱ ፣ ሰንዳፋ፣ ለገጣፎ ብለው አዲስ አበባ ከች ለማለት በሚያደረጉት እንቅስቅሴ፣ በዚያ መስመር ያለው ህዝብ ከጎናቸው ሊሆን እንደሚችል በዚህ አጋጣሚ ልገልጽላቸው እወዳለሁ፡፡ ምንም አይነት ችግርም ሆነ እንቅፋት በህዝብ ድጋፍ አንጻር አያገኛቸውም፡፡ ማድረግ ያለባቸው አንድ ነገር ነው፡፡ እርሱም በጥቃቅን ነገር ጊዜ ማጥፋት አቁመው፣ አንድ ይሁኑ፣ በአንድ እዝ ስር ይሰባሰቡ፡፡
የሸዋ ፋኖዎች አንድ መሆን ካልቻሉ ኝ አዲስ አበባ መግባቱን እርሱት፡፡ እንደውም አገዛዙ በስሜን ሸዋ የበለጠ እየተጠናከረ ይመጣል፡፡ እንደገና አፈር ልሶ ይነሳል፡፡ ፋኖዎች እየተዳከሙ ይሄዳሉ፡፡