የ35 የአማራ፣ 2 የአፋር ባለሃብቶችና ድርጅቶች የባንክ አካውንት ታገደ
የአማራ ሕዝብ ትግልን ሊደግፉ ይችላሉ በሚል፤ የአማራ ባለሃብቶችን ለማሠርና ንብረታቸውንም ልክ እንደ ትጥቁ ለማስፈታት እንቅስቃሴ መጀመሩን ትናንት በዘ-ሐበሻ ዜና መዘገባችን ይታወቃል።
በኦሮሚያ ብልጽግና ሰዎች የሚመራው የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዛሬ ለሁሉም ባንኮች በጻፈው ደብዳቤ የ35 የአማራ ባለሃብቶች እንዲሁም 2 የአፋር ባለሃብቶች በባንክ ያላቸው ገንዘብ እንዲታገድ
ለሁሉም ባንኮች የጻፈው ደብዳቤ ዘ-ሐበሻ እጅ ገብቷል። ይህም በኦሮሚያ ብልጽግና እና በአማራ ብልጽግና መካከል ያለውን ሽኩቻ አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ የብልጽግና ምንጮች ይናገራሉ። ደብዳቤውን ተመልከቱት፤ ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመጣለን።
በነገራችን ላይ የሞቱ ሰዎችም ጭምር በ እገዳው ስማቸው ተጠቅሷል።
===============
የአማራ ባለሃብቶችን ማሰር ሊጀመር መሆኑን ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገለጹ:: ብሔራዊ ባንክ ለባለሃብቶቹ ብድር እንዳያራዝም የተከለከለ ሲሆን መክፈል ሲያቅታቸው ንብረታቸውን በሃራጅ ለመሸጥና ሃብቱንወደሌሎች ለማሻገር በሚመስል መልኩ እየተሰራ መሆኑን ምንጮች ተናግረዋል:: እነዚሁ በብሔር አማራ የሆኑ ባለሃብቶች ተመርጠው ዘመቻ የተከፈተባቸው ሲሆን አንዳንዶቹም ቢሯቸው እየተሰበረ ፋይል እንደተወሰደባቸው: የባንክ አካውንቶቻቸው እየታገደባቸው መሆኑ ታውቋል::

