Breaking News
Home / Amharic / ጀነራል ተፈራ በጠና ታመዋል። ውጭ ሄደው እንዳይታከሙ ተከለከሉ።

ጀነራል ተፈራ በጠና ታመዋል። ውጭ ሄደው እንዳይታከሙ ተከለከሉ።

 
ፈራ ማሞ

 

የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ከአገር እንዳልወጣ ከአዲስ አበባ አየር ማረፊያ ተከለከልኩ አሉ።

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ትናንት ረቡዕ ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም. ወደ እስራኤል አገር ለሕክምና እና ለጉብኝት ለመጓዝ ከተነሱ በኋላ ጉዞ ተከልክለው መመለሳቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ብርጋዴር ጄኔራሉ የፓስፖርት ቁጥጥር የሚደረግበትን ስፍራ ካለፉ በኋላ ጉዞ ማድረግ እንደማይችሉ ስለተነገራቸው ወደ ቤታቸው ለመመለስ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ለክልከላው የተሰጣቸው ምክንያት “ከላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው” የሚል መሆኑን የገለጹት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ፤ የጉዞ ክልከላው ምክንያት ምን እንደሆነ ለመጠየቅ ወደ ኢሚግሬሽን ከሄዱ በኋላ፤ “የበላይ አመራሮችን ጠይቀን ምላሽ እንሰጣለን” የሚል መልስ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ጉዞ እንዳያደርጉ የተከለከሉት ከዚህ ቀደም ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉበት ጉዳይ ጋር ስለመያያዙ በግልጽ የሚታወቅ ነገር የለም።

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ግን አሁን ላይ ከአገር እንዳይወጡ የተከለከሉት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉበት ጉዳይ ጋር “የተያያዘ አይደለም” ብለዋል።

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.