ፓርላማ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራር ስነ ስርዓት ደንብ መሰረት አንድ አባል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ ለማቅረብ ከ10 ቀን በፊት ለአፈ ጉባዔ ጽ/ቤት ማስገባት ይጠበቃል።
ከዚያም ከአባላት የተሰበሰቡትን ጥያቄዎች አፈጉባኤዎችና በፓርላማው የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተሰባስበው የሚፈልጓቸውን ይመርጣሉ። የተመረጡ ጥያቄዎች ለጠ/ሚ/ሩ ይቀርባሉ ማለት ነው።
ከታች የተያያዙትን ጥያቄዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለማቅረብ ከ15 ቀን በፊት ብናስገባም የገዢው ፓርቲ በመቀስ ቆርጦ አስቀርቷቸዋል። ፓርላማው በብዙ አፋኝ ህገ ደንቦችና አሰራሮች መተብተቡና ሰፊ የአሰራር ማሻሻያዎችን እንደሚያስፈልግ አመላካች ነው።
ደሳለኝ ጫኔ (NAMA)