የፋኖ አንድነት ምክር ቤት አንደኛ አመት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ መግለጫ
ክፍል 1፡ ሁሉም ስለ ፋኖ ሊያውቀው የሚገባ እውነታ
መግቢያ
ፋኖ በዮቲዩብና በአንዳንድ ሚዲያዎች እንደሚነገረው ‘አንድ ያልሆነ፣ አንድ አመራርና ቅንጅት የሌለው፣ ፡”በጥይት ቅንድብ የሚላጭ” ነገር ግን ብዙ የሚያስብና ሰው የሌለበት፣ ማኒፌስቶ ያልጻፈና ወዴት መድረስ እንዳለበት በቅጡ የማያውቅ ተደርጎ ሲሳል እናያለን። እነዚህ እውነት ናቸውን? ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ የፋኖ አንድነት ምከር ቤት የራሱን ድህረገጽና ዮቲዩብ አቋቁማል። ከባለቤቱና ከመስክ ላይ የተዘጋጀውን ጽሁፍ በትዕግስት ላነበበ እውነታውን ይረዳል፣ ጥያዌዎቹም ይመለሳሉ።
እውነት ለመናገር ከሆነ በየትኛውም መመዘኛ ከታየ ባለፏት 70 አመት ከተቋቋሙ “የነጻነት ታጋዮች” ነን ከሚሉ ቡድኖች በላይ ፋኖ አንድ የሆነና ምሉእ የሆነ ድርጅት ነው። ጀበሀ፣ ሻቢያ፣ ህወሀት፣ ኦነግን እንደ ምሳሌ ካየን አንድ ሺ ተዋጊ ላይ ለመድረስ ከስር አመታት በላይ ነበር የፈጀባቸው። ህወሀትም በሻቢያ ሜካናይዝድ ታግዞ አዲስ አበባ ሲገባ የነበረው ጦር 60ሺ ነበር።
ሁሉም ነፃ አውጭ ነን ባዮች፣ ሁሉም ከግባቸው ለመድረስ የተነሱት በባእዳን የፖለቲካ ዕሳቤ ላይ ተመሥርተውና በአገራቸው ውስጥ አንዱን “ጠላትና አንዱን ወዳጅ” በማድረግ፥ አንዱን ዝቅ ሌላውን ከፍ በማድረግ ነበር። እምነቶችን ሳይቀር አንዱን የጠላት ሌላውን የወዳጅ ብለው በመፈረጅ ነበር።
የፋኖ መከሰት እንደ ቀደሙት ንቅናቄዎች የውጭ ጠላት የመከረው፥ የባእዳን አስተሳሰብ አእምሮውን የተቆጣጠረው፥ ከሕዝብ እሤት፣ ታሪክ፣ የአስተዳደር፣ የፍትሕ ሥርዓት፥ ከሃይማኖትና ባህልን በመቃረን በጥቂት ልሂቃን ስብሰባ የተወለደ አይደለም። ተፈጥሮ የሚገኝ ራስን ከጥፋት የመከላከል፥ ከፍ ሲል ደግሞ ታሪክን፥ የሕዝብን ልዕልናን፥ የአገርን ሉዓላዊነት ከጎሣ ልሂቃን እብደት ለመከላከል ነው።
ይህን ተፈጥሮአዊ የህልውና መጠበቅ ማኅበራዊና አገራዊ ግዴታ ለመወጣት በየቦታው ቢያንስ ለ4 ዓመታት በህቡዕ ሲደራጁ፥ ሲማማሩ፥ ሲሰለጥኑ የቆዩ የማኅበረሰቡ ልጆች ናቸው። ወያኔና ብልጽግና በፈጠሩት ግብግብ ዳፋው ወደ አማራና አፋር ተሸጋግሮ ወደ እልቂትና ውድመት በማደጉ ከተደበቀበት ህቡዕነት ወጥቶ ራስን ለመከላከል ይፋ ሆኖ ወጣ።
ከጦርነቱ በመቀስቀሱና “ፎጣ ለባሹን እቀጣዋለሁ” ያለ ሀይል ወደ ክልሉ ስለገባ ፋኖ የአማራን ህዝብ ከመጥፋትና ሊጫንበት የታቀደው የባርነት ቀንበር ለመካላከል ህዝቡ በራሱ ከታች ወደላይ መደራጀት መሰልጠን ጀመረ። ከእነዚህ በቅድሚያ ከተሰባሰቡትና አዲስ እየተፈጠሩ ከመጡት መካከል በግልጽ አደረጃጀትና የየራሳቸው መሪዎች አበጅተው ከሚንቀሳቀሱት መካከል አብዛኛዎቹ መሪዎች የተወከሉበት “የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት” ተመሠረተ።
“በአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት” ስር የተሰባሰቡት ብርጌዶች በአንድ አመት ተኩል ውስጥ 55 ሺ ስራዊት ነው የገነቡት። መንግሥት በግልጽ በአማራ ሕዝብ ላይ ጦርነት አውጆ ሠራዊት በማዝመት፥ የግብርና ግብዓት በመንፈግ፥ ወደ አዲስ አበባ መግባትን በመከልከል፥ የህክምና መድኀኒቶችን በመንፈግና፣ ተረጅዎችን በማስራብ፥ የመገናኛ አውታሮችን በመቁረጥና በገዳማት ሳይቀር በመድፍ መደብደብ ጀመረ። ፋኖ በዛ ግዜ አማራጩ ስለጠበበ ወደ ጫካ ገብቶ አካባቢውን ተለማምዶ፣ ወታደራዊ አሰላለፉን አስተካክሎ እቅዱን ከሁሉም የፋኖ ብርጌዶች ጋር ምስጢራዊ ግንኝነት አድርጎ የመልሶ በማጥቃት በአንድ ሰአት በሁሉም ክፍለሀገራት በ54 ትላልቅና ትናንሽ ከተሞች ላይ ፈጸመ።
ደብረ ብርሀንን፣ ጎንደርን፣ ባህርዳርን በከፊል፣ ደብረ ማርቆስን እና በርካታ ከተሞችን ለስድስት ቀን ተቆጣጠረ። በመጀመሪያው የስድስት ቀናት ማጥቃትና 54 ከተሞችን ሲቆጣጠር የተሳተፈው የፋኖ አንድነት ምክር ቤት 55ሺ ተዋጊዎች ግማሹ ቢሆን ነው። በበጌምድር እና በተለያዩ ቦታዎች የነበሩት ብርጌዶች ሊነሱ የሚችሉ አደጋዎች ለመመከት በተጠንቀቅ እንዲቆዩ ተደረገ።
ይህ 55ሺ ሀይል ይባል እንጂ ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚገመተው የአማራ ባለ ጠመንጃ በብዙ ቦታ ተካፋይ ሆኖ ድሉን አፋጥኖታል።
ፋኖ ሁለት አመት ባነሰ ግዜ እንዴት ህወሀት በ17 አመት ሊገነባው ያልቻለውን ኃይል ማሰባሰብ፣ ማሰልጠን፣ ማቀናጀት ቻለ? እንዴትስ ባንክ መዝረፍ ቀርቶ አንድ ብር ወድቃ ቢያይ የማያነሳ ስነምግባር ያለው ኃይል ገነባ?
በተቃራኒው አገሪቷን ይወክላል የተባለው የአገር መከላከያ ሴት የሚደፍር፥ ገዳም የሚያወድም፥ ወንድ የሚሰልብ፥ ሱቅ የሚዘርፍ፥ አቢያተ እምነቶችንና ዩኒቨርስቲዎችን ምሽግ አድርጉ እንደ ላሊበላ ያሉ ቅርስ ላይ የሚተኩስ ሀይል ሆነ?
በሕዝብ ላይ ከሰማይ ቦምብ የሚያዘንብ ብልሹ ስነ ምግባር ከሚያሳይ ሠራዊት አንፃር ፍጹም ተቃራኒ በሆነ የመልካም ስነ ምግባር አርአያ የሆነ ንቅናቄ እንዴት ተፈጠረ? ብሎ መጠየቅ የፋኖን ጠንካራ መርህ፣ አፈጻፈም አቅምና በመልካም ሕዝባዊ ስነምግባር የታነፀ መሆኑን ሁሉም ተረድቷል።
እንዴት ፋኖ ያለበትን የትጥቅና የተተኳሽ እጥረት ለማቃለል በአንድ ሰአት በማጥቃት ከመንግስት መጋዘኖች በመቶ ሚሊዮን ብር የሚገመት ትጥቅ መቀማት ቻለ?
እንዴትስ 4 ሚሊዮን አባል አለኝ የሚለውን የብአዴንን መዋቅርን በስድስት ቀን ውስጥ ማፍረስ ቻለ ብሎ ለጠየቀ መልሱ ቀላል ነው?
የፋኖ ውጤታማነት ምሥጢሩ ፋኖ ከታች ወደላይ በፈቃደኞች የተገነባ በመሆኑ፤ በራሱ ጠመንጃ በየ ብርጌዱ ተዋቅሮ በነፃነት የሚንቀሳቀስ እና ልሂቃን ከባእዳን በተማሩት በፖሊት ቢሮ በሚሰጠው ትዕዛዝ ወይንም በካድሬ ጥርነፋ የሚታዘዝ የኮሚስቶችና የዘረኛ ብሔርተኞች አይነት ማሽን ባለመሆኑ ነው።
ፋኖ በራሱ የሚያስብ፣ በራሱ ትርፍና ኪሳራውን የሚገምት (risk/reward) በራሱ የሚወስን፥ በተፈጥሮ ሰብአዊ ክብር ላይ የቆመ፥ ለሕዝብ ታሪካዊና ባህላዊ እሤቶች ራሱን ያስገዛ፥ ከሕዝብ እምነቶችና ባህሎች የሚያከብር በመሆኑ ተቀባይነቱ ፈጣን ሆኗል።
ፋኖን በሰፊው ግዛትና ስርጭት ውስጥ የሚያስተሳስረውም ለአንድ ዐላማ፣ ለአንድ ግብ እና አንድ መአከል ያለው መሆኑ ነው። ይህ መአከል ደግሞ “የፋኖ አንድነት ምክር ቤት” ይባላል። የፋኖ አንድነት ምክር ቤት አንጋፋ፥ ከሁሉ አስቀድሞ የተደራጁትን በርእዮትና በመርህ፥ በዓላማ ግልጽነት አስተባብሮ በመያዙ ነው። በመዋቅር ሰንሰለት በዚህ ስብሰብ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ያልገቡ፥ የትግሉ ስፋትና ፍጥነት በየቦታው በየጊዜው የሚፈጠርይ የፋዎችን
በማሰባሰቡ ያለውን በማካፈሉና በመረዳዳቱ ነው። ለሀገሩ ለወገኑ ህይወቱን ሊሰጥ የመጣውን ወጣት ቅድመ ሁኔታ እያስቅውመጠ ይሄንን ካደረግክ እኔ በስምህ የለመንኩትን ብር እሰጥሀለሁ ስላላለ ነው። ያለውን ያካፍላል በአንድ ላይ ይታገላል በአንድ ጉድጓ ይቀበራል እንጂ ትልቅና ትንሽ ባለቤትና ጭሰኛ ስሜት አይፈጥርም።
የፋኖ አንድነት ምክር ቤት መቼ፣ እንዴት፣ በማን እንደተፈጠረ?
የፋኖን አመራርና መሪነት በሚመለከት በበርካታ ሚዲያዎች የምናየው ግራ መጋባት ፋኖ በኮሚኒስቶቹ አደረጃጀት ተጠርንፎ እንደ ኮ/ል መንግስቱ ወይንም እንደ አቶ መለስ ከፍ ብሎ የወጣ እና ሁሉን አውቃለሁ የሚል አንድ አንባገነን ከፊቱ ስላላቆመ ነው። ፋኖ በተቻለ መጠን በጋራ ስምምነትና በጋራ አመራር እና የምክክር ውሳኔ የሚከተል (collective leadership & consensus building) ነው።
ፋኖ የነ መለሰን የነ አብይን አንባገነንነት እያወገዘ በነሱ አምሳልና ተግባር “ቆራጡ” “ታላቁ” የሚባል ሰርአት ለመገንባት አይፈልግም። ፋኖ የአንድን አገር ዜጎች ከፋፍሎ ለአንዱ ልዩ መብት ለሌላው ደግሞ መብት አልባ፣ አንዱን እዳ ከፋይ ሌላውን አስከፋይ አድርጎ ደልድሎ የሚሰጥ ሳይሆን ዜጎች ሁሉ በሰብአዊ ክብራቸው፥ መብታቸው በየትኛው ማእዘን ሙሉና የማይሸራረፍ እኩል መብትና ነፃነት እንዳላቸው የሚያምን ነው። ሰው ሁሉ እኩል
አይደለም፣ አንዱ ልዩ ጥቅም ሌላው ደግሞ ልዮ ጥቃት ይገባዋል ብሎ ፈርጆ በሰራዊት ረግጬ እገዛለሁ ያለውን
ሥርዓትና ርዕዮት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከጫንቃው ለማስወገድ የተነሳ ኃይል ነው።
ስለዚህ ሚዲያውም ሆነ በዲያስፖራ ያላችሁ ወዳጆች አንድ መሪ እና ለመሪው ታዛዥ የሆነ ድርጅት አትናፍቁ። አብይ አህመድ ሲመጣ የጨፈረው እና ለብርሀኑ ነጋ በአዲስ አበባ ስታዲዮም የጮሁ ሰዎች ዛሬ ቪዲዮውን መልሰው ለማየት ይሸማቀቃሉ። ኢትዮጵያ የሆያ ሆዮና የመንጋ ፓለቲካ ሳይሆን በስሌትና በቀመር የሚመራ ትግል ነው የሚያስፈልጋት። ስለዚህ ከስህተታችን እንማር። በዚህ መንገድ ይሄንን ስርአት እንደምናስወግደው ጥርጥር የለንም።
ሌላው ሁሉም ሊረዳው የሚገባው ፋኖ ነጻ አውጪ አይደለም፤ ማንንም ነጻ ማውጣትም አይፈልግም። ፋኖ ተግባር ሁሉም እራሱን ነጻ እንዲያወጣ የሚችልበትን መደላድል መፍጠር ነው።
ፋኖ እራሳቸውን ነጻ ያወጡ ሰዎች ናቸው ነጻ ሀገር መፍጠር የሚችሉት ብሎ ያምናል። ኢትዮጵያም ነጻ ሀገር ሆና በነጻነት የኖረችው ነጻ ዜጎች ስለመሰረቷት ነው። ኢትዮጵያ በዘመናዊ ሰራዊት ሳይሆን አራሽ፣ ተኳሽ፣ ቀዳሽ ነጻ ህዝብ ስለነበራት ነው በነጻነት የኖረችው። ነጻ ህዝብ ሌላውን የሚጠብቅ ሳይሆን በራሱ ትጥቅ ስንቅ በራሱ እቅድ ህይወቱን የሚሰጥ ህዝብ ማለት ነው
ፋኖ በመደብ፣ በብሄር፣ በቋንቋ፣ በሀይማኖት ማንንም ወገን ባሪያና ጌታ አድርጎ አልፈረጀም። ፋኖ የሕዝብን ህልውና፥ የአገርን መቀጠል አምጦ የወለደው ጤናማ ሰብእና ያለው ኃይል ነው። ራስን በስሑት ርእዮት፥ በሐሰተኛ ትርክት ተነድተው፥ የግል የሥልጣን ጥማቸውን ለማርካት ከባእዳን ጋር በመተባበር
ሰብእናቸውን ሸጠው፥ በሕዝብ ግብርና በሕዝብ ሀብት የገዛ ወገኖቻቸውን ከፋፍለው ከሚያጠፋፉ የማፍያ ልሂቃን ሥእረዓት ለመስወገድ የሚደረግ ተጋድሎ ነው።
ፋኖ እያንዳንዱ ዜጋ እራሱን ከዘረኛ የጎሣ ልሂቃን ከፈጠሩት የጭቆና ሥርዓት ቀንበር ሥር እንዲያወጣ የሚያደላድል ኃይል ነው። ነጻ አውጪዎች የሚሰጡና የሚነሱ ሲሆን የተደራጀና በራሱ የሚተማመን ዜጋ ደግሞ መብቱን ከመስጠት ሞቱን ይመርጣል። ይህ የፋኖ መዐበል የተነሳው ግለሰቦች ይህ ገብቷቸው ለመብታቸው ህይወታቸውን ለመስጠት ስለተዘጋጁ ነው።
ራሱን ነፃ ለማውጣት የተነሳና የተዘጋጀን ሕዝብ ከሩቅና ከዳር ቆሞ መሪና አመራር ልስጥህ ማለት የፋኖን አላማ አለመረዳት ነው።
ሌላው እንዴት ፋኖ በስድስቱ ቀን ማጥቃት በርካታ እስር ቤቶችን ደርምሶ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ፓለቲከኞችን ከሚማቅቁበት እሥር ቤቶች ማስፈታት ቻለ ብለን ከጠየቅን የፋኖን ውጤቶች ያለ መሪ፣ ያለ ቅንብር፣ ያለ ትብብር እንዳልመጣ መገንዘብ እንችላለን። ይህም የሆነበት ምክያት በማርክሲስቱ አደረጃጃር አምስት ወይንም ሰባት መሪዎች የፈጠሩት ሳይሆን ከታች ወደላይ መሪ እየፈጠረ እያሳደገ በመምጣት ላይ ያለ ድርጅት ነው።
መሪዎቹ ፎቶአቸው ካልተለጠፈ፥ እኛ ካላውቀነው፥ በሚዲያ ቀርቦ ወይንም ቀርባ ካልተናገረች የለም ብሎ ማሰብ ስህተት ነው። ድርጅቱም በተግባር የተፈተኑ መሪዎች ከመፍጠር ይልቅ ተሽቀዳድሞ ድርጅቱን በገንዘብ ለመግዛት ወይንም በሚዲያ በሚገነባ የሀሰት ምንነት ድርጅቱን ለመቆጣጠር መሞከር ድርጅቱን ያዳክማል እንጂ ውጤታማ አያደርገውም። አሁን በሻለቃ ዳዊት ገድለጊዮርጊስ እየተሞከረ ያለው አካሄድ ድርጅቱን ይጎዳልና ይመከሩ የምንለው ለዚህ ነው።
ፋኖ ከተማሪ እስከ ፕሮፌሰር፣ ከአራሽ ገበሬ እስከ ሀኪም፣ ከተራ ጀሌ እስከ የወታደራዊ ጠበብትና ኮለኔሎች፣ ከዘመናዊ ትምህርት ምሁራን እስከ ጥልቅ የሀይማኖታዊ እውቀት ያላቸው ሰዎች ስብስብ ነው። ከዚው ውስጥ መሪ አይወጣም ማለት ለህዝብም ለታጋዮቹም ንቀት ያስመስለዋል።
የፋኖ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ በሚዲያ የሚነበብ ሳይሆን ሰውን ያከበሩ፥ ለኅሊናቸው የታመኑ፥ ፈርሀ እግዚአብሔርን ያላቸው፥ የአገራቸውን ረዥም ታሪክ በደማቸው ለማስቀጠል የቆረጡ፥ ከአገር-በቀል እስከ ዘመናዊ አስተሳሰቦች መርምረውና የተረዱ እንዲሆኑ ይፈልጋል።
ከዛላ አንበሳ እስከ ቶጎ ጫሌ፥ ከአክሱም እሰከ ሞያሌ ከቤኒሻንጉል እሰከ ደዋሌ በተዘረጋው ብዝኃነት ያለው የአገራችን እውቀቶች፥ እሤቶችና ልዩ ልዩ ፍላጎቶች ታሳቢነት የተቀመረ ፍልስፍና ያለው ስብስብ ነው።
እንዲታወቅልን የምንፈልገው ፋኖ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሁሉ እንደተለመደው በጥቂት ምሁራን አእምሮ ስፋት ልክ በተሰፋ ጠባብ ማኒፌስቶ ውስጥ ማስገባት የሚያሻው ኮሚስታዊ ወይንም የሌላ ውጭ-ገብ ፖለቲካዊ ቀመር ባርያና አምላኪ አይደለም።
ፋኖ ልህቃን ለሚጽፉት ማኒፌስቶ ወይንም ሕገ መንግሥት ተብዬ የሕዝብ ማፈኛና ባርያ ሆኖ የሚገድልና የሚሞት ሰው የተሰበሰበት የአብዮተኞችና የነፃ አውጭዎች መንጋ አይደለም።
ፋኖ ከውልደቱ የተውሶ ፍልስፍና አንጠልጥሎ ጥራዝ ነጠቅ ሆኖ በመደብ ክፍፍል፣ በሀይማኖት፣ በጎሳ፣ በክፍለሀገር ወይንም በጎጥ፥ ወይንም ዘረኛ የጎሣ ፍልስፍና ህዝብን የሚያጋጭ አይደለም። የአማራን ገጽታና ባህርይ ይዞ የተወለደ፥ ሰፊውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነባር እሤቶች ምርኩዝ ያደረገ አገር በቀል
የህልውና ተከላካይ ኃይል ነው።
ኢትዮጵያ ያላት በጎ ነገር ሁሉ ፋኖ በውስጡ ይዞት ተገኝቷል። ፋኖ የሚበልጥ ወይንም የሚያንስ ብሔር፥ ልዩ ጥቅም የሚሰጠውና የሚከለከል፥ የሚሰደድና የሚያሳድድ፥ ካሣ የሚያስከፍልና የሚከፍል፥ የታሪክ ባለቤት የሆነና ታሪክ አልባ፥ መልካምና ክፉ፥ ጨቋኝና ተጨቋኝ ብሎ መድቦ የተነሳ አይደለም። ሕዝባቸውንን ለ50 ዓመታት ያለማቋረጥ የፈጁ፥ ያፋጁና አሁን እያጠፋፉ ከሚገኙት የነፃ አውጭዎችና የነፃ አውጭዎቹ ልጅ ከሆነው ብልጽግና መንግሥት ፈጽሞ የሚቃረን ነው።
ፋኖ በከተማም በገጠርም በመላው ኢትዮጵያ ያለ እና ስሩን እየሰደደ ያለ ድርጅት ነው። የኢትዮጵያን ባንዲራ አስቀድሞ የሚታገልው ለሁሉም የተሻለ አለም ለመፍጠር ነው። ፋኖ የሚታገለው ስለራሱ መብትና ነጻነት እንጂ በጠላትነት ፈርጆ የሚደመሰሰው መደብ፣ ብሄር፤ ሀይማኖት፥ ባህልና ማኅበረሰብእ የለዉም። የፋኖ ተግባርና ዓላማ በሚከተለው መዝሙር ግልጽ ሆኖ ተቀምጧል።
“ኢትዮጵያዊነት ውድ መልኬ ነጋ ጠባ አትነካኩት
አላወልቅም ባንዲራዬን ልቤ ላይ ነው የለበስኩት
ከልቤ ላይ አላጠፋም የአበሻነት ታሪክ ውርሴን
እሰዋለሁ ለአንዲት ሀገር አንድ ነፍሴን
ፋኖ ለነጻነት
ፋኖ ለአንድነት
ይዘምታል ምን ግዜም ለኢትዮጵያዊነት
ሜዳ ገደል ፀሀይ ብርዱን አልፈዋለሁ ሁሉን ችዬ
ለሕጻነናት ላአዛውንቱ ለሰው ክብር ብቻ ብዬ
ለነጻነት ብዬ
ያባቶቼን ፈለግ ስለምደጋግም
የበላይን ታሪክ ከታች አላደርግም
የፋኖነት ገድል የፋኖነት ክብሬ
ብሞትም ላንድ ሀገር ብኖርም ላገሬ
አቤት ብዬ ተጠርቼ ተሰልፌ በፋኖ ስም
የተሰው ጋደኞችን የደም ዋጋ አላረክስም
የደም ዋጋ አላረክስም
ፋኖ ለነጻነት
ፋኖ ለአንድነት
ይዘምታል ምን ግዜም ለኢትዮጵያዊነት”
አላማውም አማራውን ከእልቂት ኢትዮጵያን ሕዝብ ደግሞ ከጭፍን የጥጋበኞችና ባለጊዜዎች መዳፍ ስር በማላቀቅ ሁሉም የሀገሩና የሰብአዊና ዜግነት ሙሉ መብቱን እንደያስመልስ፥ በአገሩ ጉዳይ ሁሉ ሙሉ ባለቤት እንዲሆን አርአያ ሆኖ ማሳየት ነው። አማራ ፋኖ “ሰው ሰው” የሚሸት ተፈጥሮን በትርክትና በጠባብ ልሂቃን ትርጓሜ የማይቀይር የሙሉ ሰብእና መገለጫነቱን በተግባር እየገለጸ የሚገኝ ስለሆነ አማራን በመጥላት የኖሩ ፖለቲከኞች ሳይቀሩ ስለ ፋኖ ክፉ መናገር አልተቻላቸውም።
በዘረኝነት፥ በሐሰተኛ ትርክት፥ በተውሶ ውጭ-ገብና ኢሰብአዊ ነፅሮተ ዓለም ተመርተው አገራቸውን ለ50 ዓመታት ያደሙና በመንግሥትነት ደረጃ ነውረኝነትን ሕጋዊ ያደረገው ነው ፋኖ የሚታገለው። ሕዝብ በመፍጀት፥ ዜጎችን ከፋፍሎና አንዱን የበላይ ባለ መብትና ባለአገር፥ ሌሎቹን ደግሞ መጤ የሚያደርግ ስርአትን ለመዋጋት ነው። ሴት የሚደፍር፥ የሃይማኖት ቦታዎችን የሚያወድም፥ ገበሬዎችን አንዳያመርቱ ግበአት የሚነፍግ፥ በሐሰተኝነትና በሤራ ተወልዶ በሤራ አገር ለመምራት ደፋ ቀና የሚለው ለማስወገድ ነው።
የፋኖ አንድነት ምክር ቤት ውጪ ግንኙነት ስህተት
በእርግጥ የፋኖ አንድነት ምክር ቤት በውጪ ያሉ ወንድሞች ድጋፍ በማሰባሰብና መንግስታቱን የማግባባቱን ስራ በተሻለ ይሰሩታል በማለት ለጽሁፍ ትኩረት አልሰጠነውም። የኛው ናቸው የምንላቸው የጎደለውን አሟልተው የተጣመመውን አቃንተው መልዕክታችንን ያደርሱልናል በማለት ችላ ብለነው ነበር።
ይሁንና ይረዱናል ብለን የጠበቅናቸው ወገኖቻችን ፋኖ “አንድ አይደለም፣ አይግባባም፣ ዓላማና ግብ የለውም፣ ማኒፌስቶም አልጻፈም” ወደሚል ትርክት ሄዱ። ይህ ደግሞ እኛ እናደራጀዋለን፣ እኛው እንምራችሁ ወደሚል እያደገ ሲመጣ የፋኖ አንድነት ምክር ቤት የራሱን ትርክት እራሱ መጻፍ እንዳለበት ተረዳ።
አሁን የፋኖ አንድነት ምክርቤት የራሱ ድህረገጽ የራሱ ዮትዩብ የራሱ ርዕሰ አንቀጽ ትንተና በፋኖ ድምጽ ተብሎ የተሰየመ አምድ ይኖረዋል። ለመረጃ ያህል ለወደፊት በአደረጃጀት ላይ የሚገኘው ገጹ ይከታተሉ።
ይህ ከመሆኑ በፊት ግን ፋኖ ምክር ቤት ማን ነው? የት ተመሰረተ? ምን ተስፋና አዳጋ ይታየዋል? የሚለውን በዝርዝር እንደሚከተለው ከክፍል ሁለት ጀምሮ በተከታታይ ይቀርባል። ተከታተሉን።
ክብር ለወንድሞቻችንና እህቶቻችን
በቅድሚያ መጨቆን መታረድ መገደል ሰለቸኝ ብለው ትጥቅ ላነሱ በትግሉ ውስጥም ለተሰዉ፣ አካላቸው ለጎደለ፣ በእስር
ለሚማቅቁ አባሎቻችን ያለን ክብር ከፍ ያለ ነው። እነሱ የሞቱለትን የደሙለትን በእስር የተንገላቱበትን ዓላማ ከግብ
ሳናደርስ እንዳማንቆም በድጋሜ ቃል እንገነባለን። በአማራ ሕዝብ ላይ የተደቀነውን የመጥፋት አደጋ አስወግደን ሁሉም
ኢትዮጵያዊ በሰላም ወጥቶ የሚገባባት፣ በህግ ፊት በእኩል የሚታይባት፣ በፈለገው ቦታ ተንቀሳቅሶ፣ ሰርቶ፣ ከብሮ
የሚኖርባትን ኢትዮጵያን ሳንፈጥር አንቆምም፣ አናንቀላፋም አናርፍም።
source: fanolisan.org