Breaking News
Home / Amharic / የፋኖ አንድነት፣ የእስክንድር ነጋና ዘመነ ካሴ ጉዳይ #ግርማካሳ

የፋኖ አንድነት፣ የእስክንድር ነጋና ዘመነ ካሴ ጉዳይ #ግርማካሳ

 “የፋኖዎች አንድነት ምን ላይ ደረሰ?” የሚል አስተያየቶች እየተሰሙ ነው፡፡ ፋኖዎች ከአንድ አመት በፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ በየአካባቢ ያሉ አደረጃጀቶች ነበሩ:: በየአካባቢ ያሉ ፋኖዎች በጋንታ እየተደራጁ፣ ከጋንታ ወደ ሻለቃ፣ ከሻለቃ ወደ ብርጌድ፣ ከብርጌድ ወደ ክፍለ ጦር፣ ከከፍለ ጦር ወደ እዞች ተሸጋግረዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በጎጃም ፣ በሻለቃ ሃብቴና በሻለቃ ባዬ የሚመሩ ሁለት እዞች፣ በጎጃም በዘመነ ካሴ የሚመራ አንድ እዝ: በሸዋ በአቶ አሰግድና በሻለቃ መከታው ማሞ የሚመሩ ሁለት እዞች፣ በወሎ በምሬ ወዳጆ የሚመራ አንድ እዝ አሉ፡፡ ሲደመሩ ስድስት እዞች ማለት ነው፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ እዚህ ደረጃ መድረስ ተዓምራዊ ድል ነው፡፡

በተጨማሪ በእስክንድር ነጋ የሚመራው የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት የሚባለው አለ፡፡ ይህ ሰራዊት ምን ያህል ሰራዊት እንዳለው ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ከሌሎች እዞች በገንዘብ ኃይል ፋኖዎችን የመነጠል ስራ እየሰራ ያለ ነው በሚል ቅሬታዎች ይሰሙበታል::

ሆኖም ክፍተቶች ላለመፍጠር፣ የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት ፣ ብዙ ኃይል ይኑረውም አይኑረውም፣ እንደ አንድ “እዝ” ተቆጥሮ፣ የፋኖ እዝ መሪዎች በሚያደርጉት ምክክር ላይ ፣ የህዝባዊ ሰራዊት መሪ እስክንድር ነጋ፣ እንዲገባ ተድርጎ በመወያየት ላይ ናቸው፡፡

የእዝ መሪዎች መነጋገር መቻላቸው፡ በራሱ ትልቅ ነገር ነው፡፡

ባለኝ መረጃ ወታደራዊ አመራርን በተመለከተ ብዙ አከራካሪ ነገር ያለ አይመስልም፡፡ ኮሎኔል ፋንታሁን ሙኸባ ላይ ሁሉም ማለት ይቻላል አዎንታዊ አመለካከት ነው ያላቸው አሁን ደግሞ እነ ጀነራል ተፈራ ማሞም ስለመጡ፣ ወታደራዊ ክንፍ የበለጠ መልክ መልክ እየያዘ ነው፡፡ ትልቁ ነገር ደግሞ በአሁኑ ወቅት ይህ ነው፡፡

ትንሽ ቻሌንጅ የሆነው የፖለቲካ አመራሩ ላይ ነው፡፡ በአንድ በኩል እስክንድር ነጋ አለ፣ በሌላ በኩል ዘመነ ካሴ አለ፡፡ በሁለቱ መካከል ያለው ነገር፣ ችግር ፈጥሯል፡፡ ሁለቱም በራስችው መንገድ ድክመትም ጥንካሬም አላቸው፡፡ ሆኖም በሁለቱ ምክንያት ነገሮች መጓተት የለባቸውም፡፡

በኔ እምነት የፋኖ የፖለቲካ አመራር በኮሚቴ የሚመራ አመራር ቢሆን ጥሩ ነው፡፡ እስክንድር ነጋ መሪ ሆኖ ቢመረጥ፣ ራሱን የቻለ ችግር ይፈጥራል፡፡ ዘመነ ካሴን እንደዚሁ፡፡

ስለዚህ እስክንድር ነጋም፣ ዘመነ ካሴም ያሉበት ኮሚቴ ተቋቁሞ፣ የኮሚቴው አባላት በዙር ኮሚቴውንም እንዲሰበሰቡ ማድረግ ይቻላል:: ኮሚቴው በአብላጫ ድምጽ የወሰነው ተግብራዊ እንዲሆን በማድረግ፡፡

እስክንደር ነጋ ከመሪዎች መካከል አንዱ እንጂ፣ መሪው ከሆነ ግን ትልቅ ችግር ይፍጥራል፡፡ እስክንድር ላይ ችግር ያለባቸው በተቃውሞ ይነሳሉ፡፡ መከፋፈልም ይፈጥራል፡፡ እስክንድር ከአንድ አመት በፊት የነበረው ፖለቲካዊ ቁመና አይደለም አሁን ያለው፡፡ ያ በግልጽ ሊታወቅ ይገባል፡፡

ዘመነ ካሴም ጋር እንደዚሁ ተመ ሳሳይ ነገር ነው ያለው፤፡ ድጋፊዎች ብዙ እንዳሉትም፣ ተቃዋሚዎች የዚያኑ ያህል ነፍ ናቸው፡፡

ስለዚህ ዘመነም፣ እስክንድርም ከሌሎች ጋር ሆነው፣እንደ ኪሚቴ እኩል ድምጽ ኖሯቸው፣ ተከባብረው እንዲመሩ ካልተደረገ፣ አንዱ የበላይ፣ ሌላው የበታች ሆኖ እንዲቀጥሉ መደረጉ ጉዳት ያመጣል፡፡

አይ የግድ አንድ ሊቀመንበር መኖር አለበት ከተባለ ደግሞ፣ ውዝግብ የማያስነሱ፣ ከእስክንደር ነጋና ከዘመነ ካሴ ውጭ ሌሎች እጩዎችን ማቅረብ አስፈላጊ ነው፡፡ መቼም ከነዚህ ሁለት ሰዎች ውጭ ሌላ ሰው የለም እንደማልባል ነው፡፡ ይቅርታ ይደረግልኝና፣ ከእስክንድር ነጋም ፣ ከዘመነ ካሴ የተሻሉ ሊሆኑ የሚችሉ አገር ቤት ፋኖዎች መካከል ይኖራሉ ባይ ነኝ፡፡ ኧረ እንደውም አሉ፡፡ እኔ እራሴ የማውቃቸው፡፡

እስክንደር ካልተመረጠ፣ ዘመነ ካልተመረጠ በሚል የህዝብ ትግልክ ወደ ኋላ መቀልበስ የለበትም፡፡ ጉዳዩ የዘመነ ወይንም የ እስክንድር ጉዳይ ሳይሆን ጉዳዩ የህዝብ ጊዳይ ነው፡፡

 

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.