ወያኔ ከትግራይ ስትወጣ መጀመሪያ የያዘችው ኮረምን ነው። ኮረም የተያዘው መከላከያና የአማራ ልዩ ኃይል በአሻጥር እንዲለቅ ከተደረገ በኋላ ነበር። ኮረም ብላ፣ አላማጣ፣ ዋጃ፣ ቆቦ፣ ሮቢት፣ ጎብዬ፣ መርሳ፣ ሁርጌሳ፣ ዉጫሌ፣ ሃይቅ፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ እያለች ባቲ ደርሳለች።
ወያኔ ባቲ ለመድረስ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ የትግራይ ወጣቶች ሕይወት ገብራለች። በጣም ብዙ። ታጣቂዎችን እንደ ማዕበል እያስመጣች። የምታስመጣውም በኮረም፣ በወልዲያ ፣ ቆባ እያደረገች ነው። ረጅም ርቀት ነው ታጣቂዎቿን የምታመላልሰው።
መኪናዎች ታጣቂ ለማመላለስ ከሰሜን ወደ ደቡብ ታጣቂ ይዘው ቢሄዱም፣ ከደቡብ ወደ ሰሜን አቅጣጫ ደግሞ ከአማራ ክልል የዘረፉትን ይዘው ወደ ትግራይ ይሄዳሉ።
የወገን ጦር ከኮረም አጭር ረቀት ላይ በሰቆጣ፣ ከወልዲያ አጭር ረቀት ላይ በጋሸና ደጃፍና በጭፍራ ይገኛል። ሌሎች መስመሮች አሉ። ግን ሶስቱ ላይ ብቻ ስናተኮር ርቀታቸው በመኪና ከአንድ እስከ ሁለት ሰዓት ገደማ ብቻ መሆኑን እናያለን።
የአየር ኃይል ድጋፍ ተጨመሮበት ከጋሸናና ከጭፍራ ወደ ወልዲያ፣ ከሰቆጣ ወደ ኮረም የማጥቃት ዘመቻዎች ቢጀመሩ፣ አሁን ያለውን ሁኔታ ከስር መሰረቱ ነው የሚያናጋው። የወያኔም የመጨረሻ መጀመሪያ ነው የሚሆነው። ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ባቲ ፣ ኩታበር ወዘተ የተበተኑ የትግራይ ታጣቂዎች እጅ ከመስጠት ወይንም ከማለቅ ውጭ ሌላ አማራጭ አይኖራቸውም።
የደሴው ጉዳይ የአንዳንዶቻችንን ስሜት በመጉዳት ተስፋ ሊያስቆርጠን ቢችልም በጥቅሎ ስትራቴጂካዊ በሆነ መልኩ በስናየው ግን ሚዛኑ በእጅጉ ወደ ወገን ጦር ያዘነበለ ነው።
ይሄ እንግዲህ በወሎ ያለውን በተመለከተ ነው። ሌሎች ግንባሮችም እንዳሉ አንርሳ። በጠለምት መስመር ከፍተኛ የወገን ጦር ዝግጅት አለ። ጠለምትን ማስለቀቅ ብቻ ሳይሆን ሽሬ በመግባት ሙሉ ለሙሉ በዚያ የወያኔን መረብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመበጣጠስ የሚችል ኃይል።
ፈረንጆች፣ ” the big elephant in the room” ይላሉ። ሌላው የኤርትራ መንግስት ጉዳይ ነው። በአድዋ በስተሰሜን በኩል ራማ በምትባል ቦታ ዉጊያ ተደርጎ ነበር። ከዚህም የተነሳ ወያኔዎች በርካታ ጦራቸውን ወደ ሽራሮ/ባድመ መስመር፣ አድዋ/ራማ መስመር፣ አዲግራት/ዛላንበሳ መስመርና ጾሮና መስመር ለማሰማራት እየተገደዱ ነው። በደቡብ ወሎ ያሰማሩት፣ በጦርነቱም ያለቃባቸው ሰራዊት ተቀንሶ፣ ወደ ኤርትራ ድንበር ሲያሰማሩ፣ የሰው ኃይል አድቫንቲጃቸው እየቀነሰ ነው የመጣው።ጦራቸው በተከያየ አቅጣጫ እየተበታተነና እየሳሳ ነው የመጣው።
ሌላው በጣም ሊሰመርበት የሚገባ ትልቅ ጉዳይ አለ። ወያኔን ለመዋጋት ያለው ህዝባዊ መነቃነቅ ታይቶ የማይታወቅ ነው። ቢያንስ ያልተነካ ከ500 ሺህ እስከ ሚሊዮን የሚሆን መደበኛ ሰራዊትና ሕዝባዊ ሰራዊት አባላት አሉ። በትግራይ እንዳለው ተገደው የመጡ ሳይሆን በፍቃደኝነት በሰልፍ የመጡ። በወያኔ ላይ እጅግ በጣም ያመረሩ።
እነዚህ ወገኖች፣ ብዙዎች በፋኖና በሚሊሺያ አደረጃጀት ስር እየተንቀሳቀሱ ያሉ ናቸው። በቂ መሳሪያ አይሰጣቸውም ነበር። አሁን ግን መሳሪያ በደንብ የመታጠቅ እድላቸው በጣም የሰፋ ነው የሚሆነው። የአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ ክተትን ተከትሎ።