Breaking News
Home / Amharic / የጎንደር አማራ ፋኖ ያወጣው መግለጫ! ይድረስ ለመረጃ ቲቪ እና ለጎንደር አማራ ህዝብ ጠሎች ! Message from Gonder FANO to Mereja TV

የጎንደር አማራ ፋኖ ያወጣው መግለጫ! ይድረስ ለመረጃ ቲቪ እና ለጎንደር አማራ ህዝብ ጠሎች ! Message from Gonder FANO to Mereja TV

#የጎንደር አማራ ፋኖ ያወጣው መግለጫ ይድረስ ለመረጃ ቲቪ እና ለጎንደር አማራ ህዝብ ጠሎች !
ቀን፦ 21/ 08/ 2024 ዓ.ም

የሐሰት ትርክት ፈጥሮ መግደል፤ ፈርጆ ማሳደድን አንታገስም!

በአማራ ህዝብ እና የፋኖ አመራሮች ላይ የሚደረገውን የስም ማጥፋት ዘመቻ በተመለከተ ከሁሉቱም የጎንደር ፋኖ ዕዞች በጋራ የተሰጠ መግለጫ
የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ከጀመረበት ወሳኙ ወቅት ጀምሮ የውስጥ እና የውጭ ጠላቶቻችን በህልውና ትግላችን ላይ በሙሉ ልብ እና ኃይላችን እንዳናተኩር የተጠኑ፣ የተደራጁና በበጀት የተደገፉ ሴራዎች ሲሰሩብን ቆይተዋል፡፡
ለአብነት ያህል በአርበኝነትና በሰብዓዊ እሴቶቻችን የተሰጠንን ምስጉን ስማችን ለማጉደፍ፣ አማራዊ ሕብረታችን ለመበተን “ጃውሳ”የሚል የሐሰት ትርክት ፈጥረዋል፤ “ስኳድ”በሚሉት ከፋፋይ ትርክት ላይ የተመሰረተ የፈጠራ ሰነድ ተዘጋጅቶ ከውስጥ አማራነትን ለማፍረስ ተሲሮብናል፡፡ አማራዊ ኃይላችንን ተፈታትነዋል። የህልውና ትግሉን አጠናክረን ከቀጠልንበት ጊዜ ጀምሮ የአማራ ፋኖን ትግል ከሕዝብ ልብ ለመነጠል ዘራፊ እና ነብሰ ገዳይ ቡድን አሰማርተዋል፡፡ የስድስት ዓመት ወንድ ህፃን ልጅ ሳይቀር ደፍረዋል፣ አቅመ ደካሞችንና የቆሎ ተማሪዎችን ጭምር በጅምላ ረሽነዋል።
በአሁኑ ወቅትም መርዝ የሚተፉ ግለሰቦች በ”መረጃ ቲቪ” በኩል ከጠላት የተሰጠን አጀንዳ በመያዝ“ስኳድ”በሚል ፍረጃ አደገኛ ቅስቀሳ በዘመቻ መልኩ ቀጥለዋል፡፡ ይህ “ስኳድ” የሚባል የሐሰት ትርክት፣ መነሻ ፍላጎቱ የታላቁ ጎንደር አማራ ሕዝብን ውስጣዊ አንድነት ለመበተን፣ ታጋይ ልጆቹን ለማራከስ፣ የተማሩ ልጆቹን ለማሳደድ፣ ተተኪ ትውልዱን ለማኮላሸት፣ ጎንደርን እና የጎንደር አማራን ከትግል ሜዳው ለማጥፋት አልፎም አማራነትን ለመበተን በውስጥና በውጭ የአማራ ጠላቶች የተፈጠረ፣ አሁን ድረስ የቀጠለ “አጀንዳ” ነው፡፡
ይህን “ስኳድ” በሚል ፍረጃ በታላቁ የጎንደር አማራ ላይ የተጀመረው ዘመቻ፡- ቤንሻንጉል ጉምዝ ላይ “ቀይን እናጥፋ” የሚለው ዘመቻ፣ ኦሮሚያ ከልል ውስጥ“ነፍጠኛን እናጥፋ”፣“መጤን እናስወግድ”፣ ወይም ለዓመታት በራያ፣ ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የአማራ ርስቶች ላይ “ጨቋኙን አማራ እናጥፋ” በሚል ፍረጃና የሐሰት ትርክት አማራን በጅምላ ለማጥቃት ከተደጉ የአማራ ጠል ቡድኖች የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ ለይተን አናየውም።
በሳይበር ጠላቶቻችን በተደራጀና በበጀት በተደገፈ መልኩበሳተላይት ደረጃ በ”መረጃ ቲቪ”እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ”ስኳድ” የሚል የፍረጃ ስም ሰጥቶ የማሳደድ፣ የሐሰት ትርክት ሰርቶ የመግደል ተግባርን የህልውና ትግሉ አንድ አካል በማድረግ በነፍጥ ጭምር አምርረን የምንታገለው መሆኑን በልጆቹ ላይ ዘመቻ የተከፈተበት የጎንደር አማራ እና መላው አማራዊ ሕዝባችን እንዲያውቅልን እንፈልጋለን።
በህዝባችን፣ በፋኖ ታጋዮች እና አመራሮች ላይ የሚደረግን ማንኛውንም ዓይነት የሐሰት ትርክት እንደማንታገስ እያሳወቅን የሚከተሉትን ጥሪ፣ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያዎች እናስተላልፋለን፡-
1) “መረጃ ቲቪ” የርዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ ዋና አሳላጭ የነበረው ራዲዮ ኮሊንስ (RTLM) አቻ እየሆነ መምጣቱ፣ በተለይ በታላቁ የጎንደር አማራ ሕዝብ ላይ አማራ – ጠል ቡድኖች በሄዱበት መንገድ የሐሰት ትርክት ማኒፌስቶ ማስታወቂያ ሆኖ ተገኝቷል፡ ፡ በዚህ አንድ ከሆነው አማራነት ነጥሎ፣ ህዝቡን በተወለደበት ግዛት ለይቶ ለዘር ማጥፋት ወንጀል እያዘጋጀ በመሆኑ እየተፈጠሩ ላሉ ፀረ -ጎንደር አስተሳሰቦች እና ድርጊቶች ኃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን እያሳወቅን፤ ጣቢያው እስካሁን ላስተላለፋቸው ፀረ – ጎንደር፣ ፀረ – አማራ አንድነት ዘገባዎች ይቅርታ እንዲጠይቅ እና ይህ ዘገባ እንዲሰራ ዋና አስተባባሪ በሆነው አቶ ኤልያስ ክፍሌ ላይ የእገዳ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን። በተጨማሪም በ”መረጃ ቲቪ” (የአማርኛው የሩዋንዳ RTLM ግልባጭ) አማካኝነት ከላይ የተጠቀሱትን ዓይነት ይዘት ያላቸውን ምስልና መልዕክቶች ከዩትዩብ፣ ቴሌግራም፣ ረምብል እና ሌሎች የማኀበራዊ ሚዲያ መተግበሪያ ገጾቹ ላይ በአስቸኳይ እንዲወርዱ እንጠይቃለን። ይህ ሳይሆን ቢቀር ጣቢያው በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን
የዘር ማጥፋት ወንጀል በሌላ መልክ ለማስቀጠል እየሰራ በመሆኑ የተከበራችሁ የጣቢያው መስራችና ባለቤቶች አቶ ሰለሞን እና ወ/ሮ መሰረትን ጨምሮ በአማራ ህዝብ ላይ ለሚደርሰው የዘር ማጥፋት እልቂት ተጠያቂ የምናደርግ መሆኑን በቅድሚያ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
2) ከህልውና ትግሉ በተቃራኒ የቆሙ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችን እንዲሁም ተቋማትን ማበረታት እና አብሮ መስራት የአማራ ሕዝብ ትግልን መግደል እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም አርበኛ ዘመነ ካሴ በታላቁ የጎንደር አማራ ሕዝባችን ላይ የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ የሚያስተላልፈውን እና የህልውና ትግላችንን ጭቃ እየቀባ ያለውን “መረጃ ቲቪ” (RTLM) አመስግኖ ”እርዱት” የሚል ጥሪ በመግለጫ ማስተላለፉ፣ ከምን አንፃር እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጥ እንጠይቃለን። ይህ ካልሆነ አርበኛ ዘመነ ካሴ የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል እና የህልውና ታጋዮችን የሚመለከትበትን ሁኔታ ከ ”መረጃ ቲቪ” (RTLM) ቅስቀሳ አንፃር በጥርጣሬ እንድንመለከተው ያስገድደናል፡፡ ይህም አንድ አማራዊ ተቋም ለመገንባት በምናደርገው ያላሰለሰ ጥረት ላይ ትልቅ ደንቃራ መሆኑን ልናሰምርበት እንወዳለን፡፡
3) የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል በአንድ ግለሰብ ላይ የተንጠለጠለ ይመስል በ“መረጃ ቲቪ” (RTLM) ፊት አውራሪነት በአርበኛ እስክንድር ነጋ ላይ የሚደረገው ”የስብዕና ግድያ” ሙከራ ከአማራነት በታች የሆነ አሳፋሪ ተግባር ነው። አርበኛው ገና በለጋ ዕድሜው ጀምሮ በአማራነት የቆመ፣ የአማራ ትግል መሠረት በሆነውና በአባታችን ፕሮፌሰር አስራት ይመበራ በነበረው “መዐሕድ” ውስጥ የታገለ፣ በመረጃና በዕውቀት ለአማራና ለኢትዮጵያ ሲታገል የኖረ፣ በእነዚህ አቋሞቹ ትልቅ ዋጋ የከፈለ፣ አሁንም አማራ ህዝብ የህልውና ትግል ውስጥ የሞቀ ህይወቱን ንቆ፣ ቤተሰቦቹን በትኖ በረሀ ወርዶ እየታገል ያለ የጽናት ምልክት ነው። በመሆኑም የአርበኛ እስክንድር ነጋን ስም በማንሳት እና ምስሉን በመለጠፍ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የህይወት መስዋዕነት እየተከፈለበት ባለው የፋኖ ትግል ላይ የምታላግጡና የመከፋፈል ስራ የምትሰሩ ጥቂት ሚዲያዎች፣ ጋዜጠኞችና አንቂዎች ከዚህ አስነዋሪ ድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን።
4) ግፍ እና ገፈኞችን በመቃወም እድሜውን ያሳለፈውን እና አሁንም የታሪክ ሰሪውን የወሎ ቤተ-አማራን ህዝብ ከጫፍ እስከ ጫፍ በማደራጀት፣ ለጠላት የከበደ ረቂቅ የሆነ አመራር እና ወታደራዊ ስልጠና በመስጠት ፀንቶ የቆመው፤ የህልውና አደጋውን ለመቀልበስ ግንባር ተሰልፎ የሚገኘውን የህዝብ ጋሻ የሆነው ወታደራዊ መኮንን ኮርኔል ፋንታሁን ሙሃባውን ስም ማጥፋት፣ የሚመራውን ግዙፍ ሰራዊት የማወክ ኋላቀር ተግባር ባስቸኳይ እንዲቆም እናሳስባለን፡፡ መላው የአማራ ህዝብም የመልካም ሰብዕና ባለቤት ከሆነው መሪያችንና ከሰራዊቱ ጎን እንዲቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

 

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.