Breaking News
Home / Amharic / የገዳ ባንክ ተመርቋል! የአማራ ባንክ ግን እስካሁን ታግዷል !

የገዳ ባንክ ተመርቋል! የአማራ ባንክ ግን እስካሁን ታግዷል !

• “አማራ ባንክ ህዝባችን እንዴት መደራጀት እንዳለበትና አንድነት እንዴት መፍጠር እንደሚቻል ያስተማረን ክስተት ነው”።
• ባንኩ ከ188 ሽህ በላይ ባለድርሻዎች እንዳሉት የተገለጸ ሲሆን 7.9 ቢሊዮን ብር የተመዘገበ 6 ቢሊዮን ብር ደግሞ የተከፈለ ካፒታል በመያዝ ስራ ለመጀመር ተዘጋጅቷል።
• የባንኩ ባለድርሻዎቹ 50 በመቶ ከአዲስ አበባ፣ 30 በመቶ ከሌሎች ክልሎችና 20 በመቶ ከአማራ ክልል የመጡ የመሆኑ ሲታይ ባንኩ የመላው ኢትዮጵያውያን የፋይናንስ ተቋም መሆኑን ያመለክታል።
• “የአማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር የሀገራችን ግዙፍ ተቋም ነው፣ ዛሬ አክስዮን ማኅበሩ የተመሠረተበት ቀን ብቻ ሳይሆን ቅቡልነቱ የተረጋገጠበት ዕለት ነው”፡፡
• በምሥረታው “ከኔ ባሻገር የእኛ” የምንለው ሊኖረን እንደሚገባ ያረጋገጥንበት፣ የምንማርበት የፋይናንስ ኢንዱስትሪ አሻራ የጣልንበት ታሪካዊ የኢትዮጵያ ቀን በመሆኑ የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል የአማራ ባንክ ጉልህ ድርሻ የሚጫወትበት መንገድ ይፈጥራል፡፡
• “ዛሬ ለኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ የምሥራች ቀን ነው” ፡፡ የአማራ ባንክ፣ ሕዝብ እንዴት መደራጀት እንዳለበት ያስተማረን ክስተት ነው፡፡ አማራ ባንክ አንድነት እንዴት መተግበር እንዳለበትም አሳይቶናል፡፡ ባንኩን የመሠረተው ኢትዮጵያዊ ቤተሰብነትና መልካም ጉርብትና እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ የሕዝባችን ትሥሥርነትና ወንድማማችነት ውጤት ነው ያሉት፡፡
• ባንኩ በክልሉና በሀገሪቱ ለሚኖሩ የአማራ ሕዝቦች የኢኮኖሚ አቅም ሆኖ እንደሚታይ እምነታቸውንም ገልጸዋል፡፡
• የክልሉ መንግሥት ባንኩን ለማገዝና ሊያጋጥሙ የሚችሉትን ችግሮች ሁሉ በጋራ ለመፍታት በቁርጠኝነት ይሰራል፡፡
************አቶ አገኘው ተሻገር የአማራ ክልል ርዕሰ መስተደድር************
• “አማራ ባንክ መላው የሀገራችን ሕዝቦች ትስስር የፈጠሩበት ነው”
• አማራ ባንክ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል።
• ኢትዮጵያዊያን ብሔር ሃይማኖትና ቋንቋ ሳያግዳቸው አማራ ባንክ የሁላችንም ነው ብለው በአንድነት የመሰረቱት ባንክ ነው፡፡
• የባንኩ መሥረታ መቀራረብን እና መሰባሰብን ያሳየ ነው፡፡
• አማራ ባንክ በፋይናንስ ዘርፍ ከፍ ብሎ ለመብረር የሚችልበት ሕዝባዊ መሰረት ያለው ለኢትዮጵያ አዳዲስ አሠራሮችን በማስተዋወቅ ዘርፉን ከፍ ያደርጋል፡፡
• በምሥራቅ አፍሪካ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ጎልቶ ለመውጣት የተሰበሰበው ገንዘብ አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡
• “አማራ ባንክ መላው የሀገራችን ሕዝቦች ትስስር የፈጠሩበት ነው”
**********በምክትል ከንቲባ ደረጃ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማኅበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ጃንጥራር ዓባይ **********
• ‹‹አማራ ባንክ ከተባበርንና ለአንድ ዓላማ ከቆምን ሁሉን ነገር ማሳካት እንደምንችል ማሳያ ነው››
• በተለይም 188 ሺህ በሁሉም አካባቢዎች የአክሲዮን እጣ መሸጥ ቀላል አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እያደገና እየተቀየረ መምጣቱን ያመላክታል፡፡
• ከአማራ ባንክ ምሥረታ ማየት እንደሚቻለው በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢና በምሥራቅ አፍሪካ የማደግ ዕድል እንዳለን ማሳያ ነው ፡፡
• በቀጣይ በኢትዮጵያ የውጭ ባንኮችም ስለሚገቡ ባንኩ ተወዳዳሪ ለመሆን ጠንክሮ ሊሠራ ይገባል።
**********የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ዘመዴነህ ንጋቱ**********
• “ባንኩ ባለ ጸጋዎችን ብቻ ለማገልገል ሳይሆን ደሀዎችን ባለጸጋ ለማድርግ አስቦ የተነሳ ነው”
• አማራ ባንክን የማቋቋም ሃሳብ የብዙዎችን ልቦና ያስተሳሰረና ያዘመደ ነው፡፡
• የአክሲዮን ማኅበሩ ወደ ሥራ መግባት በበርካቶች ልቦና የነበረውን የመልማት ፍላጎትና የተቋም ግንባታ ውጥን እውን እንዲሆን ያስቻለ ወርቃማ እንቅስቃሴ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡
• ‹‹ባንኩን የማቋቋም ሀሳብም ድንገት የመጣና ቅፅበታዊ ድርጊት አይደለም›› ያሉት አቶ መላኩ ለኅብረተሰብ ለውጥ ሲታሰቡ ከነበሩ በርካታ የምጣኔ ሀብት ጉዳዮች ቀዳሚ ሀሳብ ነው፡፡
• የአክሲዮን አባላቱ ከቅድመ መስረታው ጀምሮ እስከ ስም አወጣጥ የተሳተፉበት፤ ሀሳባቸውን ያስተሳሰሩበት ድንቅ የአዕምሮ ውጤት ነው፡፡ ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎችና አካባቢዎች አማራ ባንክ የእኔ ነው በማለት አክሲዮን በመግዛት፣ በሃሳብ በመደገፍና ባንኩን በመቀላቀል የአማራ ባንክ እንደ አማርኛ ቋንቋ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መተሳሰሪያ፣ መግባቢያና መገናኛ መድርክ እንዲሆን ለአደረጉት አባላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
• የአማራ ባንክ የመጀመሪያ የአክሲዮን ምሥረታም በኢትዮጵያ በየትኛውም የንግድ መሥረታ ታሪክ ክብረ ወሰን በሰበረ አክሲዮኖች ቁጥርና በከፍተኛ ካፒታል ገበያውን እዲቀላቀል ተደርጓል፡፡
• የአማራ ባንክ (አባ) የተበለውም ኀላፊነት የሚሰማው ሁሉንም ልጆች በእኩልነት የሚያይ፣ የሚጠብቅ፣ የሚንከባከብ፣ የሚያሳድግና የሚያበቃ በመሆኑ ነው፡፡
• ‹‹የብዙዎችን ድንቅ አዕምሮ ያስተሳሰረ፣ የኅብረተሰቡን ቀልብ የገዛ፣ የተቋም ግንባታ ተምሣሌት ነው፤ ዘመን ተሻጋሪና ዘመናዊ የፋይናንስ ተቋም ለመገንባት ቆርጦ የተነሳ ባንክ ነው›› ፡፡
• ባንኩ ለሀገራችን የአክሲዮን ሽያጭ ፈር የቀደደ፣ በዘርፉ ተወዳዳሪ፣ አዳዲስ ፈጣን ቴክኖሎጂዎችን የሚጠቀም፣ ብቃት ባለው የሰው ኀይል የሚደገፍ፣ ከሌሎች ባንኮች ጋር እስከ መዋሃድ ቁርጠኛ የሆነ፡ አማራ ባንክ ሀገርን በእኩልነት ለማገልገል በማሰብ የተቋቋመ ባንክ ነው።
******** አቶ መላኩ ፈንታ የአክሲዮን ማኅበሩ አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ********
የአማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር ከነሐሴ 11/2011 ዓ.ም እስከ ኅዳር 21/2013 ዓ.ም የአክስዮን እጣ ሲሸጥ ቆይቷል፡፡ በዚህም ስምንት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ካፒታል ቃል ተገብቷል፤ ሥድስት ቢሊዮን ብር ደግሞ ተሰብስቧል፡፡ የካፒታል አቅሙ 16 ባንኮችን መመሥረት ያስችላል፡፡
አክሲዮን ማኅበሩ 170 ሺህ የአክሲዮን ባለድርሻዎች አሉት፡፡ የአክሲዮን ግዢ ስርጭቱም 50 በመቶ በአዲስ አበባ፣ 20 በመቶ በአማራ ክልል እና 30 በመቶ በሌሎች ክልሎች ነው፡፡
የአማራ ባንክ አክስዮን ማኅበር በሂደቱ 188ሺህ የአክሲዮን እጣም መሸጥ ችሏል፡፡
አማራ ባንክን ከጥንስሱ እስከ ዛሬው ምስረታ እንዲበቃ ያደረጋችሁ የኢትዮጵያ ልጆች የዛሬው ቀን ለእናንት ዳግም ልደታችሁ ስለሆነ እንኳን ደስ አላችሁ!
አማራ ባንክ፤ የሁሉም ባንክ

 

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.