Breaking News
Home / Amharic / የደብረ ብርሃን ከንቲባ ፖለቲካ !

የደብረ ብርሃን ከንቲባ ፖለቲካ !

 
የቅርብ ጊዜ ትዝታዎችን እናስታውስ እስቲ ጊዜውን ባልጠበቀ ሁኔታ ተፈራ ወንድማገኝ ከዞኑ አስተዳዳሪነት እንዲነሳ ሲደረግ ይህ ገዳይ ትክክል አይደለም ተፈራን ከህዝብና ከፖለቲካ ለማራቅ ሆን ተብሎ የተደረገ ስራ ነው ብለን ፅፈፋን ነበር በወቅቱ ደብረብርሃን ላይ የነበረው የመንደር ስብስብ ይህን ጩኸታችንን እልሰማ ብሎ ያንን የመሰለ የመሪነት ብቻ ሳይሆን የሰውነት ግርማ የነበረውን ሰው አጣን። በዚህ ሂደት እና የክልሉ አመራር የነበረው ተመስገን ጡሩነህ የሰራው ስራ ቀላል አልነበረም።
እንደው ለማስታወስ ያህል እንደ ላቀ አያሌው ፣መላኩ አላበል፣ ዩሃንስ ቧያለው ሁሉ ከሸዋ ተፈራ ወንድማገኝ የሚባል ጠንካራ ሰው ወደፊት ለመምጣት ይችል ነበር ነገር ግን በትምህርት ሰበብ ከፖለቱካውም ክህዝቡም ፊት ገለል እንዲል ተደረገ። ደግነቱ ተፈራ ወንድማገኝ በሌብነትም ሆነ በባንዳነት አልተከሰሰም። ብቸኛ ችግሩ የነበረው ታማኝ አማራ መሆኑ እና የኦሮሙማን ፖለቱካ የሚመክት ሃሳብ ያለው መሪ መሆኑ ብቻ ነበር።
አሁንም በተመሳሳይ ሁኔታ ሸዋ መሪ እንዳይኖረው የተለመደው አይነት የተኮንል ስራ እየተሰራ ነው። ደስታ አንዳርጌን በተመለከተ የሚነሱ ተገቢም የሆኑ የአስተዳደር የአድሏዊነት ጥያቄዎች ይኖራሉ ነገር ግን በፍፁም ደስታ አንዳርጌ ከወያኔ ጋር ይሰራ ብሎ የሚያምን አንድም የሸዋ ሰው አይኖርም የለምም! ይህን 100% እርግጠኛ ሆነን መናገር የምችለው ጥሬ ሀቅ ነው።
ሸዋ ልብ በል ልጆችህን በውሸት ክስ የምታስበላበት ጊዜ መቆም አለበት ዛሬ ከትላንቱ ተምረን ተባብረን ይህን አይነቱን ይሉኝታ ቢስ ጉዳይ ማስተካከል ካልቻልን ምናልባትም ሸዋ ላይ ወደፊት ለመምጣት የሚደፍር ሰው እስከ ማጣት እንደርሳለን።
 
የተወሰኑ ወዳጆቼ የደብረ ብርሃን ከንቲባን በተመለከተ ምነው ዝም አልክ ብለውኝ በወቅቱ መልስ ሰጥቼ ነበር። ምንም ባይጠቅምም ባደባባይ ልተንፍሰው።
ደስታ አንዳርጌን በከንቲባነት ዘመኑ በግልፅ ህዝብ የሚያነሳቸው አስተዳደራዊ ጥያቄዎች እንዳሉ የሚታወቅ ነው። እነዚህ ጥያቄዎች መመለስ የሚቻለው ባልዋለበት አውሎ ውሃ የማያነሳ እንኳን ማስረጃ ይቅርና ትክክለኛ መረጃ ሊቀርብበት ባልቻለ የውሸት ክስ ለዚያውም አደገኛ የሀገር ክህደት ክስ በመክሰስ አይደለም።
ደስታ አንዳርጌ “ከወያኔጋ ሰራ” የሚለውን የተመስገን ጥሩነህ እና ብርሃኑ ጁላን ክስ በቀላሉ የሚመለከቱ ግለሰቦች ቆም ብለው እራሳቸውን መጠየቅ ይገባቸዋል። ይህ የግለሰብ ገዳይ ብቻ አድርጎ መመልከት መጪውን አለማገናዘብም ነው። ወያኔ ማለት የሀገሪቱ ምክር ቤት አሸባሪ የተባለ ኃይል ነው። ከዚህ ኃይል ጋር በምንም መልኩ መስራት የሀገር ክህደት/Treason/ ነው።
ይህን ክስ በደስታ አንዳርጌ ላይ ማምጣት ሆን ተብሎ የተሸረበ እና ሀገር የሰራን ክህደት ታሪክ የማይገኝበት ህዝብ ጥላሸት ለማስቀመጥ የተደረገ ነው። እኔ እርግጠኛ ሆኞ የምናገረው በየትኛውም ደረጃ ያለ የሸዋ አመራር በዚህ አይነት የሀገር ክህደት ክስ አይጠረጠርም ይህ የእኔ ብቻ እምነት ነው ብዬ አላምንም ድፍን ሸዋን ብትጠይቅ ደስታ አንዳርጌም ሆነ ሌሎች አመራሮች ከወያኔ ጋር እንደማይሰሩ እርግጠኛ ሆኖ ይነግርሃል።
አዲሱን ተሿሚ ከንቲባ በተመለከተ እራሱን የቻለ ፍላጎቶች ያሉት ሹመት ስለሆነ ብዙ አልልም። ነገር ግን ጥያቄዎች አሉኝ
፩) ደስታ አንዳርጌ በፍርድ ቤት ወንጀለኛ እስካልተባለ ድረስ የከተማዋ ከንቲባ ነው በምን አይነት አሰራር ነው ሌላ ከንቲባ ሊሾም የቻለው!?
፪) ዋናው ከንቲባ ማረፊያ ቤት ስለሆነ ስራ እንዳይበደል ከንቲባ መሾም ቢያስፈልግ እንኳን ምክትሉ አለ ወይም ከተማዋ ካቢኔ አላት ከካቢኔ ውጪ የሆነ ሰው መሾም ለምን አስፈለገ!? ልብ አድርጉ ጠቅላይ ሙኑስትሩ ወደ ግንባር ስለዘመቱ ምክትላቸው ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው እየሰሩ ነው። ከዚህ የተለየ አሰራር የለም።
፫) የአንድ ከተማ ከቲንባ ለመሾም ከከተማዋ ምክር ቤት ወይም ካቢኔ ወይም እንደውን ከተማዋ ውስጥ ተወላጅ የሆነ ሰው ጠፍቶ ነው!?
በመጨረሻ ሰሚ ካለ ምክር ተመከሩ ከትላንት መማር ካልቻልን ዛሬም የትላንቱን አይነት ተፈራ ወንድማገኝን የመሰለ አመራር ያጣንበትን ውስጣዊ መጠላለፍ ካልተውን ነጋችን ጨለማ ብቻ ይሆናል። ብዙም ስለተፈራ ወንድማገኝ መናገር አልፈልግም ነገር ግን እንዴት ሆኖ ከህዝብ እና ከፖከቲካው እንዲርቅ እንተደረገ ቢያንስ አሁን መረዳት የሚቻል ይመሰለኛል። የክልሉ ፖለቲካ መቋቋም የምትችሉት ስትደጋገፉ እና ስትቻቻሉ ብቻ ነው አልያ ለራሳችሁም ለህዝቡም ሳትሆኑ ትቀራላቹህ። በተለይ ደብርፕብርሃን ላይ ሹመኞችን ከባችሁ በመንደር እየከፋፈላችሁ ያላችሁ ሰዎች እረፉ ተመከሩ።
– ዝናሽ አሳምነው ፅጌ
 

ፈቃዱ ምሥራቅ

ሰውዬው ኦሮሞ ነው? ትግሬ፣ ጉሙዝ ነው? ከሆነ እሺ። ከሌላ ቦታ የመጣ አማራ ስለሆነ ብቻ ከሆነ ግን የአዲስ አበባን የኦሮሙማ ዘር አጥፊ አገዛዝ በአማራ መካከለ ያለ ማስመሰል የለየት ሤራ ነው። አማራን ለመከፋፈል ሆን ተብሎ ከኦሮሙማ በኩል የመጣ ሤራ እንደሆነ ነው የምናስበው፣ የአዲስ አበባን የኦሮሙማ አውዳሚነት በአማራ ውስጥ አቻ በመፈለግ አማራን ለመከፋፈል፣ የእነሱን ጉድ ለማሳነስ ሆን ተብሎ የተወረወረ መርዝ አድርገን እናየዋለን፣ በነገራችን ላይ የእነ አቶ እሸቴና ደስታ የጎጥ ሠንሠለት ደብረ ብርሃንን ሰንጎ እንደያዛት እኛ እናውቃለን፣ በአቶ ደስታ መነሣት አቧራ የተነሣው ከልብ ለሸዋም ሆነ ለደብረ ብርሃን ታስቦ ቢሆን መልካም ነበር፣ ነገር ግን ነገሩ ሌላ ነው።
 

Muluken Feleke

ደብረብረሃንን ለማስተዳደር አማራ መሆኑ ብቻ በቂ ነዉ። ይህንንም ያልኩት ዘመኑ በዘር የታጠረ በመሆኑ እንጂ ማንም ኢትዮጵያዊ የትኛዉንም ከተማ ሊያስተዳድር ይችል ነበር።
ትግላችንም ወደዚያዉ ለመሄድ ነዉ።
የአሁኑ ችግራችን እሱ አይደለም። ጥያቄአችን መልካም አስተዳደር ማጣት ነዉ።
ሰው እንዴት ለወንበር ብሎ የገዛ ወንድምኑ ያለ መረጃ በውሸት በሴራ ፖለቲካ ካለስሙ ስም ሰጥቶ ያስራል???
ሰውን በሰራው ስራ እንጂ በፈጠራ ድራማችሁ ወንበር ለማስለቀቅ ብቻ ያለ ስም ስም ሰጥታችሁ ማሰር ነውር ነው።
የደብረብርሃን ከንቲባ ደስታ አንዳርጌን በሴራ ፖለቲካ አስራችሁ በሱ ቦታ ሌላ ሰው ለመሾም ምን አሮጣችሁ?! በዚህ ወቅት የሚሾም ሹመት ጤነኛ አይመስለኝም በደንብ መመርመር ያስፈልጋል!! በዚህ ወቅት ስለስልጣን እሽቅድምድሞሽ የምናደርግበት ወቅት አይደለም ህልውናችንን የምናስጠብቅበት ወቅት እንጂ!!
ደስታ ጥፋተኛ ይሁን አይሁን ሳይረጋገጥ የሱን ወንበር እደ ቅርጫት ስጋ እኔ ልሁን እኔ ልሁን ከንቲባ እያላችሁ እርስ በራሳችሁ መባላታችሁ ሲበዛ ነውር ነው።
ፍላጎታችሁ ወንበር ከሆነ እሱን ማሰር ምን አስፈለገ ስታስሩ በመነጋገር በሰላም ወንበሩን መቀበል ትችላላችሁ።
ስልጣን እኮ እርስት አይደለም ቅብብሎሽ እንጂ ግን በሴራ አስራችሁ ማሰቃየት ሀጥያት ነው። በሰራችሁት ስራ እጅግ በጣም ልታፍሩ ይገባል!

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.