Breaking News
Home / Amharic / የዝቅጠትን ክብረ ወሰን የሰበረው ጌዲዮን ጢሞቴዎስ – Achamyeleh Tamru

የዝቅጠትን ክብረ ወሰን የሰበረው ጌዲዮን ጢሞቴዎስ – Achamyeleh Tamru

የዝቅጠትን ክብረ ወሰን የሰበረው ጌዲዮን ጢሞቴዎስ
 
ጌዴዮን ጢሞቴዎስ በሕግ ትምህርት የመጨረሻ ዲግሪ [Terminal Degree] የደረሰ ሰው ነው። ጌዲዮን በአሁኑ ወቅት የፍትሕ ሚኒስትር ሲሆን ቀደም ብሎ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ነበር። ፋሽስት ወያኔ በአሸባሪነት እንዲፈረጅ ለፓርላማው ተብዮው የሕግ ምክረ ሀሳብ ያቀረበ ጌዴዮን ጢሞቴዎስ ነው። በሌላ አነጋገር ፋሽስት ወያኔ በአሸባሪነት የተፈረጀው ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ለፓርላማ ተብዮው ባቀረበው የሕግ ምክረ መሰረት ነው።
 
ፋሽስት ወያኔ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊት ካምፖች ላይ “መብረቃዊ ጥቃት” መፈጸሙን ተከትሎ በነ ጌታቸው ረዳ ላይ መከላከያ ሠራዊቱ ላይ ጥቃት በመሰንዘር ወንጀል ከፍ ባለ የአገር ክህደት ወንጀል፣ በሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ተብዮው ላይ በፈጸሙት ወንጀልና የጦር መሣሪያ ይዞ በማመፅ ወንጀል የከሰሳቸው ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ራሱ ነበር። ይህንን ሁሉ ያደረገው ጌዴዮን ጢሞቱዎስ፤
1. በሕግ ሶስተኛ ዲግሪ ድረስ ዘልቆ የቀሰመው የሕግ ሞያ የጣለበት ግዴታ ሳይገታው፤
2. ዐቃቤ ሕግና የፍትሕ ሚኒስትር ሆኖ የሚመራው መስሪያ ቤት ራዕይና ተልዕኮ ሳያግደው፤
3. ፋሽስት ወያኔን በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ ምክረ ሀሳብ ያቀረበበትና ያስፈረጀበት ኃላፊነት ሳይገደው፤
4. በሽብርተኝነት ያስፈረጀው ድርጅት ከሽብር ፈጻሚነት መዝገብ አለመሻሩ ሳይገድበው፤
5. በአገር ክህደት፣ በሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ላይ በፈጸሙት ጥሰትና የጦር መሣሪያ ይዞ በማመጽ የመሰረተባቸው ከፍተኛ የወንጀል ክስ አለመቋረጡ ሳያስጨንቀው፤
 
በሽብርተኛነት ካስፈረጀው ድርጅት ቃል አቀባይ፤ በአገር ክሕደት፣ በሽብር፣ በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት በማድረስ፣ በሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ላይ በፈጸመው ጥሰትና የጦር መሣሪያ ይዞ በማመጽ ከፍተኛ ወንጀል ፈጽሟል ብሎ ከከሰሰውና የሚመራው መስሪያ ቤት የእስር ማዘዣ ካወጣበት ከጌታቸው ረዳ ጋር ሠላሳ ሁለት ጥርሱን እያፈገገ ከታች እንደምታዩት እንዳሻው ይሆናል።
 
ጌዲዮን ጢሞቴዎስ እስከተከፈለው ድረስ እውነት፣ መርኅ፣ ኅሊና፣ ሞራል፣ የሞያ ስነ ምግባር፣ ቤተሰብ፣ ወዘተ የመሳሰሉት በማያሳስቡት low life የሚመራው የፍትሕ ሚኒስቴር የመስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የወንጀል ተከሳሽና የእስር ማዘዣ ካወጣበት አሸባሪ ጋር የመስሪያ ቤቱ ቁንጮ በአንድነት እንዲህ በሠላሳ ሁለት ጥርሱ እያፈገገ የፍትሕን ጥርስ ሲያረግፍ የምትመራው መስሪያ ቤት ስነ ምግባርና እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ድረስ የተማርህበት የሕግ ሙያ እንዲህ እንድታደርግ አይፈቅድም ብሎ የሚጠይቅ የሚጣላ ኅሊና ያለው አንድ እንኳን የፍትሕ ሚኒስቴር ሠራተኛ እንዴት ይጠፋል?
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.