Breaking News
Home / Amharic / የዘመነ ካሴ መልእክት !

የዘመነ ካሴ መልእክት !

የፋኖ ዘመነ ካሴ መልዕክት !
———————————-
“በዚህ ወቅት በየቀኑ አጀንዳ ስሆን ይጨንቀኛል። እናም ፌስቡክን ስለዘጉብኝ አንተ መልዕክቴን አስተላልፍልኝ? ” ዘሜ !

የድንግል ማሪያም ልጅ በሚያውቀው ሁሌ አጀንዳ ስሆን ይጨንቀኛል፥ያመኛልም። ቂሎች ሆነን እንጂ ከኔ ከአንድ ተራ ኩታራ ይልቅ ብዙ አንድ ሴኮንድ እንኳን የማይሰጡ ከሳት የጋሉ አጀንዳዎች አሉን ፤ ነበሩን።ለመመሳሰልና ለመምሰል ካልሆነ እምብዛም የዚህ አለም ሰው አይደልሁም ፥ ስለሆነም ለኔ ሞት እረፍት ነው።

አሳምነው “አንድ ቀን ያጠፉኛል ፥ለኔ እኮ ሞት ረፍት ነው!” እንዳለኝ ሄደ። ለኔም ሞት እረፍት ነው። ስለዚህ ሞትን አልፈራውም በሽህ አቅጣጫ የተከበበ ህዝብ እንዴት ይህን ያክል ማስተዋል ያንሰዋል!?

አንድ ነገር ሆነ በተባለ ቁጥር የተጨነቃችሁ ወገኖቼ ፈጣሪ አላህ ይጨነቅላችሁ። አልችል እያልሁ እንጅ በኔ ጉዳይ አንድ ሰው ለአንድ ማይክሮ ሴኮንድ እንኳን እንዲያስብ የምፈልግ ሰዉ አይደለሁም።

ጠላቶቼ ሆይ! ፍርሃትን በስም እንጅ በስሜት ከማያውቅ ማህበረሰብ ውስጥ እንደበቀልሁ ትረዳላችሁ ዘመነ ፈርቶ አያውቅም ዝንት ዓለም መቼምም አይፈራም።

እኔ የትግሉን ፍሬ ላላይ እችላለሁ በእርግጥም ግን ይሄ የኔ ትውልድ ግን ያሸንፋል! በዚህ ትዉልድ የነፍሴን ያህል ፍጹም እርግጠኛ ነኝ።

ድል ለአማራ ህዝብ!!!
ድል ለአፋር ህዝብ!
ድል ለኢትዮጲያ ህዝብ!!

አዲስ ትውልድ፥አዲስ አስተሳሰብ፥አዲስ ተስፋ!

ZOOM CONFERENCE on 29.01.2022

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.