Breaking News
Home / Amharic / የወሎ ህዝብ በረሀብ እየረገፈ ነው! ሰው ሰራሽ ረሃብ ! – በለጠ ሞላ (አብን)

የወሎ ህዝብ በረሀብ እየረገፈ ነው! ሰው ሰራሽ ረሃብ ! – በለጠ ሞላ (አብን)

በቃ ‼️
*****
የአብኑ ሊቀመንበር በለጠ ሞላ ጌታሁን ይህን ብሏል።
(ጉዳዩን በተጨባጭ ስለማውቀው እውነቱን እጋራለሁ)

እንደትላንቱ ሀገራዊ ፖለቲካችን ሁሉ ዛሬም የወሎ ህዝብ በርሀብ እንዲረግፍ እየተደረገ ነው !!!

አስቸኳይና ጥብቅ ማሳሰቢያ ለአማራ ክልል መንግስት፣ ለፌዴራል መንግስት፣ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ እንዲሁም ለአለማቀፍ ተቋማትና መንግስታት:-

ይህ ተጨባጭ እውነታ ስለሆነ ሀገር ይወቀው ታሪክም ይመዝግበው፤

በትግራይ ወራሪ ሀይል በተያዙ የሰሜን ወሎና የዋግህምራ ከተሞችና የገጠር መንደሮች ከጦርነት ጭፍጨፉ የተረፈው ህዝባችን በረሀብ ሰቆቃ በከፍተኛ ሁኔታ እየረገፈ ይገኛል። ስለሁኔታው ክልሉም ይሁን የፌዴራሉ መንግስት በቂ መረጃ እንዳላቸው እናውቃለን!

በህዝባችን ላይ ይህን ያህል መንግስታዊ ጭካኔና ክህደት ለምን??

ህዝባችን በጦርነት፣ በፋሽስታዊ ጭፍጨፋና በረሀብ ካለቀ በኋላ ምድረ በዳ የምንረከብበት አማራዊም ይሁን ሀገራዊ ፖለቲካ ይኖራል ተብሎ ከታሠበ ትልቅ ስህተት ይሆናል !!!

መሬት ከህዝብ አይቀድምም፣ ለህዝብ መዳን ሲባል ደግሞ ሁሉም ፖለቲካዊ አማራጭ ይወሰዳል!

ስለሆነም ህዝባችን በርሀብ ከማለቁ በፊት በአስቸኳይ ከጦርነት ነፃ እንዲወጣ በጥብቅ እንጠይቃለን !!!

Let the whole world know this:
entire communities subjected to starvation and thousands already dying everyday in TPLF occupied towns and villages of North Wollo zone in Amhara region.

Enough with politically trapping entire people and letting them die silently !!!

#Raya#Kobbo and villages
#Woldia and villages
#Habru#Mersa and villages
#Meket and villages
#Gidan and villages
#Lasta#Lalibela and villages
#Abergele and villages

Enough with systematic deprivation of #WOLLO !!!

We say NO to this !!!

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.