Breaking News
Home / Amharic / የወልቃይትን ባጀት ያገደ ቱርክ ቢሄድ ምን ፋይዳ ያመጣል?

የወልቃይትን ባጀት ያገደ ቱርክ ቢሄድ ምን ፋይዳ ያመጣል?

በቅድሚያ ይሄን በማለት እጀመራለሁ። “አትናገሩ፣ ዝም በሉ፣ ወያኔን ማገዝ ነው” የሚባል ነገር አለ። ይህ አይነቱ አነጋገር አፍራሽና ጠቃሚ ያልሆነ አነጋገር ነው። በመንግስት ሃላፊዎች ተጠያቂነት እንዳይኖር የሚያደርግ ነው። ሰው ዝም ሲል በጥፋት ስራዎቻቸወ እንዲቀጥሉ የሚያበረታታ ነው። ያ ብቻ አይደለም እንደውም ዝም ማለቱ፣ ችግሮች በቶሎ እንዲፈቱ ግፊት አለማድረጉ፣ በስህተቶች ላይ ስህትቶች እየተደራረቡ የባsእ ችግር ውስጥ እንድንወድቅ የሚያደርግ ወያኔንም ማገዝ ነው የሚሆነው። መጠየቅ ያለብን “ዝም ማለታችን ነው፣ ወይስን ዝም አለማለታችን ወያኔን የሚጠቅመው ?” የሚለውን ጥያቄ ነው።
የዶር አብይን ቱርክ መሄድ እንደ ትልቅ ድል አድርገው እያዳመቁ ያሉ ወገኖች ይገርሙኛል። ቆይ ዶር አብይ አህመድ ምን እንደተነጋገረ እውቀቱ ኖሯቸው ነው ? የቱርኩ አቋምስ ምን ያህል ከነ አሜሪካ ተለይቶ ነው ? ቱርክ መሳሪያ ለኢትዮጵያ ልትረዳ ነው የሚሉም አሉ። የሰማነው ግን ከወያኔዎች ጋር መነጋገርና መወያየት እንደሚገባ መግለጿን ነው። የተባለው እውነት ሆኖ መሳሪያዎች ከረዳችም ደግሞ የቱርክ መሳሪያ ነገ ለወያኔ አለመሰጠቱ ምን ማስተማመኛ አለን ? አሁንም እኮ ወያኔዎች እየተዋጉበት ያለው ከባባድ መሳሪያዎች የአብይ መንግስት ትቶ የሄደላቸው መሳሪያዎች ናቸው።
በግንባር ፊት ለፊት እየተዋደቁ ያሉ በዋናነት የአፋርና የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሺያዎችና ፋኖዎች ናቸው። የተወሰኑ በአሻጥረኛ የጦር መኮንኖች የማይመሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እየተዋደቁ ነው። (ሌሎች ያው በአሻጥር አካባቢዎችም ለወያኔዎች ጥለው እንዲሄዱ የተደረጉም አሉ”” እንደውም እነዚህ ይበዛሉ))። ቁጥሩ ቀላል የማይባል ወጣት ጦርነቱን እየተቀላቀለ ነው። ምክንያቱ ወያኔ “ከአማራው ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ” ብላ በሕዝብ ላይ ስለተነሳች ፣ ጦርነቱ ሕዝባዊ ጦርነት በመሆኑ።፡
ነገር ግን ይሄ በመቶ ሺሆች ምን አልባትም ሚሊዮን የሚቆጠር ወጣት በቂ ትጥቅና ስንቅ የለውም። ያለውም ጥቂትና የድሮ መሳሪያ ይዞ፣ ህዝቡን ከራሱ ቀንሶ ምግብ እያቀረበለት ነው እየተዋጋ ያለው።
በአብይ አህመድ የሚመራው የፌዴራል መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ ባጀት እንኳን በሚኒስትሮች ምክር ቤት አስፈቅዶ፣ በስሜን የሚዋደቁ ወገኖች አስፈላጊውን ስንቅና ትጥቅ እንዲያገኙ ማስድረግ እንኳን አልቻለም። ይሄንን እንኳን መሰረታዊ ክፍተቶችን መሙላት ያልቻለ ደካማ መሪ ቱርክ፣ ዱባይም አስመራ እያለ ቢዞር ምን የሚፈይደው ነገር አለ ? ይልቅ ዝም ብለን ራሳችንን ባናሞኝ ይሻላል።
በረባ ባልረባ ዉሸቶቻቸውን ለመሸፈን ከምንሞክር፣ በትንሹም በትልቁም ዉሃ የማይቁጥር ነገር ይዘን የነርሱ ፕሮፓጋንዲስት ከምንሆን፣ ከህወሃት ጋር ፊት ለፊት እየተዋደቁ ያሉ ማህበረሰባት “በበቂ ሁኔታ ለምን አይደገፉም?” ብለን ጫና ማሳደሩና ግፊት ማድረጉ ላይ ነው መስራት ያለብን።
በግላችን የምናዋጣው ገንዘብ አለ። እንደ አበበ በለው ያሉ ወገኖች ብዙ እየሰሩ ነው። ግን ይሄ ሁሉ ተጠራቅሞ አንድ ቢሊዮን ብር አይሞላም። በቂ አይደለም። የግድ መንግስት ለጦርነቱ በጀት መመደብ አለበት።
እንዴት ? ቀላ መልስ አለ። ለሌሎች ክልሎች ከሚሰጥ ባጀት በመቀነስ፣ አንዳንድ ፕሮጀክቶችም በማጠፍ የፌዴራል መንግስቱ ገንዘብ ማግኘት ይቻላል። ለምሳሌ በኦሮሞ ክልል በአዲስ አበባ በቢሊዮን ብሮች የኦሮሚያ ፍርድ ቤት የሚባል ለመስራት ባጀት ተመድቧል። ያንን መሰረዝ ይችላል። በፌዴራል ደረጃም እንደ አስፈላጊነታቸው ታይቶ አንዳንድ ፕሮጀክቶችን ማስተላለፍ ይቻላል። መንግስት አቅም አለው። ለትግራይ ክልል ከሁለት አመት በፊት የተመደበው ባጀት 7 ቢሊዮን አሁንም ደግሞ ወደ 12 ቢሊዮን ብር አካባቢ ነው፡ ለትግራይ የተጨመረው ግማሹን ወደ አማራ ክልል ማድረግ ይቻላል።፡ብዙ አማራጮች አሉ።፡ የፌዴራል መንግስቱ ግን ያንን አላደረገም !!!!!!
በወልቃይት ጠገዴ ወያኔ 12 ጊዜ ዉጊያ ከፍታ 12 ጊዜ ተደምስሳለች። እዚያ ያለው ማህበረሰብ ራሱን በራሱ አደራጅቶ ነው ወያኔን እየታገለ ያለው። ከላይ እንዳልኩት ለጂንካ፣ ለአምቦ፣ ለአርባ ምንጭ፣ ለደሴ፣ ለጂጂጋ በአጠቃላይ የፌዴራል መንግስት ለሁሉም ወረዳዎችና ዞኖች በክልል ደረጃ ባጀት ይመድባል። በፌዴራል የሚሰጠው ባጀት በክልሎች ከ70% እስከ 90% የሚሸፍን ነው። ምን ማለት ነው ክልሎች በብዛት የሚንቀሳቀሱት ከፌዴራል በሚመጣ ገንዘብ ነው።
እሺህ የተለየ ባጀት ባይመደብ እንኳን፣ ወልቃይት ጠገዴዎች ለነርሱ የሚገባ የተመደበ ባጀትት ስላለ፣ በትግራይ ውስጥ እንዳለ ታስቦ፣ ለትግራይ ከተመደበው ውስጥ የተወሰነው ለነርሱ መሰጠት ነበረበት። ግን ላለፊት 9 ወራት የአብይ አህመድ መንግስት የፌዴራል ባጀት እንዳይሰጣቸው ነው ያደረገው። ኢፍትሃዊ ኢኮኖሚክ በደል ነው በአብይ መንግስት የተፈጸመባቸው። የሚገባቸውን ፣ እንደ ዜጎች፣ በአብይ መንግስት ተከልክለዋል። እስከ አሁን ድረስ ገንዘብ አልተለቀቀላቸውም።
አብይ አህመድ ቱርክ ሄደ ከምትሉኝ የወልቃይት ገንዘብ ተለቀቀ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ባጀት እንዲመደብ የሚኒስተሮች ምክር ቤትን ሰብሰባ ጠራ ብትሉኝ እኔም አብሬ ባላዳምቅም፣ ቢያንስ ጥሩ ተሰራ ማለት እችል ነበር።
 
 
 
 
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.