Breaking News
Home / Amharic / የክተት ዘመቻው አንድምታ፣ አስፈላጊነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ! – Dessalegn Chanie

የክተት ዘመቻው አንድምታ፣ አስፈላጊነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ! – Dessalegn Chanie

ትግራይ ክልል አጠቃላይ ያሉ ወረዳዎች ብዛት 35 ነው። በፌደራል መንግስቱ የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ መሰረት መከላከያ ትግራይን ለቆ ከወጣ ባለፈው አንድ ወር ትህነግ በትግራይ ባሉ እያንዳንዱ ወረዳዎች የወታደር ምልመላ ኮታ በመጣልና በግዴታ መልምላ (Forced conscription) ከ3 ቀን እስከ አንድ ሳምንት የሚፈጅ የለብ ለብ ስልጠና በመስጠት ወታደር አሰባስባ እነዚህን ምልምል ወጣቶች ከፊት በማሰለፍ በመጀመሪያው ዙር ዘመቻ የተረፉትን እንደ ዋነኛ አጥቂ ጦር አድርጋ እየተዋጋች ነው።

የቀራትን ዋነኛ ተዋጊ ሀይል ፊት። በትግራይ ክልል አጠቃላይ ያሉ ወረዳዎች ብዛት 35 ነው።
የተማረኩ የትግሬ ወጣቶች በተለያየ መልክ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ለእያንዳንዱ ወረዳ ከ5 ሺእስከ 10 ሺ ወጣቶችን እንዲመለምሉ ትዕዛዝ ቢሰጥም በብዙ ወረዳዎች የተጠበቀውን ያክል ወታደር ሊገኝ አልቻለም። አንዳንድ ወረዳ 2 ሺህ፣ አንዳንድ 3 ሺ፣ ጥቂት ወረዳዎች ደግሞ ከ5 እስከ 7 ሺ መመልመል ችላለች።
ከፍተኛ አማካኝ ወስደን በየወረዳው 5 ሺህ ወታደር መልምላለች ተብሎ ቢታሰብ ትህነግ ወደ 175,000 ተዋጊ ህዝብ አሰልፋለች ማለት ነው። ትጥቅ ያለው ትጥቅ ይዞ፣ ትጥቅ የሌለው ጀሌውን «ከአማራ ልዩ ኃይል ማርከህ ታጠቅ» እየተባሉ እንደሚላኩ ምርኮኞቹ ገልጸዋል።
ስለዚህ የትህነግ ሀይል እስከ 175 ሺህ ሊደርስ እንደሚችል ሁሉም አማራ ግምት ውስጥ ማስገባት አለበት። ይህን የጥፋት ሀይል አሳንሶና አቃሎ ማየት፣ በቸልታ መመልከትና ማናናቅ ህዝባችንን ለመከራ፣ አገራችንን ለብተና የሚዳርግ ነው። ስለዚህ ይህን የሚመጥን ወይም የሚበልጥ ሀይል ማሰለፍ ተገቢ ነው።
እስከ አሁን በግንባር ያለው የአማራ ልዩ ሀይል፣ ፋኖና ህዝባዊ ሚሊሻ ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችንና ከሌሎች ክልሎች ልዩ ኃይሎች ጋር በመሆን አስደናቂ ውጊያ እያደረገ ቢሆንም፣ ከላይ ከተገለጸው የትህነግ አሰላለፍ ጋር ተያይዞ የሰው ቁጥር አለመመጣጠን ሊፈጠር እንደሚችል ለማንም ግልጽ ነው። ስለዚህ በወገን ጦር በኩል ለጊዜው ይህንን የሚመጥንና የሚመክት የሀይል ቁጥር ማሰለፍ በማስፈለጉ የአብክመ መንግስት የክተት አዋጅ አውጇል። ይሄም ተገቢና ንቅናቄያችንም ተቀብሎት ከአመራሩ እስከ አባላት ድረስ በሙሉ አቅማችን ለመተገብር የምንንቀሳቀስ ይሆናል። የጀግኖች አባቶቻችን የነ በላይ ዘለቀን ፀረ ፋሽስት የአርበኝነት ትግል የመቀላቀል ያህል ዕድል ለኛ ትውልድ ስለመጣም በዚህ ታሪካዊ የክተት ጥሪ ተሳትፈን ደማቅ ታሪክ ለመፃፍ የአማራ ወጣት ተዘጋጅቷል።
ወደ አማራ ክልል ሁኔታ ስንመለስ ክልሉ ወደ 170 አካባቢ ወረዳዎች አሉት። ከየወረዳው በትንሹ ከ3000 እስከ 5000 ተዋጊ ሀይል በክተት አዋጁ ማንቀሳቀስ ቢቻል እንኳ አሁን ግንባር ካለው የአማራ ሕዝባዊ ሰራዊት ላይ ተጨማሪ ከ500 ሺ እስከ 850 ሺ ወዶ ዘማች ይገኛል። በዚህም የትህነግን በሰው ማዕበል ጦርነት የማካሄድ ስትራቴጅ «እሾህን በእሾህ» በመንቀል ትህነግ ድጋሚ እሾህ ሆኖ ህዝባችንን እንዳይወጋ ማድረግ ይቻላል።
ይህን ዘመቻ በስኬት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከተወጣን በኋላ በቋሚነት ህዝባችን ሙሉ ትኩረቱን ወደ ሰላምና ልማት አዙሮ እንዲሰራ ለማድረግ በሳይንሳዊ ጥናት ላይ የተመሰረተና የህዝባችን ሰላም በአስተማማኝነት የሚጠብቅ የፀጥታ ሀይል እንዲደራጅ መደረግ አለበት። ለዚህም አሁን ወደ ማሰልጠኛ የገቡት አዳዲስ የአማራ ልዩ ሀይል ምልምል ወጣቶች መሰረት ይጥላሉ።
የአማራ ክልል መንግስት ላስተላለፈው የክተት አዋጅ ማንኛውም የመንግስትም ይሁን የግል መሳሪያ ያለውና የሚችል የአማራ ኃይል ወደ ራያና ወልቃይት መዝመት አለበት። መሳሪያ ይዞ መዝመት የማይችል ከሆነ መሳሪያውን መዝመት ለሚችል ማስረከብ አለበት።
በዘመቻው ለሚጓዙ የአማራ ዘማቾች እያንዳንዱ ቤተሰብ፣ ወዳጅ፣ ዘመድና ጎረቤት ደረቅ ስንቅ በአስቸኳይ አዘጋጅቶ መስጠት፣ ለክረምት የሚሆን የዝናብ ልብስ፣ የፕላስቲክ ገሳ፣ ሙቀት የሚሰጡ አልባሳት፣ ሽርጥ፣ ፎጣ፣ ኮፍያ፣ ትጥቅና ስንቅ ማዘያ የጀርባ ሻንጣ ወይም ከረጢት፣ የቁስል መጠቅለያ ነጭ ሻሽ፣ ሳንጃ አሟልቶ መላክ ያስፈልጋል።
በዘመቻው የማይሳተፈው የአማራ ህዝብና ወጣቱ ደግሞ በየአካባቢው ተደራጅቶ የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ የማስከበር፣ በተደራጀና በቀለጠፈ መንገድ ስንቅ ማዘጋጀት፣ የአርሶ አደሩ የግብርና ምርት እንዳይቀንስ የእርሻና የግብርና ስራውን መደገፍና ማሳለጥ፣ የዘማቾችን እርሻ ማረስና ቤተሰቦችን መደገፍ፣ እርስ በርስ መረዳዳት ያስፈልጋል።
ድል ለአማራ ልዩ ሀይል፣ ህዝባዊ ኃይልና ለጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.