በአዲስ አበባ ትምሕርት ቤቶች የሚፈጠሩ ግርግሮች ቀጥለዋል።
የአዲስ አበባ ትምሕርት ቤቶችን በኦሮሚያ ክልል ስር ለመሰልቀጥ የሚደረገው ስራ ተቃውሞ እየገጠመው ነው። አዲስ አበባ በቻርተር የምትተዳደር ከተማ ሁሉም ብሄሮች ያቀፈች ከተማ ነች ። አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ጀርባ በሚገኘው በአዲስ አበባ መስተዳደር በሚተዳደረው የብሄራዊ ትምሕርት ቤት ውስጥ የኦሮሚያ ባንድራ ሰቅለው የኦሮሚያ ክልልን ብሄራዊ መዝሙር ለማዘመር የተደረገው ሙከራ ከሽፏል። ወላጆች የት/ቤቱን በር ገንጥለው ገብተው ነው ልጆቻቸውን ያወጡት። ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ የመጡ አመራሮች ዳይሬክተሯን በማስፈራራት ለመውሰድ የሞከሩት እርምጃ በወላጆች ርብርብ ከሽፏል።
