Breaking News
Home / Amharic / የኦህዴድ/ብልጽግና ፖሊሶች ሽብር በአማራና ኦርቶዶክስ ላይ !

የኦህዴድ/ብልጽግና ፖሊሶች ሽብር በአማራና ኦርቶዶክስ ላይ !

የኦህዴድ/ብልጽግና ፖኢሶች ሽብር #ግርማካሳ
የወይብላ ማርያምን ታቦት ቤተክርስቲያን አታስገቡም በሚል ከኦህዴድ/ብልጽግና ፖሊስ በተተኮሰ ጥይት 4 የኦርቶዶክስ የእምነት ተከታዮች ጉዳት ደርሶባቸ ው በአለርት ሆስፒታል ህክምና ሲደረግላቸው ቆይቶ ሶስቱ ሕይወታቸው ማለፉን እየሰማን ነው፡፡
ብዙ ጊዜ እንደጻፍነው ሰዎቹ ማለት ኦህዴዶች “የኛ ጊዜ ነው፣ ተራችን ነው” ብለው የፈለጉት እያሰሩ፣ በፈለጉ ጊዜ እየገደሉ፣ እያፈናቀሉ፣ ህዝቡን እያሸበሩ ፣ እንደፈለጉ እየሆኑ የሚጠይቃቸው የለም፡፡ ከሕግ በላይ ናቸው፡፡
ኦህዴድ የተባለውን የወንጀለና የግፈኛ ስብስብ እስከመቼ፣ አገርን በዚህ መልኩ እያተራመሰ እንደሚቀጥል ሊገባኝ አልቻሉም፡፡
እነዚህ ሰዎች እንደዚህ የሚፈነጩት ፣ 1ኛ ህዝብን ስለናቁ ነው፡፡ 2ኛ ሲንቁን ሲጨማለቁብን ዝም በማለታችን ነው፡፡ ግፍና መከራን ተሸክሞ መኖር የሚፈልግ ማህበረሰብ ሁልጊዜ አንገቱን እንደደፋ ነው የሚኖረው፡፡ መብቱን የሚጠይቅ፣ ለመብቱ የሚታገል ማህበረሰብ ግን ነጻነቱን ያግኛል፡፡
ጎበዝ ሕወሃት ሕወሃት ስንል ከሕወሃት የባሰ ኦህዴድ የሚባል ተረኛና ከህወሃት የባሰ ዘረኛ ቡድን እንዳለ ካልተረዳህና ለህልዉናህ ለመብትህ ካልቆምክ፣ የህወሃትን ዘመን የምትናፍቅበት ጊዜ መምጣቱ አይቀርም፡፡ በተወሰነ መልኩም እየመጣ ነው፡
 
 
 
 
 
 
 
 
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.