Breaking News
Home / Amharic / የእምቦጭ መድኃኒት ተገኘ !

የእምቦጭ መድኃኒት ተገኘ !



መሪጌታ በላይ አዳሙ የእምቦጭን መድኃኒት ማግኘቱን እምቦጭን አድርቆ በተጨባጭ አሳይቷል።
ሆኖም ለሀገር ግድ የሌላቹው ቢሮክራቶች ሚስጥሩን ካልገልልለጥክልን ፍቃድ አንሰጥህም ብለው እንቅፋት ሆነውበታል። ጉዳዩ የሚመለከታችሁ ባሉስልጣናት ቤስቸኳይ አንድ ብላችኋቸው ባለሙያው አገር ያድን!
 ይኼን ተመልከቱ።መርጌታ በላይ አዳሙ ያገኙት መድኃኒት እምቦጭን እንዲህ ነው ያደረቀው ‼️
” በ24 ስዓት ውስጥ እምቦጭን የሚያጠፋ መድኃኒት በእጃቸው ይዘው ይንከራተታሉ …” ታደለ ጥበቡ
መርጌታ በላይ አዳሙ ያገኙት መድኃኒት ተሞክሮ እንደምታዮት እምቦጭን በዚህ መልኩ ድራሹን አጥፍቶታል።
የአማራ ክልል የምርምር ተቋም እና የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ
ደግሞ ይኬን አረጋግጠው ደብዳቤ ጽፈዋል።
ነገርግን የደን እንስሳትና እፅዋት ምናምን የሚባል ቢሮ መድኃኒቱን ያገኘባቸውን ዕፅዋት ዘርዝረህ አምጣ ወይንም እንግዛህ ነው የሚሉት።
መርጌታ በላይ አዳሙ ደግሞ “የለፋሁበትን ግኝት ለማንም አሳልፌ አልሰጥም፤አልሸጥምም ለምርምር ስራየ መጀመሪያ የባለቤትነት መብት ይሰጠኝ” ነው የሚሉት።
በዚች አገር በየቢሮው የተሰገሰጉ ለአገር ቅርስ የማይጨነቁ ማህይማን ደግሞ “መድኃኒቱን ያገኘህበትን ዕፅዋት ካላመጣህ አንቀበልህም” በማለት ከቢሮ አስወጥተው በራቸውን ዘግተውበታል።በዚህ ላይ ጣና ሐይቅ እየደረቀ ነው፤መርጌታ በላይ አዳሙ ደግሞ በ24 ስዓት ውስጥ እምቦጭን የሚያጠፋ መድኃኒት በእጃቸው ይዘው ይንከራተታሉ። ደካማ እናቶች ደግሞ እምቦጭን ለመንቀል ሲታገሉ ይውላሉ።
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.