Breaking News
Home / Amharic / የኣማራ ሴቶች ማህበር

የኣማራ ሴቶች ማህበር

በዶክተር መሀሪ የተገኝው ለ10 የአማራ ሴቶች የትምህርት እድል ምደባ ላይ በአሚሪካ የሚኖሩት የአማራ ሴቶች ማህበር የፃፉትን ፓስት አድርገው ነበር ። በዛ ላይ አስተያየት እንድሰጥ ተጠይቄ ትናንት ስላልቻልኩ ዛሬ ትንሽ የራሴን ሀሳብ መስጠት ፈለኩ። ምድቡ 2 ለጎንደር ፣ 2 ለጎጃም 2 ለሸዋ ፣2 ለወሎ ፣አንድ ለወልቃይትና አንድ ለራያ ነው። በግሌ ይህ አመዳደብ ትክክልና ህዝባችንን ሳይከፋፍል አብሮነትን የሚያሳይ መልካም ተግባር ነው። የአማራ ሴቶች ማህበር በፊስ ቡካቸው አስተያየት እንድትሰጡበት በለጠፉት ፓስት ላይ ኮሜን የሰጣችሁትን አይቸዋለሁ።
አንዳንዶቻችሁ ትክክል እንዳልሆነና አማራ በሚል ብቻ እንዲመደብና ይህ የጎጥ አይነት ይመስላል በማለት የፃፋችሀን አይቻለሁ። በግሌ በዚህ አልስማም ። እነ እርስቴና የመሀበሩ አባላት የወሰኑት ውሳኔ ትክክል ነው።
በእርግጠኝነት እነዚህ ሰዎች በአንድ የአማራ ህዝብ ስም ከአንድ አካባቢ ወይም ዘመዶቻቸው ልከው ማስተማር ይችላሉ። ነገር ግን የአማራን ህዝብ አንድ ለማድረግና ለመተማመን አልፎም እኩልነት እንዲፈጠር የሰሩት ትልቅ አስተማሪ የሆነ ጉዳይ ነው። አማራ ክልል ውስጥ ጎንደር ጎጃም ወሎ ሸዋ የሚባል ምድብ ቦታ አለ ይሄ የማይካድ ሀቅ ነው። ስለዚህ እህቶቸ እኔ ኮርቸባችኃለሁ። በርቱልኝ እግዚአብሔር ይርዳችሁ ታሪክ አንድ ቀን ይዘክራችኃላ ከታሪክም በላይ ስራቹሁ ለዘላለም እርካታና የአይምሮ እረፍትን ይሰጣችኃል በርቱልን።
እኛ ሴቶች እናትም እህትም ሚስትም ነን ብዙ የማስተዋል ፀጋ እግዚአብሔር ሰጦናል። ደግሞ ተረቱ ከአንድ ጠንካራ ወንድ ጀርባ አንዲት ጀግና እንስት አለች ይባል የለ ። ሴቶች በአማራ ህዝብ ትግል ላይ የበለጠ ብንሳተፍ አፍሪዎች እንሆናለን ብየ አምናለሁ።
ዝንታለም አማራ💚💛❤

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.