Breaking News
Home / Amharic / የኢትዮጵያ የባህር በር ማጣት ታሪክ!!! – By Dr. Debru Negash (MD)

የኢትዮጵያ የባህር በር ማጣት ታሪክ!!! – By Dr. Debru Negash (MD)

የኢትዮጵያ የባህር በር ማጣት ታሪክ!!!

~ ኦቶማን ቱርክ እና የኢትዮጵያ ጦርነት (1557_1589)
ጦርነቱ የተቀሰቀሰው በ1557 ኦዝደሚር ፓሻ የወደብ ከተማ የሆነችውን የምፅዋ ከተማን ከያዘ በኃላ ከኦቶማን ኢምፓየር የኢትዮጵያ ግዛት ወረራ ጋር በተነሳ ነው።

~ የግብፅ እና ኢትዮጵያ ጦርነት በኢትዮጵያ ኢምፓየር እና በግብፅ ኬዲቫት መካከል ከ1874 እስከ 1876 ባለው ጊዜ ውስጥ የኦቶማን ኢምፓየር ራስ ገዝ በሆነው በግብፅ መካከል የተደረገ ጦርነት ነበር።

~ የመጀመርያው የጣሊያን እና የኢትዮጵያ ጦርነት ወይም የመጀመሪያው የጣሊያን እና የአቢሲኒያ ጦርነት እየተባለ የሚጠራው፣ በቀላሉ በጣሊያን የአቢሲኒያ ጦርነት ተብሎ የሚጠራው በጣሊያን እና በኢትዮጵያ መካከል ከ1895 እስከ 1896 የተደረገ ወታደራዊ ፍጥጫ ነበር። ይህ ጦርነት በአድዋ የኢትዮጵያ ድል አድራጊነት የተጠናቀቀው ነው።

~ Ottoman Turkey Ethiopian war (1557_ 1589)
The war was triggered with the Ottoman Empire invading territories of the Ethiopian Empire starting in 1557, when Özdemir Pasha took the port city of Massawa
~ The Egyptian–Ethiopian War was a war between the Ethiopian Empire and the Khedivate of Egypt, an autonomous tributary state of the Ottoman Empire, from 1874 to 1876.
~The First Italo-Ethiopian War, also referred to as the First Italo-Abyssinian War, or simply known as the Abyssinian War in Italy, was a military confrontation fought between Italy and Ethiopia from 1895 to 1896. The war ends by Ethiopians victory on the battle of Adawa.

~ የኢትዮጵያ የባህር በር ጉዳይ ኢትዮጵያን ከቀይ ባህር የመነጠል ጉዳይ ለብዙ አመታት የቀጠለ እረጅም ታሪክ ያለው ነው። ለብዙ ጊዜ የውጭ ሃይላት በቀይ ባህር በኩል በኢትዮጵያ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችንና ወረራዎችን ፈጽመዋል። እነሱም ቱርኮች፣ ግብፆች፣ አውሮፓውያን ጣሊያኖች ሲሆኑ፣ በቀይ ባህር በኩል ተደጋጋሚ ጥቃትና ወረራ ፈፅመዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ማጣት፣ የቀይ ባህርን ተደራሽነት ማጣት ታሪክ እንዲህ ይጀምራል።

~ ከመጀመሪያዎቹ ዋና ከሚባሉት ኢትዮጵያ በቀይ ባህር በኩል ያላትን ተፅኖ ፈጣሪነት እያጣች የመጣችው የአፄ ዩሐንስ በቀይ ባህር አካባቢ የመጡትን ጣሊያኖች ችላ ማለት ተከትሎ ነው። በዚያ የነበረው የጣሊያን ቅኝ ገዥ ኃይል ተስፋፍቶ ኤርትራን በመውረር ቅኝ ግዛት ሊያደርግ በቅቷል። ይህ የቅኝ ገዥ ኃይል በየ ጊዜው እየተስፋፋ ከአፄ ዩሐንስ ሞት በኃላ መስፋፋቱን ቀጥሎበት ከአፄ ዩሐንስ በኃላ ከነገሱት አፄ ምኒልክ ጋር እስከመዋጋት የደረሰ ሲሆን። ይሄም ኢትዮጵያን በሙሉ ቅኝ ግዛት የሚያደርገውን መስፋፋት አጠናክሮ ገፍቶበት አድዋ ላይ በተደረገው ጦርነት ሊሸነፍ እና ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛት የማድረግ ጥረት ሳይሳካለት ቀርቶ ከሽፏል።

~ ከዚህም ድል በኃላ በአፄ ምኒልክ እና በጣሊያን መንግስት መካከል የስምምነት ውል ተፈርሞ የሁለቱ ወሰን መረብ ምላሽ የሚል ውል የፀደቀ ሲሆን። ሌላው በውሉ አንቀፅ አምስት ላይ “ጣሊያን የያዘውን ቦታ እለቃለሁ ባለ ጊዜ እና ለቆ ሚሄድ ከሆነ ለሌላ ለማንም ሶስተኛ አካል አሳልፎ ሊሰጥ አይቻለውም” የሚል አለበት። ይህ አንቀጥ ጣሊያን የያዘው ቦታ ባለቤት አለመሆኑን በትክክል ገላጭ ነው። የአቅም ጉዳይ እንጂ ለጣሊያን ይሁን ተብሎ የተሰጠ አለመሆኑን በተፈረመው ውል አንቀፅ አምስት በግልፅ ያሳያል።

~ ከአፄ ምኒልክ በኃላ ተተኪ የነበሩት ልጅ እያሱ ለሶስት ዓመት ሀገር ተረክበው ቢመሩም አይናቸውን ቀይ ባህር ላይ ጥለው ስለነበር “ፈረሴን የቀይ ባህር ውሃ ካላጠጣሁ አልነግስም እያሉ ዘውድ ሳይደፉ እየፎከሩ እንደቆዩ ነው ሚነገረው። ከዚያም በንግስት ዘውዲቱ እና በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሲተኩ ኤርትራ በጣሊያን እጅ እንደ ወደቀች ነበረች። በኃላም ጣሊያን ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛቷ ስር የማድረግ ምኞቷን ለማሳካት ባደረገችው ዳግም የወረራ ጦርነቱ በመላው ሀገሪቱ ጦርነት ተስፋፍቶ ንጉሱም ሀገር ጥለው ሂደው በስደት በእንግሊዝ ሀገር ሲቀመጡ፣ የኢትዮጵያ አርበኞች ግን ለአምስት አመት በዱር በገደሉ እየተደበቁ እያደፈጡ የጣሊያንን ወራሪ ተዋግተው ፋታ በመንሳት ሀገሪቱን አረጋግቶ ለመግዛት እንዳይችል አድርገው፣ ከአምስት አመታት ወከባና ተጋድሎ በኃላ አሸንፈው ሲያስወጡት፣ ንጉሱም ከስደት ተመልሰው ስልጣናቸውን አስቀጥለዋል።

~ በዚህ ጊዜ የኤርትራ ጉዳይ በተባበሩት መንግስታት ቀርቦ ከፍተኛ ክርክር ተካሂዶበታል። በዚህ ክርክር የኢትዮጵያዊዩ ዲፕሎማት የአክሊሉ ኃብተወልድ ሚና ቀላል አልነበረም። የተባበሩት መንግስታትም ጉዳዩን መርምሮ ኤርትራ በፌዴሬሽን የኢትዮጵያ አካል እንድትሆን ተወሰነ። የኢትዮጵያ አጋር የነበረችው እንግሊዝ በሞግዚትነት ከጣሊያን ተረከበች። የእንግሊዝ ሞግዚትነት ካበቃ በኃላ ኤርትራ በፌዴሬሽን ስትተዳደር የነበረችውን ፌዴሬሽኑን አፍርሳ ከኢትዮጵያ ጋር አሃዳዊ ሆነች። ይሄም በጉዳዩ ያልተስማሙ የኤርትራ ነፃ አውጭ አካላትን ፈጠረ። ከዚህ በኃላ የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግስት ነፍጥ ካነሱ የኤርትራ አማጥያን ጋር ወደ ውጊያ ገባ። ይሄም ጦርነት የኃይለስላሴ መንግስት በደርግ ሲተካም በውርስ ቀጠለ እንጂ አልቆመም። በዚህ ጊዜ ደርግ እነዚህን አማፅያን በአግባቡ አናግሮ የቀድሞ የተባበሩት መንግስታት የወሰነላቸውን የፌዴሬሽን መንግስትነት መብታቸውን በመመለስ መፍታት ሲችል በግትርነት ጦርነቱን አስቀጠለው።

~ ይህ ጦርነት ለብዙ አመታት ቀጥሎ የኤርትራ ነፃ አውጭዎች የኤርትራዊያን ጥያቄ ተገቢና የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው ብለው ከሚያምኑት ደርግን ከሚዋጉት ጋር በመተባበር ደርግን በኃይል ወግተው ጣሉት። ደርግ ከወደቀ በኃላ የኢትዮጵያን የወደብ እና የባህር በር ጥያቄ ያላነሳ፣ ጥያቄውን ማንሳት ያልፈቀደ ኃይል የኢትዮጵያን መንግስት (TPLF) ተረክቦ እየመራ የወደብና የባህር በር ጥያቄው እንዳይነሳ ከልክሎ የኤርትራን ነፃነት እወቁልኝ የሚል ደብዳቤ ለተባበሩት መንግስታት ጽፎ ኢትዮጵያን የባህር በር አልባና ወደብ አልባ አደረገ።

~ የኢትዮጵያ የባህር በር እና የወደብ አልባነት ታሪክ በትቂቱ ይሄንን ይመስላል። ኢትዮጵያ ወደ የቆየው ታሪኳ ወደ ገናናው የአክሱም ዘመን ብንመለከት በቀይ ባህር የባህር በሯ በወደቦቿ፣ በመርከቢቿ ገናና የነበረች የባህር በር ታሪካዊ ባለቤት እና ሰፊ ቁርኝት ያላት እንደሆነች እንረዳለን። ታዲያ ኢትዮጵያን ከዚህ ታሪኳ መነጠል ፍፁም ተገቢ ነው ሊባል ይቻላል? አልነበረም አይደለም።

~ አንድ ቀላል ጥያቄ አለ:: ሻቪያና ህወሓት የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው፣ ኢትዮጵያም ቅኝ ገዥ ሀገር ነች፣ ብለው ያምናሉ፣ በዚህ ካመኑ ዓለም አቀፍ ህጉ አፍሪካ እና የአፍሪካ ሀገሮች አሁን ያላቸውን የፖለቲካ ካርታ ቅርፅ የያዙት ቅኝ ገዥዎቻቸው በአወጡላቸው ድንበር ነው፣ ሀገራት ወሰን እንዲሆኑ የሚፈቅደው፣ ታዲያ አሰብ ከኤርትራ የተለየ አሰብ ራስ ገዝ ተብሎ ነበር በቅኝ ገዥዋ ኢትዮጵያ የሚተዳደረው፣ ታዲያ እንዴት የኤርትራ አካል እንዲሆን ተፈቀደ? ለሚለው መመለስ ነበረባቸው።

~ በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምም ሆነ፣ ብሔራዊ ክብር ግድ በሌለው ተገንጣይ የነፃ አውጭ ቡድን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ተላልፊ ነው የተሰጠው። ስለዚህ የኢትዮጵያ የወደብ እና የባህር በር ጥያቄ ከትውልድ ትውልድ እየቆየም ቢሆን መነሳቱ አይቀርም።

~ አሁን አሰብ እየተጎሳቆለች ወደ ኃላ እየሄደ፣ ኢትዮጵያ ስንትና ስንት ኢንቨስት ማድረግ ሲገባት በአመት $1.5 ቢሊዮን ለጅቡቲ ለወደብ ትከፍላለች። ይህ ገንዘብ አሰብ ላይ ኢንቨስት ቢደረግ በአካባቢው ላይ የሚያሳየውን ለውጥ አስባችሁታል። ይህ እኮ የኢትዮጵያ ጥያቄ ብቻ አይደለም፣ የአሰብም ጭምር እንጂ የኢትዮጵያም ብቻ አይደለንም።

~ይሄም ሁኖ ይሄንን ክፍተት በመጠቀም፣ የኦህዴድ ኦነግ ብልፅግና ፋሽስታዊ መንግስት ወደብ ለማስመለስ በሚል በኤርትራ ላይ የሚከፈት ጦርነት የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስጠብቅ ሳይሆን ኢትዮጵያዊያንን የሚያስጨርስ እና የኢትዮጵያን ሃብት የሚያስወድም ነው ሚሆነው። ኢትዮጵያ ያለ ምንም ጦርነት የባህር በርና የወደብ ጥያቄዋን በአግባቡ ለውይይት ለድርድር አላቀረበችም እንጂ ብታቀርብ ይሄን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብር መንግስት ቢይዘው፣ ያላንዳች ጥይት በሰላማዊ መንገድ ሊፈታ የሚችል ነው ብየ አምናለሁ።

 

Debru negash (MD)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.