Breaking News
Home / Amharic / የአዲስ አበባ ጉዳይ በጣም ያስፈራል። አንብቡና ለዘመዳችሁ ንገሩ !

የአዲስ አበባ ጉዳይ በጣም ያስፈራል። አንብቡና ለዘመዳችሁ ንገሩ !

ሰላም ባይኖርም ሰላም ልበላችሁ ውድ አንባቢያን

ነገሩ የተፈጸመው ቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 2012ዓ.ም ነው፡፡ ጀሞ ሁለት በሚባለው አካባቢ  አንዲት አነስተኛ ቡና ቤት ውስጥ የተከሰተ አስፀያፊ ድርጊት ነው፡፡ ባለቡና ቤቷ ለስምንት ዓመታት በሥራ ፍለጋ ያለምንም ሥራ ስትንከራተት ቆይታ አክስት አጎቶቿ ተባብረው አንዲት ቡና ቤት ይከፍቱላታል፡፡ በዚያ መተዳደር ከጀመረች ጥቂት ወራት አለፉ፡፡

ባለፈው ቅዳሜ እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ እንዲህ ሆነ፡፡ የሠፈር ሰዎች በቡና ቤቷ ደጃፍ ላይ ቁጭ ብለው ይዝናናሉ፡፡ የሚናገሩት በአማርኛ ነው፡፡ በአጋጣሚ ደግሞ የተከፈተው ዘፈን ተራው ሆኖ አማርኛ ነው፤ ቡና ቤቶች ዘፈን እያፈራረቁ ነው የሚያዘፍኑት – በባለጊዜዎች/ተረኞች ካልተገደዱ በስተቀር፡፡ ያኔ ያካባቢው ቄሮዎች ይሰባሰቡና “ሆ!” እያሉ መጥተው “ናፍጠኞታ! ናፍጠኞታ!” በማለት ቡና ቤቱን በድንጋይ ሩምታ ያደበላልቁታል፡፡ እንዲህ ያደረጉት ሴትዮዋ አማራ መስላቸው ነው፡፡ እርሷ ግን በጊዜው አነጋገር ትግሬ ናት፡፡ በትግሬነቷ ግን አልተጠቀመችም እንደመረጃ ምንጬ፡፡

ዕብዶቹ በድንጋይ ቡና ቤቱን ማተረማመስ እንደጀመሩ ሴትዮዋ ደምበኞቿን ገፋፍታ በጓሮ በር አስወጣችና የሚሆነውን ለማየት ቤቷ ውስጥ በድንጋጤ ፈዝዛ ቁጭ አለች፡፡ እነዚያ ቄሮዎች በኦሮምኛ አማራን እየተሳደቡና እየተራገሙ ፍሪጁን፣ በርና መስኮቶችን፣ በቤት ውስጥና በግቢው ውስጥ ያለውን ዕቃ በሙሉ ሰባብረውና የዘረፉትንም ዘርፈው ወደመጡበት ተመለሱ፡፡ አንድም ገላጋይ አልነበረም፡፡ ሁሉም ለባለጊዜዎቹ ያጎበደደ ወይም በፍርሀት የራደ ነውና፡፡

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.