Breaking News
Home / Amharic / የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት “ባልደራስ” ከአርባ ምንጭ ከተማ ህዝብ ጋር ለመመካከር ማቀዱ ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት “ባልደራስ” ከአርባ ምንጭ ከተማ ህዝብ ጋር ለመመካከር ማቀዱ ተገለፀ፡፡

በጋዜጠኛ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ የሚመራው የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት “ባልደራስ” ከአርባ ምንጭ ከተማ ህዝብ ጋር ለመመካከር ማቀዱ ተገለፀ፡፡

ለጂ ኤም ኤን የደረሰው መረጃ እንደሚጠቁመው “ባልደራስ” የፊታችን ሰኔ 16/2011ዓ.ም በባህርዳር ከተማ የሚያደርገውን የውይይት መድረክ ካጠናቀቀ በኋላ ሁለተኛ የክልል ቆይታውን በአርባ ምንጭ ለማድረግ አቅዷል፡፡

የባልደራሱን የአርባ ምንጭ ጉብኝት የሚያመቻች ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ጂ ኤም ኤን የተረዳ ሲሆን የመድረኩ ዋንኛ ዓላማ የአዲስ አበባ ጉዳይ የሁሉም ኢትዮጵያዊ መሆኑን ለማስገንዘብ ነው ተብሏል፡፡

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.