Breaking News
Home / Amharic / የአሜሪካ ዜግነቱን በራሱ ፈቃድ ለመተው የፈለገ ግለሰብ…

የአሜሪካ ዜግነቱን በራሱ ፈቃድ ለመተው የፈለገ ግለሰብ…

የአሜሪካ ዜግነቱን በራሱ ፈቃድ ለመተው የፈለገ ግለሰብ ማድረግ ያለበት…

የሌላ ሀገር ዜግነት ለማግኘት ያመለከተበት ማስረጃ ማቅረብ
አሜሪካ ኤምባሲ በአካል በመገኘት ማመልከት
በአሜሪካ መንግሥት የተዘጋጁ ቅጾች መሙላት
የመጨረሻ ዓመት የታክስ ቅፅ መሙላት
ያለፉት አምስት ዓመታት ግብር ታክስ የሞላ መሆን
የፋይናንስ ወንጀሎች ማስከበሪያ መረብ ወይም Financial Crimes Enforcement Network በኩል የ Foreign Bank and Financial Account ፎርም 114 መሙላት
ለቃለመጠይቅ ቀጠሮ ማስያዝ
በተለያዩ ቀናት የሚደረጉ ሁለት ቃለመጠይቆች ላይ መገኘት
ዜግነቱን መተው መወሰኑን በቃለ መሃላ መግለጽ አለበት

ከዚያ ኤምባሲው ቅጾችን እና ቃለመሃላውን አያይዞ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ይልካል። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ሰነዶቹን ከመረመረ እና ግለሰቡ በታክስ ክፍያ እና ሌሎች ወንጀሎች በአሜሪካ መንግሥት የማይፈልግ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ዜግነቱን ማጣቱን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት 👉Certificate of Loss of Nationality (CLA) DS-4083👈 እንዲሰጠው ውሳኔ ያስተላልፋል ። ውሳኔውንም ለኤምባሲው መልሶ ሲልክ ግለሰቡ ሰርተፊኬት ያገኛል። አሁን ባለው አሰራር የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ሰርተፊኬቱን ለማጽደቅ 5 ወራት ጊዜ ይፈልጋል ። ስለዚህም ዜግነት የማጣት ሂደቱ ተጀምሮ እስኪያልቅ ከፈጠነ 6 ወራት የሚፈልግ እንደሚሆን ይገመታል። በአንዳንድ ሃገሮች እስከ 15 ወራት እንደሚፈጅ ይታወቃል። የአሜሪካ ዜግነቱን በፈቃዱ የሚተው ግለሰብ በአሜሪካ የመኖር እና የመስራት መብትን ወዲያውኑ ያጣል።በፈቃዱ የተወ ግለሰብ እንደገና ተመልሶ የአሜሪካ ዜግነትን ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ነው ፣ ይሁንና የመስሪያ ፈቃድ ለማግኘት እንደማንኛውም የውጭ ሀገር አመልካች ማመልከት እና መጠበቅ ይችላል ።

Support Amhara Movement

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.