Breaking News
Home / Amharic / የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ማዋቀሩን አስታወቀ

የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ማዋቀሩን አስታወቀ

#ሰበር_ዜና

የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ማዋቀሩን አስታወቀ 🔥🔥🔥🔥

የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት በአምስት መስራች ድርጅቶች ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ከተቋቋመና ሊቀመንበሩን ከመረጠ በኋላ፣ ብዛት ያላቸውን አመራሮች ለመምረጥ ተከታታይ ስብሰባዎችን ሲያደርግ ቆይቷል። ከሚፈለጉት አመራሮች ብዛት አኳያ ተጨማሪ ጊዜ አስፈላጊ ሆኖ የተገኘ ቢሆንም ለህዝብ ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ሐምሌ 26/2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በመጀመሪያ ዙር ምደባው የሚከተሉትን አርበኞች በስራ
አስፈፃሚነት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

📌 1ኛ. ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር፦ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ

📌 2ኛ. ምክትል ሊቀመንበር እና ወታደራዊ አዛዥ፦ ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሀባ

📌 3ኛ. ምክትል ሊቀመንበር እና የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ፦ አርበኛ መከታው ማሞ

📌 4ኛ. ምክትል ሊቀመንበር እና የፋይናንስና አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ፦ ኮነሬል ታደሰ እሸቴ

📌 5ኛ. የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ፦ አርበኛ ረ/ፕሮፌሰር ጌታ አስራደ

📌 6ኛ. የመረጃ እና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ፦ አርበኛ መስፍን አባተ

📌 7ኛ. የድርጅት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ፦ አርበኛ ደረጀ በላይ
8ኛ. የውጭ ጉዳይ እና ዲያስፖራ ጉዳዮች ኃላፊ፦ አርበኛ ማስረሻ ሰጤ

📌 9ኛ. የፅህፈት ቤት ኃላፊ፦ አርበኛ መምህር ምንተስኖት ወንድአፈረ

በቀጣይነትም፣ ቀሪዎቹ የስራአስፈፃሚ እና የአመራር ምደባዎች ተጠናቀው ለህዝብ ይፋ ይሆናሉ።

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.