Breaking News
Home / News / የአማራ ጥያቄ

የአማራ ጥያቄ

መንግስት እውነት አለ ከተባለ ለፌደራል መንግስቱ የምንጠይቀው ቢኖር፦
1) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ፣ የመከላከያ ሚኒስትሯና ኢታማዦር ሹሙ በተፈጠረው ጉዳይ ላይ ግልፅ ማብራሪያ እንዲሰጡን እንጠይቃለን።

2) የመከላከያ ሰራዊት በንፁኃን አማራዎች ላይ ግድያ እንዲፈፀም ትዕዛዝ የሰጡ አመራሮችና ወንጀሉን የፈፀሙ የሰራዊቱ አባላት በሕግ እንዲጠየቁ ይጠይቃል። በንፁኃን ዜጎች ላይ ለደረሰው ግድያም መንግስት ይቅርታ እንዲጠይቅና ለተጎጂ ቤተሰቦችም ካሳ እንዲከፍል እንጠይቃለን።

3) የመከላከያ ሰራዊት የክልሉ መንግስት ባልጠየቀበት ሁኔታ በተራ የደንብ ማስከበር ሥራ ከመሰማራት ተቆጥቦ ወደ ካምፑ እንዲሰባሰብና ሰላማዊ ሕዝብን ከማሸበር ድርጊቱም እንዲቆጠብ እንጠይቃለን።

4) የክልሉ መንግስት በተለይም የአማራ የፀጥታ ኃይሎች በሰላማዊ ሕዝባችን ላይ ከማናቸውም አካል የሚቃጣን ጥቃት እንዲከላከሉ እንጠይቃለን።

5) መላው አማራ ከተጎጂ ወገኖች ጋር እንዲሆንና ከመቼውም በላይ አንድነቱን እንዲያፀና፤ ራሱን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብቱንም እንዲያስከብር እንጠይቃለን።

ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ሀገረ ኢትዮጲያ የተለያዩ ትንንሽ ሀገር እንደሆነችና እኛም የራሳችን የሆነች ትንሽ አማራ የተባለች አገር ለመመስረት እንገደዳለን።

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.