Breaking News
Home / Amharic / የአማራ ክልል ምክር ቤት ይልቃል ከፋለን (ዶ.ር) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አድርጎ መርጧል፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት ይልቃል ከፋለን (ዶ.ር) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አድርጎ መርጧል፡፡

“ዓላማችን ወራሪውን ቡድን አቁስሎ መተው ብቻ ሳይሆን ዳግም የሀገራችን ስጋት እንዳይሆን ማስወገድ ብቻ ነው” የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)
ባሕር ዳር፡ መስከረም 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛ መሥራች ጉባኤው እየተካሄደ ያለው የአማራ ክልል ምክር ቤት ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አድርጎ መርጧል፡፡ አዲሱ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ክልሉን ወደ መምራት የመጡበት የአሁኑ ወቅት በርካታ ፈተናዎች ያሉበት በተለይም የሽብርተኛው ትህነግን አከርካሪ በመስበር ሕዝብን ከመከራ መታደግ የሚጠይቅበት ወቅት በመሆኑ ለዚህ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የሽብርተኛው ትህነግን ወረራ ለመመከት የህልውና ዘመቻ ታውጆ በሁሉም ዘርፍ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ያነሱት ርእሰ መሥተዳድሩ አሸባሪውና ወራሪውን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ እና የሌሎች ክልሎች ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ፣ ፋኖ እና ሕዝቡ በጀግንነት እየተፋለሙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ወረራውን መግታት እና አንዳንድ አካባቢዎችን ከሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን ነጻ ማውጣት መቻሉን አንስተዋል፡፡ የተቀሩትንም አካባቢዎች በአጭር ጊዜ ነጻ እንደሚወጡ ገልጸዋል፡፡ ሕዝቡ በጀግንነት እና በአንድነት በግንባር ሕልውናውን ለማስከበር ጀብዱ እየፈጸመ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
“ዓላማችን ወራሪውን ቡድን አቁስሎ መተው ብቻ ሳይሆን ዳግም የሀገራችን ስጋት እንዳይሆን ማስወገድ ብቻ ነው” ብለዋል ዶክተር ይልቃል፡፡
የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን የሕዝብን ተስፋ የማጨለም ዓላማ እንደማይሳካ ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡-አዳሙ ሽባባው እና ቡሩክ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.