Breaking News
Home / Amharic / የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የኮምቦልቻ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ከደጋፊዎች የቢሮ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገለት

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የኮምቦልቻ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ከደጋፊዎች የቢሮ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገለት

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የኮምቦልቻ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከደጋፊዎች የቢሮ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገለት፡፡ ወደ ጽ/ቤቱ በሚመጡበት ወቅት የቢሮ ቁሳቁስ እጥረት እንደላ የተመለከቱት የንቅናቄው ደጋፊ አቶ ሠውነት ታደሠ ኮምፒውተርና ፕሪንተር ገዝተው ትላንት ነሀሴ 21 ቀን 2011 ዓ/ም ጽ/ቤታችን በአካል በመገኘት አስረክበዋል፡፡ ለደጋፊው ልባዊ ምስጋና ያቀረቡት ሊቀመንበሯ ኢንጅኔር ዘሀራ ሰኢድ አያይዘውም << የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ለማሳለጥና አብን አንግቦት የተነሳውን የአማራ ህዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች ፤ በዴሞክራሲያዊ ትግል ለማስመለስ ፤ ሁሉም አማራ ሊረባረብና ንቅናቄአችንን ሊደግፍ ይገባል! >> ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

.

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፣ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.