Breaking News
Home / Amharic / የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አመራሮች ከአሜሪካው ብሔራዊ የዴሞክራሲ አመራሮች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረጉ፤

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አመራሮች ከአሜሪካው ብሔራዊ የዴሞክራሲ አመራሮች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረጉ፤

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከፍተኛ አመራሮች ከአሜሪካው ብሔራዊ የዴሞክራሲ ተቋም አመራሮች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረጉ፤
***
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ከፍተኛ አመራሮች ከአሜሪካው ብሔራዊ የዴሞክራሲ ተቋም (National Democratic Institute – NDI) አመራሮች ጋር በምርጫ 2012፣ በወቅታዊ የአማራና የኢትዮጵያ ፓለቲካ ሁኔታ እና ከተቋሙ ለፓለቲካ ፓርቲዎች ማጠናከሪያ ስለሚገኙ ድጋፎች በተመለከተ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም አብን የተመሰረተበትን ዓላማና ማሳካት ስለሚፈልጋቸው ግቦች፣ በአንድ አመት ከአምስት ወር ጊዜ ወስጥ ስላደረጋቸው አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ለቀጣይ ምርጫ እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶችን እንዲሁም አብን ከተቋሙ ለቀጣዩ ምርጫ የሚፈልጋቸውን ድጋፎች በተመለከተ በአብን አመራሮች ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የተቋሙ አመራሮች በበኩላቸው ከ50 በላይ በሆኑ የአለም አገሮች ተቋሙ ስለሚያከናውናቸው ድጋፎችና በኢትዮጵያም ለቀጣዩ ምርጫ ማከናወን ስላቀዳቸው ተግባራት እንዲሁም ለአብን ሊያደረጉ በሚችሉት ድጋፎች ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል።

በዚህም ተቋሙ በቀጣይ ለአብን የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግ የገለፀ ሲሆን በትብብር መስራት የሚቻልባቸውን መስኮች በመለየት ውይይቱ ተጠናቋል።

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.