Breaking News
Home / Documents / የአማራ ሕዝባዊ ኃይል – ጥብቅ መረጃ

የአማራ ሕዝባዊ ኃይል – ጥብቅ መረጃ

ጥብቅ መረጃ፣ በ Ermias Legesse Wakjira

ይሄ ከታች ያስቀመጥኩትን ውይይት ካደረግን በኋላ “የአማራ ሕዝባዊ ኃይል” የሚያደራጁ አመራሮችን አግኝተናል። አናግረናቸዋል። የጠየቅነውን ጥያቄዎች ግልጽ ምላሽ ሰጥተውናል። ከታች የዘረዘርኩት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
#1ኛ፡- የአማራ ሕዝባዊ ኃይል በየትኛውም የብልፅግና መንግስት መራሽ እዝ ሰንሰለት ውስጥ ለመግባት ስምምነት እንዳልደረሰ ነግረውናል።
#2ኛ፡- የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ከመንግስት የሎጅስቲክ ድጋፍ እንዲደረግለት ከመጠየቅ በስተቀር በእጁ ያለውን የሰው ኃይልም ሆነ ሎጅስቲክ ለማስመዝገባና በመንግስት ጠገግ ውስጥ ለመግባት ስምምነት ላይ አልደረሰም።
#3ኛ፡- “በአማራ ሕዝባዊ ኃይል” እና በብልጽግና ፓርቲ መካከል ያለው ግንኙነት መተማመን የሌለበት በጥርጣሬ የተሞላና መደጋገፍ ያለበት አይደለም። ቁንጮ ላይ የተቀመጡ የብልፅግና መሪዎች “ከዘመነ ካሴ ወይንስ ከደብረጺዬን ጋር ብትነጋገሩ ትመርጣላችሁ?” ተብለው ቢጠየቁ ደብረፂዮንን እንደሚመርጡ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል አመራሮች ያምናሉ። ቃል በቃል የነገሩንም ይህንን ነው።
#4ኛ፡- የአማራ ሕዝባዊ ኃይል አመራሮች አቶ ዬሃንስ ቦያለው፣ ጌትነት አለሙ (ፒ.ኤች.ዲ.) ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና አቶ ነዓምን ዘለቀ ሕዝባዊ ኃይሉን ለማፍረስና እነ ዘመነ ካሴ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ከጀርባ ከሚሰሩት ሴራ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.