Breaking News
Home / Amharic / የአማራ ህዝብ ያለውን ሁለገብ ትግል የሚደግፍ ንቅናቄ ተቋቋመ !

የአማራ ህዝብ ያለውን ሁለገብ ትግል የሚደግፍ ንቅናቄ ተቋቋመ !

የአማራ ህዝብ ለህልውናው ለፍትህና ለዴሞክራሲ እያደረገ ያለውን ሁለገብ ትግል የሚደግፍ ንቅናቄ ተቋቋመ::

የአማራ ፋኖ እያደረገ የሚገኘውን ፍትሃዊ ትግል ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እና ህዝብን አደራጅቶና አቀናጅቶ መምራት አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት የአማራ ልጆች በአንድነትና በፅናት በመቆም
ፋኖ ለህልውና ለፍትህና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ (ፋ.ህ.ፍ.ዴ.ን.) የተሰኘ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ማቋቋማቸዉን በዛሬዉ ዕለት ባወጡት መግለጫ አስታዉቀዋል።
ንቅናቄዉ በመግለጫዉ ወደ ሁለገብ ትግል ለመግባት ተገደናል ያለ ሲሆን በመላው ዓለም የሚኖሩ ወገኖችም በሚያስፈልገው ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉላቸው አፅንኦት ሰተዋል።
ፋኖ ለህልውና ለፍትህና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ የተሰኘዉ ህዝባዊ አደረጃጀት በግልፅ በተቀመጠ አላማና ራዕይ የሚመራና በአባላቱ ፀድቆ ስራ ላይ በዋለ ድርጅታዊ መተዳደሪያ ደንብና መዋቅር የሚተዳደር የአማራ
ህዝብ ንቅናቄ መሆኑ በመግለጫዉ ተገልጿል።
የአደረጃጀቱ አላማም በመንግስታዊ ስርዓትና በመዋቅር ተደግፎ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመበት ከሚገኘው ይፋዊ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ጥቃት አማራንና አማራነትን መከላከልና ማዳን፣ የአማራን ህዝብ የሃገር
ባለቤትነቱን፣ የዜግነት መብቱንና፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ፣ ለአማራ ህዝብ እድሜ ጠገብ የማንነት፣ የእኩልነትና፣ የዴሞክራሲ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት፣ በአማራ ህዝብ ላይ ለተፈጸሙ ወንጀሎችና ጥቃቶች
ወንጀለኞችን በህግ ፊት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግና ለህዝባችን ፍትህ እንዲበየን ማስቻል ነዉ ሲል አስታዉቋል።
ንቅናቄዉ የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን አደጋ ለመቀልበስ እና ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች፣ ለመላው የአማራ ህዝብ፣ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና ለሁሉም የጸጥታ አካላት እና ለፖለቲካ
ድርጅቶች፣ ለሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ ለሲቪክ ተቋማት፣ ለመላው የኢትዮጵያ ምሁራን፣ ለሀገር ተረካቢ ወጣቶች፣ ለሐይማኖት አባቶች፣ በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንዲሁም ለጎረቤት ሀገራትና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የትግል ጥሪውን አቅርቧል።
 
ሻለቃ ውብአንተ አባተ (የወታደራዊ ክንፍ መሪ)
ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋሁን አትንኩት (የፓለቲካ ክንፍ መሪ)
ረ.ፕሮፌሰር እያሱ አባተ (ሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ)
አብዩ በለው (የውጭ ክንፍ ሰብሳቢ)
 

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.