Breaking News
Home / Amharic / የኖቤል ሽልማት ከተሰጠ ቦሀላ ሰላማዊ ሰልፉ አንዲካሄድ ዶር አቢይ ፈቀደ::

የኖቤል ሽልማት ከተሰጠ ቦሀላ ሰላማዊ ሰልፉ አንዲካሄድ ዶር አቢይ ፈቀደ::

በአስክንደር ነጋ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፉ አንዲካሄድ ዶር አቢይ ፈቀደ።

“የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እሁድ ለሚደረገው ሰልፍ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አደረገ።
የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) ከነገ በስቲያ እሁድ ጥቅምት 2 የጠራውን ሰልፍ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ የሆኑት አቶ ጌቱ አርጋው ለአሃዱ ኤፍ ኤም ገለፁ።
ተጀምሮ እስከሚጠናቀቁ ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ሰልፉ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችንም ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት፦ ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ፣ ከብሄራዊ ትያትር ወደ መስቀል አደባባይ፣ መሿለኪያ፣ ከውጭ ጉዳይ እስጢፋኖስ ፣ መስቀል ፍላወር እስከ ደምበል ሲቲ ሴንተር፣ ከኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ ወደ ሰልፉ ስፍራ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት 991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና
0111 -11- 01-11፣
0111- 26- 43- 59፣
0111- 01- 02- 97፣ መጠቀም የሚችል መሆኑን ኮሚሽኑ አስታቋል።”

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.