Breaking News
Home / Amharic / የታመነ አስደንጋጭ ሰበር ዜና የኦሮሞ ታጣቂዎች ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሚገኝበትን…..

የታመነ አስደንጋጭ ሰበር ዜና የኦሮሞ ታጣቂዎች ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሚገኝበትን…..

የታመነ አስደንጋጭ ሰበር ዜና የኦሮሞ ታጣቂዎች ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሚገኝበትን ጉባ ወረዳ ዙሪያ መክበባቸው ተጋለጠ:: ከኦሮሚያ ክልል የተነሱ ሸኔ እና ሌሎችም ታጣቂ ኃይላት በእነ ዓብይ እና ሽመልስ የግዛት ማስፋፋት ሴራ ይሁንታ ተሰጥቷቸው ባለፉት ወራት ኦሮሚያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሰሜን እና ደቡብ ሱዳን ጋር እንድትዋሰን በተነደፈው የሴራ እቅድ መሰረት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሶስት ወረዳዎች ካማሼ ማኦኮሞ እና አሶሳ ዙሪያ ተቆጣጥረው የክልሉን መዋቅር በማፍረስና ነዋሪውን በማፈናቀል የራሳቸውን የኦሮሚያ አስተዳደር አደረጃጀት መዘርጋታቸው ተጋልጦ ነበር::

በሁለቱም ሱዳን እና በአፋር የኢትዮጵያን ዋና የድንበር ንግድ መተላለፊያ መስመሮች በኃይል ወሮ ወደ ኦሮሚያ በማጠቃለል ኢትዮጵያ የምትባለውን ሃገር ጉሮሮዋን ዘግቶ በዕቅዳቸው መሰረት ለመበታተን የጀመሩትን እንቅስቃሴ ለማሳካት ለሕዝባችን የብሄር እና የሃይማኖት ግጭቶችን, የንሮ ውድነት , የነዋሪውን መኖሪያ ቤት ዘር ተኮር በሆነ መልኩ በተደራጀ ሁኔታ ማፍረስ እና ሌላም የተለያየ አጀንዳ በመስጠት ማህበረሰቡ በዛ ጉዳይ ላይ ሲራኮት እነሱ እጅግ በሚያስፈራ ሁኔታ አጎራባች ክልሎችን በመውረር ለወደፊት እንደ ሃገር ሲገነጠሉ የሚጠቅማቸውን መሬት በሁሉ “የእኛ ኬኛ” መርሃቸው መሰረት በኃይል በመውረር የግዛት ማስፋፋቱን ቀጥለውበታል::

አሁንም በሚያስፈራ ሁኔታ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ዕድገት ተስፋ የተጣለበትን እና መላው ኢትዮጵያዊ ያለውጭ ዕርዳታ ላቡን አንጠፍጥፎ በገንዘቡ የገነባውን ታላቁ የህዳሴ ግድብ ወደ ኦሮሚያ ክልል ለማጠቃለል ታጣቂ ኃይሎቹ ያለ ከልካይ መስፋፋታቸውን ቀጥለው ግድቡ የሚገኝበትን ጉባ ወረዳ ዙሪያ እየተቆጣጠሩ እንደሚገኝ ታውቋል:: ከአካባቢው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች እንደገለጹት በአሁኑ ሰዓት ጽንፈኛ ተስፋፊዎቹ በመተከል ስር በሚገኘው ጉባ ወረዳ አዋሳኝ በሆኑ ሲርብ ዓባይና ኦዳቡልዱጉል ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የቤኒሻንጉል ክልል መንግሥት መዋቅርን አፈራርሰው የራሳቸውን አደረጃጀት ፈጥረዋል::

በሌላ በኩል ታላቁ የህዳሴ ግድብ በሚገኝበት ጉባ ቅርብ በሆነው ሸርቆሌ ወረዳ ልዩ ስሙ አውልቤጎ በተባለ አካባቢ ግድቡን ለማስፋፋት በሚካሄደው የደን ምንጣሮ ስራ ከተሰማሩ የጉልበት ሰራተኞች ዓማራዎች እና የሌላ ብሄር ተወላጆች እንዲባረሩ ሲደረግ ስራውን ሙሉ ለሙሉ የኦሮሞ ተወላጆች ብቻ እንዲቆጣጠሩት ተደርጓል:: ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወያኔ የአካባቢውን የወርቅ እና ሌላም የተፈጥሮ ኃብት ለመቀራመትና ታላቋን ትግራይ ሲመሰርትም አብሮ ገንጥሎ ወደ ክልሉ ለማጠቃለል እ.ኤ.አ በ 1991 ዓ.ም ከምዕራባዊ ጎጃም መተከልንና የአባይ ተፋሰስ የሚያዋስኑ ሰፊ ግዛትችን በኃይል ከዓማራው አጽመ ርስት ቀምቶ የተመሰረተው አዲስ ክልል ሲሆን “ዓማራ ከሚለማ ሱዳን ይልማ የሚል” ሰይጣናዊ እሳቤ የተጠናወተው ሕውሃት እጅግ ከፍተኛ በቢልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከስክሶ የአባይን የውሃ ፍሰት አቅጣጫ በቁፋሮ ከአማራ ክልል ወደ ቤኒሻንጉል ጉባ ወረዳ አቅጣጫ በማስቀየር እንደገነባው ይታወሳል::

ወያኔ ላለፉት 18 ዓመታት በአካባቢው በርካታ ትግራዋይን ከአፍሪካ ልማት ባንክና ከመንግስት ባንኮች በህገወጥ መልኩ ገንዘብ እንዲያገኙ በማድረግ በቤኒሻንጉል በእርሻ ልማት እና ማዕድን ቁፋሮ ተሰማርተው አካባቢውን እንዲበዘብዙ ሲያደርግ ቆይቷል:: ግድቡ ከፍተኛ ቁጥር ላላቸው ተጨማሪ የአፍሪካ ሃገራት ሊሸጥ ካሰበው የኤሌክትሪክ ኃይል ሌላ ውሃው ከፍተኛ የዓሳ ሃብት ልማት ምንጭና የቱሪስት መስብ ሆኖ ከፍተኛ ገቢ እንደሚያመጣ ይታመናል::

የሚያሳዝነው የኦሮሙማው ተስፋፊ ቡድን የቀድሞን የጎጃም ዓማራ ምድር መተከልና አካባቢውን እንዲሁም ግድቡን በመቆጣጠር ኢትዮጵያ እንደ ኬንያ ሰሜን እና ደቡብ ሱዳኖች ጅቡቲና ለሌሎችም የአፍሪካ ሃገራት በዶላር መሸጥ የጀመረችውን ሃብት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ 60 በመቶ በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል አጥቶ በጨለማ ይኖራል እየተባለ በሚነገርበት በአሁኑ ሰዓት ወደ ኦሮሚያ ክልል የግድቡን ወረዳ ጠቅልሎ የሚያስገባበት ጊዜ እጅግ ቅርብ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው:: ለምሳሌ ገና ግድቡ ሳይጠናቀቅ ከ 4 ባነሱ ተርባይኖች ያመነጨውን ኃይል ለሱዳን እና ለጅቡቲ የሸጠው መንግስት አምና 32.7 ሚልዮን ዶላር ማግኘቱ ታውቋል:: እንደ ሶማሌ ላንድ እና ታንዛኒያ ያሉ ሃገራትም ኃይል ለመግዛት ከሃገራችን ጋር ተስማምተዋል:: አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ይህ የለየለት ተገንጣይና ጠላት መንግሥት ወደ ቀልቡ ይመለሳል በሚል ሃገሪቱ እስክትፈርስ በቸልታ እና በዝምታ መጠበቃቸው ያሳዝናል::

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.