Breaking News
Home / Amharic / የብ/ር ጀነራል አሳምነው ፅጌ ባለቤት ወይዘሮ ደስታ በማታውቀው ነገር ከ 2 ወር በላይ በጨለማ ቤት ታስራለች ::

የብ/ር ጀነራል አሳምነው ፅጌ ባለቤት ወይዘሮ ደስታ በማታውቀው ነገር ከ 2 ወር በላይ በጨለማ ቤት ታስራለች ::

ከግማሽ በላይ በኢትዮጵያ ፌድራሊስት ስርአት የካቢኒ ቦታ የያዛችሁ ሴቶች የሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንባ ጥበቃ ኮሚሽን፣ የፍትህ አካላት ሴት የአለም ልሂቃን ማሕበር ምን ሆናችሁ?

የብ/ር ጀነራል አሳምነው ፅጌ ባለቤት ወይዘሮ ደስታ ሰኔ15 ከተፈጠረው ክስተት ጋር በተያያዘ በማታውቀው ነገር በጨለማ ቤት ታስራ ምነዉ ቅሽሽ አለላችሁም?

ሴት ልጅን ማንገላታት አረመኔነት ነው ያዉም እርጉዝን ሴት በጨለማ ወህኒ ቤት አስሮ ማሰቃየት የለየለት ኢ-ሰብአዊ
ድርጊት መሆን ምነዉ ዘነጋችሁ?

ሴትዬዋ የተገኘባት ምንም አይነት ጥፋት የለምና
በአስቸኳይ ትፈታ በሉ እስኪ ክብርት ፕሬዝዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴና መአዛ አሸናፊ።
ፍትህ ለነፍሰ ጡሯ ደስታ አስፋው!

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.