Breaking News
Home / Amharic / የሱዳን መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች የእርሻ ልማት ካምፕ ዙሪያ ሰፍሯል።

የሱዳን መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች የእርሻ ልማት ካምፕ ዙሪያ ሰፍሯል።

ወሳኝ መረጃ!
የሱዳን መከላከያ ሰራዊት መጋቢት 20 ቀን 2012 ዓ.ም ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በኩል በመግባት ስናር በተባለ የኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች የእርሻ ልማት ካምፕ ዙሪያ ሰፍሯል።

ይህም የሆነበት ምክንያት፣ በዛሬ ዘገባው ዓሻርቅ አል-ዓውሳት (Asharq al-Awsat) የሚባለው ለንደን እንግሊዝ በዓረብኛ ቋንቋ የሚታተም ጋዜጣ እንዲህ ይገልጸዋል፣ 👉የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የነበረውን ለም የእርሻ መሬት ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት መስማማቱንና፣ በሱዳኖች አጠራር “አልፋሽቃ” የሚባለው ይሄ በኢትዮጵያ ቁጥጥር ስር የነበረው መሬት በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ወደ ሱዳን እንደሚመለስ ጋዜጣው አስረድቷል፡፡ በውይይቱ ኢትዮጵያን ወክለው የተሳተፉት ኢታማዦር ሹም አደም መሐመድ መሆናቸውንም አክሎ ዘግቧል፡፡

በነገራችን ላይ ይሄን ለም የእርሻ መሬት ለሱዳን በፊርማቸው አሳልፈው ለመስጠት የተስማሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮነን ናቸው፡፡

ፋኖን ለመምታት የተፈለገበትም አንደኛው ምክንያት፣ ፋኖ የአማራን መሬት ለማስመለስ እርምጃ እንዳይወስድ ተሰግቶ ይመስላል።

ዝርዝር መረጃውን ማንበብ ለምትፈልጉ ሊንኩ እዚህ አለላችሁ

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.