Breaking News
Home / Amharic / ወልቃይት የማነው? ራስ መንገሻ ስዩም

ወልቃይት የማነው? ራስ መንገሻ ስዩም

ክቡር ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም የአፄ ዮሐንስ የልጅ ልጅ ልጅ ናቸው (አራተኛ ትውልድ)፡፡ በኢትዮጵያ በመንግሥት ሥራ በተለያዩ ቦታዎች ያገለገሉ ሲሆኑ፣ የትግራይ ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ (አገረ ገዥ) ሆነው ሠርተዋል፡፡
በትግራይ በጣም ተወዳጅ የነበሩ ታታሪ ሰው መሆናቸውን ሁሉም ምስክርነት የሚሠጠው ነገር ነው፡፡ የትግራይ ሰው “ልዑል ጌታችን” ብለው ነው የሚጠሯቸው፡፡

በቅርቡ በ2010 (ኢትዮጵያ አቆጣጠር)፣ የትውልድ አደራ በተባለው መፅሐፋቸው በጣም ብዙ መነበብ የሚገባቸው መዘክሮች አስፍረውልናል፡፡ ከሀቅ የተነሱ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያሳየው፣
በወቅቱ የነበረውን የትግራይ ጠቅላይ ግዛትን ካርታ በመፅሐፋቸው ውስጥ ማቅረባቸው ነው፡፡ (ገፅ 130) በዚህ ካርታ፣ የትግራይ ጠቅላይ ግዛት በምዕራብ በኩል ከበጌምድር ጠቅላይ ግዛትና ከኤርትራ ጠቅላይ ግዛት የሚዋሰን ሲሆን፣
በዚህም የወልቃይት፣ ሁመራና አካባቢዎች በበጌምድር ጠቅላይ ግዛት እንጂ በትግራይ እንዳልነበሩ አስቀምጠዋል፡፡ የትግራይ ጠቅላይ ግዛት ከሱዳን ጋር የሚያዋስን ደንበር አልነበረውም፡፡ ዕድሜ ይስጣቸው፡፡

ይህ አሁን “ምዕራብ ትግራይ” የሚባለው ቦታ በትግራይ ውስጥ ሆኖም አያውቅም፡፡ ይህንን፣ እሳቸው ብቻ ሳይሆን ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች የሚያውቁት ነገር ነው፡፡ የይገባኛል ጥያቄው ታሪካዊም ህጋዊም አይደለም፡፡
የትግራይ ህዝብ በሰላም ከወንድሞቹ ጋር እንዳይኖር የዕድሜ ልክ ጦርነት ውስጥ እንዲገባ ለማድረግ ካልሆነ በስተቀር ይህን አካባቢ ማንም ተነስቶ ወዳልነበረበት ቦታ የሚቸረው ነገር አይደለም፡፡

የውጭ ሀይሎችም ቢሆን ይህንን ታሪክና ዕውነታ በትክክል ያውቁታል፡፡ በትግራይ ህዝብ ህይወትና መከራ የፖለቲካ ጥቅም ማስጠበቅ ተገቢ አይደለም፡፡ የትግራይ ህዝብም ቢሆን ይህንን ተረድቶ በሰላም አብሮ ወደመኖሩ መሄድ የበለጠ ይጠቅመዋል፡፡
አንኳን ያን ጊዜ አሁንም ቢሆን፣ የትግራይ ተወላጅ በሁመራና አካባቢው ሠርቶ እንዲኖር የከለከለው የለም፡፡ ለትግራይ ሕዝብ ቆሜልሃለሁ በሚሉ ሰዎችና ሀይሎች፣ ለትግራይ ደሀ ህዝብ ጠብ ያለ ነገር የለም፡፡ መከራ፣ እንግልትና ሞት ነው የተደገሰለት፡፡

በዚህ ሥራቸው፣ ልዑልነታቸው የትግራይን ህዝብ ከወደፊት መከራ ለማውጣት ውነቱን ተናግረዋል፡፡ ለትግራይ ሥልጣን ቀርቶ፣ ለኢትዮጵያ ዙፋን ከሳቸው በላይ የቀረበ ሰው የለም፡፡ የሚታወቁትም በኩሩ ትግራዊነታቸው ነው፡፡
የሳቸው አባት ልዑል ራስ ሥዩም የውጭ ሀይሎች ኢትዮጵያን ለመበታተን ያሴሩትን ሴራ ካስቆሙት ሀይሎች ዋናው እንደነበሩ ታሪክ ይዘከርላቸዋል፡፡ እሳቸውም የትግራይ ባላባት ነበሩ፡

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.