Breaking News
Home / Amharic / ከአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት ዛሬ የወጣው መግለጫ::

ከአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት ዛሬ የወጣው መግለጫ::

ፖሊስ የጥቅምት ሁለቱን ሰልፍ ስለመከልከሉ …….

የአዲስ አበባ ምክር ቤት ጥቅምት 2 2012 ዓ.ም የጠራውን ሰልፍ የአዲስ አበባ መስተዳድር በህጉ መሠረት በዝምታ ፍቃድ ከሰጠ ቦኃላ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥቅምት 1 2012 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ክልከላ አድርጎበታል።

ይህን አስመልክቶ ምክር ቤቱ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ፣ ምክር ቤቱ ቀደም ብሎ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት፣ለሀገሪቱ ሰላምና ለህዝቧ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ሰልፉን ሰርዟል።

የመንግስት ህገ ወጥ ክልከላ የዴሞክራሲ እና ፍትህ ቅልበሳውን አረጋግጧል። ስለዚህም፣ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደገለፀው፣ ሰላማዊ ትግሉን በሂደት ወደ ቀጣይ ምእራፍ ለማሸጋገር እንደሚገደድ በዚህ አጋጣሚ ይገልፃል።

የአዲስ አበባ ባላደራ ምክርቤት የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማሳካት ሲንቀሳቀሱ የታሰሩ በርካታ ወጣቶች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን።

በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ፣ እንዲሁም፣ በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ቀን ከሌሊት ያደረጋችሁት ልፋት ለዲሞክራሲ እና ፍትህ መምጣት የምትከፍሉት ዋጋ ቢሆንም፣ ባለ አደራ ምክር ቤቱ የላቀ ምስጋናውን እና አክብሮቱን ይገልፃል።

ፈጣሪ ህዝቧንና ኢትዮጵያን ይባርክ

የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት
አዲስ አበባ

Yotor Abysinia Ayzoh anbesaw kegonih nen….yegala teregninet keguzoachn ayagdenm.

Hewan Legesse Hero, the true Ethiopian son! Big respect!

Yotor New Abate This is the best way to achieve our mission and this was what Gandhi and Mandela did. Don’t forget, fighting enemy through positive action is the best weapon to fight ur enemy. More talk is expected from nulls. you are our hero and we are with you in every fractions of second. Go ahead Eskinder.

ማንበበ ሙሉ ሰው ያደርጋል አይዞን ለሁሉም ቀን አለው እግዜር ይፈርዳል ለነገሩ በሀሳብ ልዕልና አርበድበደናቸዋል::

Suutee Lataa እስኪንድር የጣራዉ ሰልፍ ሠላማዊ ሰልፍ ሣይሆን የናዉጥ ሰልፍ ነበረ ሰለሆነም የከተማችንን ሠላም ለማወክና የመባጠበጥ አጃንዳን በማንጋብ የተጠራ ሰልፍ እንዳይካሄድ በመንግሥት መከልካሉ ትክክላኛ እርምጃ ነው::

Ama Nan አዲስ አበባ የኦሮሚያ ሆነች የአማራ ሆነች የአዲስ አበቤ ሆነች በህዝቡ ኑሮ ላይ አምስት ሳንቲም አይጨምርም ያው ሰውን ለማባላት ፓለቲከኞች የሚጫወቱት ቁማር ነው አዲስ አበባ ከሀብትዋ ድሀው የበዛባት ከአለም ከተሞች የወረደች መሆንዋ እየታወቀ መባላት ይገርማል::

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.