Breaking News
Home / Amharic / ከአማራ ፋኖ የተሰጠ አስቸኳይ ወቅታዊ መግለጫ!

ከአማራ ፋኖ የተሰጠ አስቸኳይ ወቅታዊ መግለጫ!

መንግስት ጎንደርን በከባድ መሳሪያ እና እና ቦምብ ሲያናውጣት አድሯል! አልተሸበርንም ! ወደ 2008 ልንመለስ ግን እንገደዳለን !
ሁሉም የአማራ ፋኖ በተጠንቀቅ እንዲቆም ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡ በአማራ ፋኖወች ላይ ሚደረገዉ ወከባ በአስቸኳይ አሁኑነ የማይቆም
ከሆነ በመላዉ አማራ ህዝባዊ እምቢተኝነት ለመጀመር እንገደዳለን፡፡ ፋኖነት ከኔ በላይ ቅድሚያ ለሀገሬ ከሚል ብሂላዊ እሳቤ የሚወለድ
ቢሆንም በህዝብ ደም ላይ መነገድ የለመዱ እኩያን ፋኖን እያሳደዱት ነዉ፡፡ ነገሮች መስመር ሳይስቱ ማስተካከል የሚጠቅመዉ ገዥዉን መንግስት ነዉ፡፡ ከዚያ ዉጭ ግን አማራን ሰላም ለመንሳት በሚደረገዉ ወከባ ሁሉ ፋኖ እጅ ሰጥቶ የማይንበረከክ መሆኑን እንድትገነዘቡ እያሣሰብን በሁለት ቀነ ገደብ ዉስጥ ፋኖን የማሳደድ ስራ የማይቆም ከሆነ ከጎንደር ዉጭ ባሉ የአማራ ከተሞች ባህርዳር፤ ደሴና ደብረብርሀን ህዝባዊ እምቢተኝነት የሚጀመር መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በዚኅም እንደ አሁን ቀደሙ ወደበረሃ ሸሽቶ የሚታገል ፋኖ የለም፡፡ ከተማን ምሽጉ ያደረገዉ የፋኖ ሃይል የከተማ ዉስጥ ጥቃት መፈጠም
እንዲጀምርም አትገፋፉት፡፡ ፋኖ ህዝባችን እየደረሰበት ካለዉ በደል አንፃር ነገሮችን በአርምሞ እንከታተል ብለን ለዉጭ ጥቃት አጠፋ ራሳችንን
ስናዘጋጅም ነበር፡፡ ይህ ማለት ግን የፋኖን ያክል ፖለቲካዊ መረዳት የሌለዉ ሆዳም ካድሬ እኛን ለማጥፋት ሌት ከቀን እንደሚሰራም ሳይገባን ቀርቶ
አይደለም፡፡ ሆዳሙን እንደሆዳምነቱ መጠበቅም የፋኖ ተልዕኮ ነዉ በማለትም ትዕግስት ተላብሰን ቆይተናል፡፡ ያ ሳይሆን ቀርቶ ግን መሳደድ
የሚቀጥል ከሆነ ፋኖ ለሚቃጣበት ጥቃት ሁሉ እራስን የመከላከል አጠፋ ብቻ ሳይሆን ወደ ማጥቃት የተሸጋገረ ተልዕኮ ይፈፅማል፡፡ የአማራ ህዝብ
ዙሪያዉን በከበቡት የኦነግና ህወሃት አይነት የድርጅት ጠላቶች ምክንያት ግፍና በደል ማስተናገድ ከጀመረ ግማሽ ክፍለዘመን የሞላዉ ሲሆን ይህንን
ፅዋ የተረዳዉ ፋኖ ህዝባችንን ለመጠበቅ ካለዉ ፅኑ ፍላጎት የተነሳ የአደረጃጀት ሰንሰለቱን በብዙ መዋቅር ዘርግቷል፡፡ ይህንን መዋቅር በፖለቲካ ሴራ
መመታት አይደለም አማራን ኢትዮጵያን እንደሃገር ይጎዳታል፡፡ በፋኖ እምነት ‹‹ፋኖ ላይ የሚሰነዘር ጥቃት ሁሉ ኢትዮጵያን ለመበታተን የሚደረግ ተልዕኮ›› እንደሆነም እንገነዘባለን፡፡
 
ስለሆነም፡ 1- በሁሉም የኢትዮጵያና አለም ከተሞች ያላቹህ የአማራ ሲቪክ ማህበራት፤ ፖለቲካ ድርጅቶች፤ የአማራ ወጣት ማህበራት፤ አተማና ሌሎችም፡- መንግስት ፋኖ ላይ እያደረሰ ያለዉን ማሳደድና፤ ወከባና እንግልት በአስቸኳይ እንዲያቆም የሽምግልናና ግንዛቤ
ማስጨበጥ ስራ እንድትሰሩ ስንል እናሳስባለን፡፡
 
2- ለአማራ ህዝብ፡- ፋኖ ራሱን ለመከላከል በሚወስደዉ አጠፋ ህዝባችን ላይ እንግልት ሊደርስ ስለሚችል ከአሁነ ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ እያሳሰብን የማህበራዊ ሚዲያ አዉታር ተጠቃሚ የአማራ ህዝቦች ፋኖ ላይ እየተሸረበ ያለዉን ሴራ ሁሉ በገጠር ለሚገኙ ዘመዶቻቹህ መረጃ በማድረስ እንድትተባበሩ እንጠይቃለን፡፡
 
3- ለአማራ ልዩ ሃይል አባላት፤ ድህንነትና ፀፅታ መዋቅር፡- ብልህ ከሌሎች አይቶ ይማራል፡፡እኛ ግን እየደረሰብን ያለዉ ግፍና በደል እንኳን ሊያስተምረን አልቻለም፡፡ የትኛዉም የፌዴራል መንግስት የፀፅታ መዋቅር ለፋኖ ስጋት ሁኖ አያዉቅም፡፡ ያዉቁናል፡፡ እየተሸረበዉ ያለዉ ሴራ ሁሉ ወንድምን ከወንድም የማጋጨት ተልዕኮ ነዉ፡፡ ፋኖ ወደ ወንድሞቹ አፈሙዝ አያዞርም፡፡ አዙሮም አያዉቅም፡፡ ያ ማለት ግን በመተዳደሪያ ደንባችን ዉስጥ ላስቀመጥነዉ አላማ እንቅፋት የሚሆን ማንኛዉም አካል ከገጠመን ግን በሬሳ ላይ ተረማምደን እናልፋለን፡፡ ምክንያቱም እኛ ህዝባዊ ሰራዊት ነን፡፡ ስለሆነም ባላቹህበት የፀፅታ ዘርፍ መዋቅር ዉስጥ ሁናቹህም ሆነ ወጥታቹህ ለምታደርጉት ድጋፍ ከልብ እያመሰገንና አንደነቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እያሳሰብን ህዝብን በሚጠቅም ተልዕኮ ሁሉ ፋኖ የጀርባ ደጀናቹህ ባቻ ሳይሆን መንገድ ጠራጊያቹህ ጭምር መሆኑን እንድትገነዘቡ እንጠይቃለን፡፡
 
4- ለአማራ ምሁራን፡- የእናንተ ፖለቲካ መረዳት ለአማራ ህዝብ ትልቅ አስተዋጥኦ አለዉ፡፡ ያልተረጋጋ ቀጠና የህዝባችንን ሰላምና ኢኮኖሚ ከመንሳት የተሻገረ ፋይዳ አይኖረዉም፡፡ ፋኖ ይኸንን ጠንቅቆ ይረዳል፡፡ ቢሆንም ግን ከመንግስት የፀፅታ መዋቅር ተደጋጋሚ ትንኮሳ ፋኖ ላይ እየተደረገ ነዉ፡፡ፋኖ ብዙ ሙከራን በትዕግስት አልፏል፡፡ ነገሮች ከቁጥጥር ዉጭ ሳይሆኑ የሸምጋይነት ሚና በመጫወት ለአንድ አላማ እንድንታገል ጥሪ እናቀርባለን፡፡
5- ጎንደር እንደሌለቹ የሀገሪቱ ከተሞች ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ትፈልጋለች፡፡ በዚህ ዘርፍ ለሚሰማሩ አካላት ሁሉ ፋኖ ሙሉ ጥበቃ ያደርጋል፡፡
ከዚያ አልፎ ግን ጎንደርን ሁሌም የጥይት አሩር መሞከሪያ ብቻ ማድረግ አሁኑኑ ሊቆም ይገባል፡፡ አማራነትንም ሆነ ኢትዮጵያዊነትን ከወደቀበት ዝቅታ
አንስታ ወደከፍታ ማማ የሰቀለች ጎንደር በፋኖ ልጆቿ ተከብራ ይሄንንም ጊዜ ታልፈዋለች፡፡ ፋኖ አማራ!
 
መጋቢት11-2012ዓ.ም ጎንደር
(መረጃዉ ለሁሉም ሰዉ ይዳረስ ዘንድ የአማራነትወን ግዴታ ይወጡ!)
 

 

 
 
 

3 comments

  1. This situation is a wake up call and should raise the alam for those who are concerned about the future of the amhara people and their sovereignty. As the saying , “Jeb bekededew leba yegebal,” goes the current Ethiopian leaders are determined to use what the TPLF has created during the last 30 years to their advantage. They want to create Ethiopia in their own image. This has been evidenced by the fact that the Ethiopian leaders recently removed real leaders of the Amhara from their influential position and put in their place Bandas. The move was carefully orchestrated so that they would take subsequent measures. The goal is to continue to weaken amhara nationalism and real amhara leadership so that they can implement their own version of Ethiopia, just like their predecessors did.

    I think that the focus of any amhara opposition group, including, ANM, should be on seeking ways in which the amharas will get their own leaders, both with in the current regime and outside in the opposition camp. The ones that are in top leadership were handpicked by their masters. They have already shown their contempt to the amhara people and wouldn’t be trusted any more.

    What happened in Gondar should be seen in this perspective and is nothing less than trying to disarm Amhara vanguards before upcoming election. Therefore, every concerned Amhara should raise its voice and be alert for what is to come next.

  2. ማነነታቺን እናስከብራለን እነዋደቃለን እናሸነፋለን

  3. I heard the announcement of the Gondar City Administration today. It supports my view that the current leadership have decided to war with Fano! This struggle is the struggle for the survival and safety of Amhara as a people. We need to oppose this announcement and encourage the leaders to come to talks with Fano and find a solution.

    Fano and the Amhara people should be ready for any eventuality!
    We can’t let this chance to slip from our hands or else we would find ourselves slaves to an even more determined and formidable enemies lurking sound us.

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.