ግንባር ቀደሟ ጎንደር አቢዮታዊ መፈክሯን ከፍ አድርጋ እያሰማች ነው!!
ዛሬ መጋቢት 8/2011 ዓ.ም በአጼ ፋሲል ስታዲዮም ከደቂቃዎች በኋላ ለሚጀምረው፣
በፋሲል ከነማና በሲዳማ ቡና መካል ለሚደረገው የእግርኳስ ግጥሚያ ጎንደሬ አማራዎች መፈክራቸውን እየተስተጋቡ ነው!!
እየተስተጋቡ ያሉ መፈክሮችም ከብዙ በጥቂቱ፦
***
* ለአማራ ተብሎ የሚሻሻል ህግ ከሌለ አማራው የራሱን ህገ መንግስት ለመጻፍ ይገደዳል!!
*አገር ለማፍረስ ትምህርትም እውቀትም አይፈልግም!! ጃዋር ከአ.አ እጅህን አንሳ!!
* ጌዲኦ ሁሉም ያልፋል ስለእናተ እኛ አማራዎችም ታመናል!!
*ቅድሚያ ከአማራ ክልል ውጭ ያሉ አማራዎች ህጋዊ ውክልና ይሰጣቸው!!
* እኛ አማራዎች አንቆጠርም!! አናስቆጥርም!!
* አማራን የማይወክል ህገመንግስት ለአማራው ምኑነው?
*የተበታተነ ህዝብ ሳይሰበሰብ የፈረሰ ቤት ሳይሰራ ስለ ቆጠራ መስማት አንፈልግም!!
*አዲስ አበቤዎች ስሙ!! ምንም ቢፈጠር አማራ እያለ እናተ አታለቅሱም!!
* ሶማሌዎችና አፋሮች ስለደረሳችሁልን እናመሰግናችኋለን!!
* የእኛ ትግስት ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ እንጂ ከማንም!! በምንም አንሰን አይደለም!!