Breaking News
Home / Amharic / ከአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የተሰጠ መግለጫ!

ከአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የተሰጠ መግለጫ!

ከአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የተሰጠ መግለጫ!

ከዚህ በፊት በተደረገው ጥሪ መሰረት በርካታ የሕዝባዊ ኃይሉ (ፋኖ) አባላት በሁለት የተለያዩ ግምባሮች ዘመቻውን የተቀላቀሉ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም የጦርነቱ ስፋት እና አጠቃላይ ሁኔታው እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት ተከታዩን ጥሪ ማስተላለፍ አስፈልጓል።

ስለሆነም:-

1/ የግል ትጥቅ እያላችሁ በተለያየ ምክንያት እስከዛሬ ወደ ግምባር ለመግባት የዘገያችሁ አባሎች በአስተባባሪወቻችሁ አማካኝነት ወደ ተነገራችሁ ቦታ በአስቸኳይ እንድትከቱ ይሁን፤
2/ ዘመቻውን ከተቀላቀልን ወዲህ በተወሰኑ ወረዳወች ወታደራዊ ስልጠና የተጀመረ ቢሆንም ይህ ስልጠና በሁሉም ወረዳዉች ተጠናክሮ መቀጠል ስላለበት ሰሞኑን በየከተሞች ባደረግነው ቅስቀሳ መሰረት የተመዘገባችሁ እና ሌሎችም ስልጠናውን እንድትጀምሩ፤
3/ ማንኛውም የመንግስት አካል ስልጠናወችን ቢቻለው ያስተባብር፣ ያግዝ አልያ ደግሞ መሰናክል ከመሆን ይቆጠብ፤
4/ ሰልጥናችሁ እና ለዘመቻ ብቁ ሆናችሁ በግብዓት እጥረት ምክንያት መዝመት ያልቻላችሁ የህዝባዊ ኃይሉ አመራር የናንተን ፍላጎት ለማሟላት የሚያደርገው ጥረት እስኪሳካ ድረስ በአንድ በኩል በራሳችሁ መንገድ ትጥቅ የምታሟሉበትን መንገድ እየፈላጋችሁ በሌላ በኩል ደግሞ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመናበብ አካባቢያችሁን የመጠበቅ ፣የዘማች ቤተሰቦችን በመንከባከብ እና ሰብል በመሰብሰብ እንድትጠብቁ ይሁን፤

5/ በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም ያላችሁ የትግሉ ደጋፊወች ቀሪዋ የህዝባችን ጀምበር ሳትጠልቅ እንደ አማራ ስንነሳ እንደምናሸንፍ አምናችሁ የህዝባዊ ኃይሉን (ፋኖ) ለመደገፍ ተረባረቡ።

 

አዲስት ትዉልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
 
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.