Breaking News
Home / Amharic / ከምስራቅ ወለጋ ዞን አማራዎች በብዛት አዲስ አበባ ገብተዋል::

ከምስራቅ ወለጋ ዞን አማራዎች በብዛት አዲስ አበባ ገብተዋል::

   

ከምስራቅ ወለጋ ዞን በማንነታቸው የተፈናቀሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች አ

ዲስ አበባ ገብተዋል፤ አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ እንዲደረግላቸው ተጠይቋል።
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ህዳር 5 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ
ከምስራቅ ወለጋ ዞን በማንነታቸው የተፈናሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ
አማራዎች በጅማ በኩል ዞረው አዲስ አበባ ገብተዋል፤ አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ እንዲደረግላቸው ተጠይቋል።
ከጥቅምት 25 ቀን 2014 ጀምሮ ከምስራቅ ወለጋ ዞን ቦነያ ቦሼ ወረዳ ከተፈናቀሉት በሽህዎች ከሚቆጠሩ አማራዎች መካከል 91 የሚሆኑት ህዳር 3 ቀን 2014 ዓ/ም አዲስ አበባ ገብተዋል።
ከመካከላቸው 28ቱ ህጻናት መሆናቸው ታውቋል፤ በወለጋ ተፈናቅለው ከሰሞኑ አዲስ አበባ ከገቡትም ነመንገድ ላይ ጭምር የወለዱ እናቶች እንደሚገኙ እየተገለጸ ነው።
ገና አዲስ አበባ አየር ጤና አካባቢ ከመግባታቸው ለሚዲያ መረጃ እንዳይሰጡ እና የገዳዮችና የአፈናቃዮች ገመና እና ትንሽነት እንዳይጋለጥ በአንዳንድ ካድሪዎች ጫና የተደረገባቸው መሆኑ ታውቋል።
በስቃይ የደረሱት ተፈናቃዮችም ኮልፌቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዘነበ ወርቅ አካባቢ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።
ከዚህ በተጨማሪም በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስኮ መነሀሪያ አካባቢ ከወለጋ ተፈናቅለው የመጡ 75 አማራዎች እንዳሉ ተሰምቷል።
ለወገን ደራሽ ወገን ነውና የአካባቢው ማህበረሰብን ጨምሮ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ለወገኖቻችን በመድረስ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ተጠይቋል።
መንግስት ንጹሃንን ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ፣ በቢሮ ከተሰገሰጉ ጽንፈኛ ኦነጋዊያንና ቡድኑ ካሰማራቸው ዘራፊዎች ለመታደግ አልቻለም፤ አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታና መጠለያ ለመስጠት አልቻለም በሚል በተደጋጋሚ እየተወቀሰ ይገኛል።
አቶ ሽመልስ የሚመሩት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አማራን ከክልሉ የማጽዳት የኦነግ ሸኔን አላማ ይጋራዋል ብቻ ሳይሆን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በበላይነት እያስፈጸመው ይገኛል የሚሉት ብዙዎች ናቸው።

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.