Breaking News
Home / News / እስክንድር አዳራሹን በመከልከሉ ጋዜጣዊ መግለጫውን እንዲያቋርጥ አስገድዶታል::

እስክንድር አዳራሹን በመከልከሉ ጋዜጣዊ መግለጫውን እንዲያቋርጥ አስገድዶታል::

በጣም የሚገርም ነው ምን ያህል የአዲስ አበባ ህዝብ ተኝቶ በኦነግ ስር እንደ ወደቀ ያሳዝናል:: ለዚህ እኮ ነው አማራው ጠንክሮ እንዳይወጣ እያታገሉት የነበረው:: አሁንማ ስልጣን በእጅ ሆነ እኮ !

ፍርዱን ° ለህዝብ!!

ሰላማዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ፕሮግራም ማስተጓጎልና የመንግስት ግልጽ የአምባገነንና የአፈና ተግባር ነው!!

እነ እስክንድር ነጋ ዛሬ በራስ ሆቴል አዳራሽ ከሕዝብ ጋር ሊያደርጉት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ የአዲስ አበባ እና ፈደራል ፖሊሶች በጥምረት ከላይ የመጣ ትእዛዝ ነው በማለት ከልክሏቸዋል።

መረጃ 1)

እስክንድር ነጋ በራስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጥ መከልከሉን ተከትሎ ውጪ ወጥቶ ለዘገባ ለመጡት ጋዜጠኞች መግለጫን በመስጠት ላይ እያለ ፖሊስ መንገዱን በመዝጋት ጋዜጣዊ መግለጫውን አቋርጧል።

መረጃ 2)

ኮሚሽነሩ፡ “እስክንድር አንዴ ለብቻህ ማናገር እንፈልጋለን!”

እስክንድር፡ “ኮሚሽነር፣ እዚሁ በሰዎች ፊት በምስክር ፊት መነጋገር እንችላለን!”
..

ከዚህ በኃላ የኢትዮጵያን ህዝብ ፍላጎት ማፈን አይቻልም። ከእንግዲህ ወዲያ ኢትዮጵያን አፍኖ መግዛት ፈጽሞ የማይሞከር መሆኑን የዶ/ር አብይ መንግስት ሊረዳ ይገባል።

ዛሬ እስክንድር ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጥ መከልከል ትችሉ ይሆናል። ነገር ግን እስክንድርን የቆመለት ሃሳብ የሁላችን ሃሳብ ነውና ማፈን አትችሉም።

የኢትዮጵያ ህዝብ አውቆ ሊያልፍ ይችል ይሆናል እንጂ ሊሸውድ የማይችል ማንም ሊደልለው የማይችል ንቁ ህዝብ ስለሆነ ጀግናው እስክንድር ነጋ እንዳይናገር ቢታፈንም ምን እንደሚናገር እናውቃለን።

ስለ አዲስ አበባ ስለ ኢትዮጵያ ፤ ስለ ፍትህ እንጮሃለን። የእስክንድር ልብና የኢትዮጵያ ህዝብ ልብ አንድ ነው!

ከእስክንድር ጎን ለእውነትና ፍትህ እንቆማለን!!

አብይ በዚህ ድርጊትህ ልታፍር ይገባል !!!!!

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.