Breaking News
Home / Amharic / ኢትዮጵያ የታላቁ የሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ በአሜሪካ ሊካሔድ በታሰበው ስብሰባ ላይ እንደማትገኝ አስታወቀች!

ኢትዮጵያ የታላቁ የሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ በአሜሪካ ሊካሔድ በታሰበው ስብሰባ ላይ እንደማትገኝ አስታወቀች!

ኢትዮጵያ የታላቁ የሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ በአሜሪካ ሊካሔድ በታሰበው ስብሰባ ላይ እንደማትገኝ አስታወቀች
**************************************

የታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ በአሜሪካ ሊካሔድ ታስቦ የነበረው የሦስትዮሽ የድርድር መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን እንደማይገኝ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን የካቲት 19 እና 20 ቀን 2012 በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ሊካሔድ በታሰበው የሦስትዮሽ ድርድር ላይ እንደማይሳተፍ የውኃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ነው ያስታወቀው።

ቡድኑ በስብሰባው የማይገኘው በአገር ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገውን ውይይት ባለማጠናቀቁ እንደሆነም ጥሪውን ላደረገው የአሜሪካ የትሬዠሪ ቢሮ አስታውቋል።

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.