Breaking News
Home / Amharic / “ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል ስለተሰረዘ ቅር ብሎኛልና ይመለስ ! Professor Fikre Tolossa

“ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል ስለተሰረዘ ቅር ብሎኛልና ይመለስ ! Professor Fikre Tolossa

“ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል ስለተሰረዘ ቅር ብሎኛልና ይመለስ
*********************************
ከ ሶስት ወራት በፊት ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጋራ ተገናኝቼ ነበር። ስለተለያዩ የሀገር ጉዳይዎች ከተወያየን በሁዋላ “የብልጽግና” የሚባል ፓርቲ ሊመሰርቱ እንደአሰቡ ገለጡልኝ። እኔም “የብልጽግና ፓርቲ” የሚለው ስም ኃይል የለውም ፣ “የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ” ቢባል የተሻለ ነው አልኩአቸው። “አይ፣ ስሙ እንዲያጥር ፈልጌ ነው፣ ሁለት ቃሎች ብቻ እንዲሆኑ ሽቼ ነው፣” አሉኝ። ”ስሙ ቢያጥር እና ኃይል ባይኖረው ምን ጥቅም አለው? ‘ኢትዮጵያ’ የሚለው ቃል አንደኛ የድል አድራጊነት ምልክት ነው። ጎሰኝነት መሸነፉን የሚጠቁም ነው። ሁለተኛ፣ እግዚአብሄር የመረጠው የክብር ስም ነው። ሶስተኛ የኢትዮጵያ መስራች የአባታችን የኢትዮጵ ስም ነው። አራተኛ ብሄራዊ ስም ስለሆነ መላውን ሀገር ስለሚጠራ የኢትዮጽያ ህዝብ ሁሉ ፓርቲው የኔ ነው፣ ብሎ ሊያስብ ይችላል። ስለእዚህም ድምጹን ለእርስዎ ፓርቲ ሊሰጥ ይችላል፣” አልኩአቸው። እሳቸውም ፈገግ ብለው “ሌላም ሰው “የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ” ይባል ብሎኛል፣ አስብበታለሁ፣” አሉኝ። እኔም ፈገግ ብዬ “ምንም ማሰብ አያስፈልግም፣ በቃ እኔ ” የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ ብየዋለሁ፣” አልኩአቸው።

ሳምንታት አለፉና “የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ” ተብሎ በ መገናኛ ብዙሀን ተበሰረ። እኔም ደስ አለኝ።

ፓርቲውን ለማዋሀድ ኢህአደግ እና አጋሮቹ ከተሰበሰቡ በሁዋላ ከፓርቲው መጠሪያ ውስጥ “ኢትዮጵያ” የሚለው ክቡር እና መለኮታዊ ቃል ተጥሎ “የብልጽግና ፓርቲ” ብቻ ተብሎ ብቅ አለ። የስሙም ግርማ ሞገስ ተገፎ ፓርቲው ቀትረቀላል ሆነ። አዘንኩ። ለምን መላውን አፍሪካ እና አትላንቲክን እና የህንድን ውቅያኖሶችን ድሮ “ኢትዮጵያ” ያሰኝ የነበረው የመላው ጥቁር ሁሉ ኩራት የነበረው ስም ተጣለ ብዬ ራሴን ጠየቅሁ። ከህሊናዬ ያገኘሁትም መልስ ኢትዮጵያን የሚጠሉ፣ ግን በእናት ኢትዮጵያ ጡት የፋፉ፣ ሆኖም ጡትዋን የሚነክሱ አክራሪ ፓለቲከኞች ጠቅላይ ሚንስትሩን ክፉኛ ሞግተዋቸው ስሙን አስቀሩት፣ የሚል ነው።

የ “ኢትዮጵያ” ትክክለኛ ትርጉሙ “ብጫ ወርቅ ስጦታ ለእግዚአብሄር” ማለት ነው። ከፊቱ “ኢትዮጵያ” የሚለው መለኮታዊ፣ ቅዱስ እና ድል አድራጊ ቃል የሌለው የፓርቲ ስም በጣም ደካማ ነው። ጥላቢስም ነው። እግዚአብሄር የወደደውን እና የመረጠውን ቃል ጠልቶ እና ጥሎ ያለ እግዚእብሄር ፍቃድ እበለጽጋለሁ ማለት ከንቱ ነው። ደሞም “የብልጽግና ፓርቲ” የሚለው አጠራር ባለቤትአልባ ነው። የማን ፓርቲ? የቻይና? የህንድ? የኮርያ? አይለይም። ስለእዚህ፣ ጠቅላይ ሚንስትሩ ነገሩን እንደገና አጢነው ከፓርቲያቸው ስም ፊት “ኢትዮጵያ” የሚለውን እጡብ ድንቅ ስም መልሰው አኑረው “የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ” ይሉት ዘንድ እመክራለሁ።

ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ, የሁማኒቲስ ፕሮፌሰር

  • Fikadua Assefa ኢህአዴግ ርግማናችን ነው። አጭበርባሪ ፤ ዋሾ ፤ በፀረ ኢትዮጵያ ትርክት ተኮትኩተው ባደጉ ባንዶች ፣ ማይማንና ሆድ አደሮች የተሞላ የነቀዘ ቡድን ነው። ስልጣኑን/ ስርዓቱን ማስቀጠያ መንገድ እንጂ የኢትየጵያና ኢትዮጵያውያን ክብር አይገደውም።
  • ሀይፋ ሀይፋ ሀይፋ ሀይፋ ኢሀዲግ ኢትዮጵያ ብሎ ምን ለውጥ አመጣ?🤣🤣🤣
  • Mezmur Zdawit ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ክብር ይመልሳል ብለው ማሰብዎት እራሱ ለፓለቲካው አዲስ እንደሆኑ ያሳያል…ሌላው ቀርቶብን እንደ ግለሰብ ኢትዮጵያዊ ተብለን እንድንጠራና በየትም ቦታ ተዘዋውረን የመስራት መብታችን በተከበረ….በሃገራችን መጤና ሰፋሪ እየተባልን ነው
  • Eman Negash ይህ ሰው የእውነት ፕሮፌሰር ነው ?
    ብልፅግና የሚል ቃል እንኳን ቻይና፣ሕንድና ኮርያ 1/3ኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቀዋል ?አይ ፕሮፌሰርነት እንደዚህ መጫወቻ ሆነ?ኢትዮጵያ የሚልን ስም እግዚአብሔር መረጠልህ ? ፓ ፓ ፓ ፓ ፓ
  • Tadesse Kebede አንድ የፖለቲካ ድርጅት በአገሩ ውስጥ የተመስረተና ዜግነታቸው ኢትዮጵያ የሆኑ ስዎች የፈለጉትን ስም ኢትዮጵያ የሚል ስም ከጎኑ ካልተጨመረ ዚጋ መሆናቸው አይታወቅም ማለት? በዚህ በአሜሪካን አገር ውስጥ የትኛው የፖለቲካ ድርጅት ነው የአሜሪካን ስም ያለው ፓርቲ? እንደዚህ አይነት ጥያቂዎች የሚነሱት በፖለቲካ ድርጅቱ ላይ ወይም በግለስቦቹ ላይ በኢትዮጵያዊነታቸው ሳናምን ስንቀርና የውጭ ዜጎች ናቸው ብለን ስናምን ብቻ ነው በርግጠኝነት ዶ/ር አብይ እንደዚህ ዓይነት ጥያቂ የሚያነሱትን ግለስቦች ይታዘቧቸዋል ብየ አምናለሁንኝ:
  • Fikre Tolossa ታዴ
    በመጀመሪያ ሰላም ላንተ ይሁን። ቀጥሎ ስለአሜሪካን ፓርቲዎች የጠቀስከው እነሱ ቀደም ሲል የጎሳ ፓርቲዎች አልነበሩም። የኛ በጎሳ የተደራጁ ናቸው። ኢትዮጵያ የተባለውን ስም ለመጥራት የተጠየፉም ጎሰኞች ሀገሪቱ ሲልዋት ከርመዋል። አሜሪካኖቹ ግን አሜሪካን ጠልተዋት አያውቁም። God bless America” ነው የሚልዋት። ስለእእዚህ Republican or Democratic Party ቢሉ ችግር የለውም። ይህን ማገናዘብ ያሻል። የእኛና የእነሱ ሁኔታ የተለየ ነው። ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል።
  • Tadesse Kebede ዶ/ር ፍቅሪ ትክክል ነው ያሉት ነገር ግን በአገራችን እጅግ በጣም ክፉ ስዎች ስላሉ ምክንያት እየፈጠሩ እርስበር የማጣላት ሥራ ስለሚስሩ ነው ለጥንቃቂ ነው

    Fikre TolossaFikre Tolossa replied

      1 reply   1 hr

  • Aster Melaku ስሙ ምን አርጋቸው ኢትዮጵያን የጠሉት በስሙ እኮ ነውየሚበጣበጡት
  • Eddie Mekasha የዲሞክራሲን ጽንሰ-ሃሳብ ያፈለቁት ግሪኮቹ ሆነ በዲሚክራሲ የሚመሩ ሃገሮች የግሪክ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የአሜሪካ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የእንግሊዝ ኮንሰረቫቲቭ ፓርቲ ተቀጽላ የላቸውም:: በጥቅሉ አዲስ ዲሞክራቲክ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊካን ሌበር ኮንሰረቫቲቭ እንጂ:: ማንኛውም ፓርቲ በሚንቀሳቀስበት ሃገር የሃገሩ ስም ሲጠቀስ ኣላየንም::
  •  
  •  
  • Muhammed Awel Obsa ቀባዣሪ
  • Saddam Muhammed ስለዚህ እርስዎ ቅር ያልዎት የራስዎ ሀይማኖት ኣንጸባራቂ የሆነ ቃል (ራስዎ እንደ አስቀመጡት ትርጓሜ-እኔ ትርጉሙ እውነት ባይመስለኝም ) ለምን አገሪቱን ወክሎ በተዘዋዋሪ ያቺ እምነትዎ ቦታ አልተሰጣትም ነው ? በአገሪቱ <መለኮታዊ > ያሉት ገለጻ የማይከተል ብዙ ሚልየን ሰው እንዳለን ለምን አይረዱም? የ EOTC ሀይማኖት እንደ ኦፊሻላዊ መንግስት የማየት አባዜ እልም ያለ ዘረኝነት መሆኑ ብረዱ ደግሞ መልካም ነው።
  • Saddam Muhammed ስለዚህ እርስዎ ቅር ያልዎት የራስዎ ሀይማኖት ኣንጸባራቂ የሆነ ቃል (ራስዎጨእንደ አስቀመጡት ትርጓሜ-እኔ ትርጉሙ እውነት ባይመስለኝም ) ለምን አገሪቱን ወክሎ በተዘዋዋሪ ያቺ እምነትዎ ቦታ አልተሰጣትም ነው ? በአገሪቱ <መለኮታዊ > ያሉት ገለጻ የማይከተል ብዙ ሚልየን ሰው እንዳለን ለምን አይረዱም? የ EOTC ሀይማኖት እንደ ኦፊሻላዊ መንግስት የማየት አባዜ እልም ያለ ዘረኝነት መሆኑ ብረዱ ደግሞ መልካም ነው።

    G'ashu AsmareG’ashu Asmare replied

      1 reply   7 hrs

  • Netsanet Ybeltal ፕ/ር ሀሳበዎት ተቀባይ ቢያገኝ መልካም ነበር።ነገር ግን እርሰዎም እንደገለጹት ዶ/ር አብይ አስቀድሞ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ማከተት እንዳልፈለገ በምክንያት አስረድቶወታል።ሀገራዊ ፓርቲ አቋቋምሁ እያሉ የሀገርን መጠሪያ መጠቀም አለመፈለግ የሚያሳየው ነገር የፓርቲው ምስረታም እውነተኛ አንድነት ለማምጣት ያለመ፡ሳይሆን ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚደረግ ጥረት አካል ነው።
    የአክራሪዎች ሚና እንዳለ ሁኖ ከመነሻውም፡ ደፍሮ ከመሞገት ዶ/ር አብይ አላመኑበትም፡ነበር።በእምነት ያልተያዘ ነገር ደግሞ፡ ውጤቱ ዜሮ ነው
  • Getachew Mulatu ፕሮፌሰር ስዎች በጣም የተካኑ አስመሳይ ባለማስክ መሆናቸዉን እንጅ በእዉነት የኢትዮጵያ ፍቅር ያላቸዉ ሰዎች አይደሉም። ይህ ከዉስጣቸዉ ያለዉን የኢትዮዮያ ጥላቻቸዉን ነዉ ሚያሳየዉ። ሌላዉ እነዚህ ሰዎች ያስመሳሉ እንጅ እምነት የሌላቸዉ የሶዶማዊያን ደግፊዎች ናቸዉ። ስለዚህ የኢትዮዮያን መለኮታዊነት፣ ሃያልነት አይቀበሉም። ስለዚህ በኢትዮጵያ ስም እየማሉ ሰንደቅ አላማችንንም ያከበሩ እየመሰሉ ያታለሉን አታላዮች ናቸዉ። ለጊዜው ነዉ እንጅ እርስ በእርሳቸው እስከመባላትና መቦጫጨቅ ይሄዳሉ አይቀናቸዉም አይስስካላቸዉ። እኔ በታሪክ በአጭር ጊዞ ያን ያህል ፖፕላር ሁኖ በፍጥነት ባዶ የቀረ መሪ አላዉቅም።
  • Kidane Lilay የስሙም ግርማ ሞገስ ተገፎ ፓርቲው ቀትረቀላል ሆነ።
  • Nathan Nathan RESPECT.
  • Msmaku Asrat ተገዶ መቀየር ብሎ ነገር የለም። ጠቅላይ ሚንስትሩ ፈቅደው ፈልገው ያደረጉት ነው። ማጭበርበር በጣም ስለተደጋገመ ሰልችቶናል። መርሮናልም።
  • Añteneh Gobezie ይህ ሀሳብ የመላዉ ኢትዮጵያ ዊ ሀሳብ ና ስሜት ነዉ ግን አሁን ኢትዮጵያ ን ጠል በዝቶዋል ። ምንም አያመጡም ጠሎችዋ ይጠፋሉ።
    ክቡር ፕሮፌሰር ፍቅሬ ኢትዮጵያ ላይ ተዶልቶ የአለም ሀገራት ሳይወዱ ሁለቱን የ አለም ጦርነት ውስጥ ተማገዱ ። አሁን ጠሎችዋ በሀገርም በዉጪም ሀገራት በዝቶዋል የማይታገሱ ከሆነ ለይነሱ ዳግም ፫ኛውን የ አለም ጦርነት ያቀርቡታል ።
    ኢትዮጵያ ን የጠላ፣ ያሴረባት ና ያንቓሸሸ አሸንፎ አያዉቅም ድባቅ ከመመታቱ ዉጪ ።
  • Kaleb Negus ኘሮ ፍቅሬ የተቀደሰ ሀሳብ መክረዋል! ግን ምከረው እንቢ ካለ መከራ ይምከረው እንዲል የ7ኛውን ንጉስ መጨረሻ የፖለቲካ ፍልስፍና ጉዙውን ማየት ነው።
  • Yodit Kassa በጣም ትክክል ኖት ፕሮፌሰር በማስተዋል የሚራመዱ ትልቅ ሰዉ ኖት።
  • Anchor Christian I always do respect you! ግን ይህ ሰው ማነው? ፕሚ ማለቴ ነው… እስካውቀው ቸኩያለሁ … የነጮችን የዘመናት ህልም እያሳካ ያለ .. ለማመን አስቸግሮኛል … ኢትዮጵያን አይናችን እያየ ልናጣት ይመስላል … 😢
  • Abera Yi Habte ፕ/ር ፍቅሬ እውነተኛው የታሪክ ሰው ነህ። ብዙዎቻችን ኢትዮጵያ የሚለው ከፊት ለምን አልታከለበትም ብለን ቅሬታ ተሰምቶናል። ዶ/ር አብይ ራሱ ቢያምንበት ኖሮ አይቀርም ነበር። ኢትዮጵያ የሚለውን ስም እና የኢትዮጵያን ታሪክ የራሱ ድርጅት የሆነው የኦዴፓ አንዳንድ ጽንፈኛ አመራሮች አክራሪ ሙስሊሞች እና ኦነጎች አይፈልጉትም። ኢትዮጵያ ማለት አማራ ማለት ስለሚመስላቸው። ኢትዮጵያ ማለት ኦርቶዶክስ ሃይSee more
  • Asmare Topia እኔም የእርስዎን አይነት አስተያዬት በfb አድራሻዬ ጠቁሜ ነበርደ አሁን ይባስ ብሎ ሁሉም ጎሳ ስሙን እያሰቀደመ እገሌ የብልጽግና ፓርቲ እያለ ነው። ለምሳሌ የኦሚያ ክልል መንግስት በዚህ ሳምንት ሹመት ሲሰጥ፦ አኮሚያ ብልጽግና ፓርቲ የገጠርና ከተማ አደረጃጀት ሀላፊ ብሎታም። ከሆነም መባል ያለበት የብልጽግና በፓርቲ የኦሮሚያ——ቢባል ይሻል ይመስለኛል።
  • Solomon G Adem ለማከብሮ ፕሮፌሰር ፍቅሬ እንደምን አሉ? አንድ ጥያቄ አለኝ በእውነት ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ኢትዮጵያን ከልባቸው ይወዶት ይመስልዎታል የሳቸው ኢትዮጵያ ያላቸው ከከፈራቸው ላይ ናት ከልባቸው ውስጥ አይደለችም ለዛም ነው ዛሬ ሊወገዝ የሚገባው ዘረኝነት በሳቸው ዘመን ሙሉ አካል ሁኖ አገራችንን እያጠፋ ያለው ወደድንም ጠላንም አብይ ተስፋ ማድረግ የትም ሊያደርሰን አይችልም
  • ጆሲ ጆሲ እነጋገራቸውን ስራ ላይ ቢያውሉት ድንቅ መሪ ይሆኑ ነበረ ነገር ግን ወሬያቸውን ህዝብ የሚፈልገውን ብቻ እየተናገሩ ስራቸው ግን ጸረ ኢትዮጵያ ነው አሁን የነበራቸው የቀባይነት እያሽቆለቆለ ነው ምናልባትም ኢትዮጵያን በታሪክ አይታው የማታውቀው ቀውስ ውስጥ ይከታታል።ኢትዮጵያን በሚጠላው አክራሪው ጽንፈኛ ተጽእኖ ስር የወደቁ ይመስላሉ ለዛም ነው በኦሮምያ ክልል በሀገሪቱ ይሄን ያክል ሰው ነገጀራ ብሄርናSee more
  • Eyob Girma “በምናብ የተደረገ ውይይት”
  • Liya Tsion ዎንድሜ አዉነተኛው .የታሪክ ተመራማሪ አትዮጵያዊ ዘመኑ ሀገራችንን .የሚጠሉ .ርኩሳን .አጋንንት የተረቹበት ክ ፉ ዘመን ነው fetari mels.አለው
  • Liya Tsion አይ .ፕሮፌሰር በዎያኔ ዘመን .ያልተፈፀመ .ዎንጀ ል kero በቺካኔ የሰዉ .ልጅ አንደበግ ሲያርድ ርምጃ ከመዉሰድ .ይልቀ mamogesin
    መርተዋል

    Fikre TolossaFikre Tolossa replied

      1 reply   2 hrs

  • Hailu Tsigie የአትዮጵያ በለፅግና ፓርቲ ነበረ መባል የነበረበት መክን ያቱም ሁሉንም ሕዝብ ሰለሚወክል የአማራ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ያማራንንና የኦሮሞን ሕዝብ አንደምወክሉት ፕሮፌስር ፍቅሬ አንዳሉት
  • Dersolign Tsedalu Ewunie በጣም ትክክለኛ ሀሳብ ነው
  • ሃፍታሙ ኣማረ ምርጥ የኢትዮጵያዊነት ደም የተላበሰ ኢትዮጵያዊ -ፕ/ር ፍቅረ ቶሎሳ
  • Yosef Worku Degefe ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ቢኖርም ባይኖርም ችግር ያለው አይመስለኝም like in USA just “Democratic Party” and “Republican Party” እንደሚባለው፣ ማለት ነው።
    በ2ኛ ደረጃ ደግሞ የሶማሌ ከልል ም/ፕሬዚዳንት ሙስጤ ለምንድነው የኢትዮጵያ-ሱማሌ እንደሚባለው የኢትዮ-አፋር (አፋሮች ጅቡቲም ኤርትራም ስላሉ) የኢትዮ-ትግሬ (ትግሬ ኤርትራም ስላሉ) የማይባለው ብሎ የኢትዮ ሱማሌ See more
  • Nyerere Patrice Lumumba Yeqalun tenteletilo meqom yalteredu sewoch zim bilu minale? Anyway Prof. abiy tenegna meri ayedelem! Ersewon gin Fetari Yebarkewot wondim!
  • Ahunim Fenitie በምርጫ ለመሸነፍ ስለፈልጉ ይመስለኛል። ስልጣን ቶሎ ለማስረከብ የቋመጡ ይመስለኛል።
  • Dereje Mengesha የእኔም ምርጫና እምነት የኢትዮጵያ ብልፅግና ፓርቲ ተብሎ እንዲጠራ ነበር ።ሲጀምርም በዚያ ጀምረውት በመሃሉ ተዉት።ይኼ የሚያሳየው ኢትዮጵያ ሲባል ለመስማት የማይፈልጉ ሐይሎች ጫና በፓርቲው ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ እንዳለ ነው።
  • Teshager Belay ሰውየው ሀያላኑ አድርግ የሚሉትን ብቻ የሚያደርግ አይነት ሰው ነው፡፡…ሀያላኑ ደሞ ይህቺን ሐገር መቼ የወዷታል?..ስሟስ እንዲጠራ መች ይፈልጋሉ?..እግዚአብሔር ድል የሚያደርጋቸው በዚቹ በናቋት ኢትዮጵያ በተባለው ስሟ ስለሆነ…እኛ ግን ሴራው ሁሉ ይገባናል፡፡
  • Tewodros Hunachew የሚጠበቅቦትን ሀላፊነት ተወተዋል።
    እግዚ አብሔር ያክብሮት።
  • Fikre Tolossa ውድ አቶ ብንያም
    Septugian Bible ማለትም የመጀመርያው በ 60 የእብራይስጥ ሊቃውንት የተተረጎመው መጽሀፍ ውስጥ “ኢትዮጵያ” እንጂ “ኩሽ” አይልም ። በሁዋላ ዘመን የመጡ የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው ኩሽ የሚሉት። አውጥተህ እየው። ደግሞም ኢትዮጵያ በሴት ስለምትመሰል ቅዱስ ዳዊት ኢትዮጽያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች ይላል እንጂ ኩሽ እጁን ወደ እግዚአብሄር ይዘረጋል አይልም። ኩሽ ወንድ ነውና። ይህን ሁሉ ብናገናዝብ መልካም ነው። ኩሽ የሚባል ህዝብ እንጂ ሀገርም የለም። የጠላት መሳሪያ እንዳንሆን እንጠንቀቅ። እግዚአብሄር በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ከ አርባ ግዜ በላይ ኢትዮጵያ እንጂ ኩሽ እያለ አይደለም የሚጠራት።
  • Fikre Tolossa Tadesse Kebede
    እሺ ወዳጄ ታደሰ
    ። አንተ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ የኦሮሞ ተወላጅ እንደሆንክ አውቃለሁ።
  • Lily Abebayehu Simu endiyatr ? Hahaha . Ethiopia Edmewa endiatr new . Masmeselu bhkerbet ?
  • Ab U Sh አሁን ሚስጥሩ የተገለጠ ይመስላል
    ይህየፈን ያደረገው የጃዋር እና ትህነግ መልዕክተኛ አፉ ማር ውስጡ አረመኔ የሆነው ሱሴ ሀሳብ ነው ማለት ነው
  • Elias Yeteklye Lij ጋሽ ፕሮፎ ፍቅሬ ቶሎሳ አሪፍ ሀሳብ
  • Fikre Tolossa ሰላም ውድ ሳዳም
    ኢትዮጵያ የሚለው ቃል በሁላችንም አባት (በአንተም አባት) በኢትዮጵ የተሰየመው የክርስትያን ሀይማኖት ከመከሰቱ ከ 2000 ዐመታት በፊት ነው። ደሞም የእስልምና ሀይማኖት ከመታወጁ ከ 2600 ዐመታት በፊት ነው። እስከዛሬ መቶ ሀምሳ ዐመት ድረስ መላው አፍሪካ እና ዛሬ የአትላንቲክ ውቅያኖስ የተሰኘው ሁሉ ኢትዮጵያ ይባል ነበር። የአውሮፓ መርከበኞች ከ 150 ዐመት በፊት ይይዙት የነበረው ካርታ ላይ ይህን ሀቅ ታገኘዋለህ። ሀይማኖት ሌላ፣ ሀገር ሌላ ነው። ሀይማኖት የግል ነው። ሀገር የጋራ ነው። ከጎሳችን ውጪ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ የተወለድነውን ሰዎች ሁሉ በጋራ የሚያገናኘን ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ነው። ስለ እዚህ ነው ይህን ቃል መጣል የሌለብን።
  • Mulatu Aderajew ዶ/ር አብይ ድብቅ አላማ ካላቸው ሰዎች ውስጥ አንዱ ነው ም/ት ለምን “ኢትዮጵያ”ቆርጦ ጣለ? እሱም እንደ ህወሀት ኢትዮጵያን ስለማይወድ ነው።ይህ ውህድ ፓርቲ ባይሳካለት ደስ ይለኛል።

    Mulatu AderajewMulatu Aderajew replied

      3 replies   1 hr

  • Fikre Tolossa ወዳጄ መካሻ
    እላይ የጠቀስካቸው ሀገራት በጎሳ ተከፋፍለው ሀገራቸውን አይጠሉም። የሀገራቸው ስም ሊቀይሩ አይናቆሩም። በሀገራቸው ፍቅርና አንድነት ላይ ተመሳሳይ አቁዋም ስለ አላቸው የሀገራቸውን ስም ያልያዘ ፓርቲ ቢመሩ ችግር የለውም። በኛ ሀገር ላይ ጎሰኝነትና ክልል እንዴት እንደነገሡ ካንተ የተሰወረ አይደለም። የኛ ሁኔታ ከእነዛ የሀገራቸው ማንነት እና ልዐላዊነት ጥያቄ ውስጥ ካልገቡ ሀገራት ጋራ በፍጹም የማይገናኝ ነው። ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል። ጎሰኝነትና ዘረኝነት ሀገሪቱን ሊበጣጥስዋት በአሰፈሰፉበት ወቅት ብቸኛው መድህን ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው።
  • ወይዘሮ ገለቡ ፋሪስ ፕ/ር ሆን ተብሎ ነው ኢትዮጵያ የሚለው የተወገደው ። እነ ምዕራባውያን እንደፈለጉ በሚምነሸነሹበት ሀገር ኢትዮጵያ የሚል የድል አድራጊነት : የሀይማኖት : የአንድነት : የነፃነት እና የእግዚአብሔር ሀገር ምልክት የሆነ የአርማን ስም እንደት ያፌታውያን ወደውና ፈቅደው በዛች ቅዱስ ምድር የግማደ መስቀሉ መገኛ : የታቦት ፂወን መገኛ: የላሊበላ ዳግማዊት እየሩሳሌም መገኛ: የቅዱስ ዋንጫው መገኛ: የSee more
  • Gizaw Cars የጎሳ ፓርቲ (ethnic based political party) በህገ መንግስቱ ካልተወገደ በስተቀር ሽኩቻውም ማፈናቀሉም ወዘተ ይቀጥላል። Ethnic based Government means Apartheid system. There is no democracy in Apartheid!

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.